2018-07-06 13:39:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለሐምሌ ወር ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ፡ ብቸኝነት የሚሰማቸውን ካህናት ማገዝ ያስፈልጋል።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለሐምሌ ወር ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ፡ ብቸኝነት የሚሰማቸውን ካህናት ማገዝ ያስፈልጋል።

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 26/2010 ዓ.ም  ለሐምሌ ወር 2010 የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ይፋ ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው ለሐምሌ ወር መላው ምዕመን እንዲጸልይበት ያስተላለፉት የጸሎት ሐሳብ በዚህ የሐምሌ ወር ስለካህናትና ሐዋርያዊ ሥራዎቻቸው ከእኔ ጋር ጸልዩ!” ማለታቸውን ካስተላልፉት የቪዲዮ መልእክት ለመረዳት ተችሉዋል።

በእዚህ በሚመጣው የሐምሌ ወር በጋራ በመሆን “በሐዋርያዊ ሥራዎቻቸው ድካምና ብቸኝነት የሚሰማቸው ካህናት ከጌታ ጋር ባላቸው ቅርበትና ከሌሎቸ ካህናት ወንድሞቻቸው ጋር ባላቸው ወዳጅነት ውስጥ መጽናናትና ድጋፍ እንዲያገኙ እንጸልይላቸው” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ልማዳዊ በመሆነ መልኩ ለእያንዳንዱ ወር የሚሆን የተለያየ ዓይነት የጸሎት ሐሳብ ይፋ በማድረግ ምዕመናን በጸሎቱ እንዲካፈሉ ጥሪ እንደ ሚያቀርቡ ይታወቃል።

በተለይም በብርቱ ችግር ውስጥ ያሉ፣ ብቸኝነት፣ ድካምና ብርታት ማጣት ለሚሰማቸው ካህናት አናንተ ብርታት እንድትሆኑዋቸውና ሁሉም ክርስቲያኖች ቆሞሶቻቸው (ካህናቶቻቸው) ድጋፍ ሲያስፈልጋቸው ከጎናቸው ይቆሙ ዘንድ እጸልያለሁ ብለዋል። በእዚህ አጋጣሚ እኛም በመጪው የሐምሌ ወር በተለያዩ ሐዋሪያዊ የሥራ መስኮች ለተሰማሩ ካህናት እና ቀሳውስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያቀረቡትን የጸሎት ጥሪ ተቀበለን ካህናቶቻችን ብርታትን ያገኙ ዘንድ ልንጸልይላቸው ይገባል ለማለት እናወዳለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.