Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ ሰደተኞችን መንከባከብ ያስፈልጋል ማለታቸው ተገለጸ።

በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ - REUTERS

06/07/2018 16:46

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ ሰደተኞችን መንከባከብ ያስፈልጋል ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 3/2013 ዓ.ም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን አሳፍሮ ከሊቢያ ሚስራታ ከሚባል ወደብ ተነስቶ ላምፓዲዛ ወደ ምትባለው የጣሊያን የወደብ ከተማ በመቅዘፍ ላይ የነበረ ጀልባ በደረሰበት የባሕር ላይ አደጋ በጀልባዋ ላይ የነበሩ ከ369 በላይ የሚሆኑ አፍሪካዊያን ስደተኞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው የሚታወስ ሲሆን 155 ያህሉን ደግሞ ከሞት መታደግ እንደ ተቻለ ይታወሳል። ይህ አሳዛኝ የሆነ ገጠመኝ ከተከሰተ እነሆ አምስት አመታትን አስቆጥሩዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አደጋው ወደ ተከሰተበት ወደ ላምፓዱዛ ከእዚህ ቀደም ተጉዘው ከአደጋው የተረፉ ስደተኞችን መጎብኘታቸው እና በእዚህ አሰቃቂ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ደግሞ ሕግዚኣብሔር ነብሳቸውን በመንግሥቱ ይቀበል ዘንድ በስፍራው ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን እነሆ ይህ አሰቃቂ አደጋ ከተከሰተ ከአምስት ዓመታት በኃላ በዛሬው ዕለት ማለትም በሰኔ 29/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ስደተኞች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸውን እና ከእዚህ ቀደም በላምፓዱዛ ሕይወታቸውን ያጡትን ስደተኞች በመስዋዕተ ቅዳሴያቸው ማስታወሳቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር ለስደተኞች እጃችንን እንድንዘረጋ ይፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው መንግሥታት የሌሎችን ሀገሮች መልካም ጎኖች መመልከት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል። ስደተኞችን ተቀብለው በመርዳት ላይ የሚገኙትን በጎ አድራጊዎችን ያመሰገኑት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ስደተኞ በእንግደነት የተቀበሉዋቸውን ሀገራት ሕግ እና ስነ-ስረዓት እንዲጠብቁ እና ከአዲሱ ማሕበረሰብ ጋር መዋዐድ እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኃላ በወቅቱ ከሊቢያ ሚስራታ ከሚባል ወደብ ተነስቶ ላምፓዲዛ ወደ ምትባለው የጣሊያን የወደብ ከተማ በመቅዘፍ ላይ የነበረ ጀልባ በደረሰበት የባሕር ላይ አደጋ በጀልባዋ ላይ የነበሩ ከ369 በላይ የሚሆኑ አፍሪካዊያን ስደተኞ ነብሳቸውን ያጡበትን አደጋ በፍተኛ ደረጃ ልባቸውን ለሐዘን የዳረገ ክስተት መሆኑን በመግለጽ  ምንም ዓይነት የጉዞ እቅድ ባልተቀመጠበት ሁኔታ አደጋው ወደ ደረሰበት የጣሊያን የወደብ ከተማ ወደ ሆነቺው ላምፓዱዛ ተጉዘው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳርጋቸውን ቀደም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መሳውዕተ ቅዳሴ ላይ እንደ ገለጹት “ግላዊነት የተላበሰ ዓለም አቀፋዊነት” በዓለማችን ላይ እየተንሰራፋ መምጣቱ እንደ ሚያሳዝናቸው ቅዱስነታቸው በወቅቱ መናገራቸው ይታወሳል።

ስደተኞች የምግብ ብክነት ሰለባዎች ናቸው

ቅዱስነታቸው በዛሬው ቀን ማለትም በሰኔ 29/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የዛሬ 5 ዓመት ገደማ ነብሳቸውን በበሕር ላይ አደጋ ላጡ ስደተኞችን ለማስታወስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በወቅቱ ከአደጋው የተረፉ ስደተኞች እና የተለያዩ ስደተኞችን የሚረዱ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ያካተተ ከ200 በላይ ሰዎች ይህንን የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት መታደማቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት የጀመሩት በወቅቱ ከትንቢተ አሞጽ ከምዕራፍ 8፡4 ጀመሮ ተወስዶ በተነበበው የመጀመሪያው ምንባብ ላይ ተመርኩዘው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “እናንት ችግረኞችን የምትረግጡ፣ የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ላል፤“በምድር ላይ ረሐብን የምሰድበት ዘመን ይመጣል፤ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሐብ እንጂ፣ እንጀራን  መራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም” (አሞጽ 8፡4-6) በማለት እግዚኣብሔር በወቅቱ ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት በአደጉት ሀገራት የሚታየው የምግብ ብክነት ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ በድሎት የሚኖሩ ሀገራትን በር እንዲያንኳኩ እንዳስገደዳቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ሰብአዊ ላፊነት ለመውሰድ የቀረበ ጥሪ

የዛሬ አምስት ዓመት በላምፓዱዛ ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ባሳረጉበት ወቅት የሰው ልጆች አንዱ ለአንዱ ኃላፊነት እንዳለው ለመገልጸ በማሰብ “ወንድምህ የት አለ?” የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ በመጮኽ ላይ ይገኛል ይላል እግዚኣብሔር” በማለት አንዱ ለአንዱ ኃላፊነት ሊሰማው እንደ ሚገባ ገልጸው እንደ ነበረ በስበከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ከማቴዎስ ወንጌል 9፡9-13 ላይ ተወስዶ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርተው እንደ ገለጹት “ እያንዳንዱ ግለሰብ ለእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ሊሰማው እንደ ሚገባ ገለጸው “ጌታ በዓለም ውስጥ የተጨቆኑት ሁሉ እረፍት ለማሳረፍ እና ነጻ ለማውጣት ቃል ገብቷል፣ ነገር ግን ጌታ ይህንን ቃሉን ገቢራዊ ለማድረግ  የእኛን ትብብር ይፈልጋል፣ የወንድሞቻንን እና የእህቶቻችንን ችግር እና ተግዳሮት ለማየት እና ለመርዳት የእኛን ዐይን እና የእኛን እጅ ይፈልጋል” ብለዋል።

ሁሉንም ሀገራት በበጎ መልኩ መመልከት ይገባል

በስደተኞች እና በጥገኝነት ጠያቂ ሰዎች ጉዳይ ውስጥ በመኣከልነት ልጠቀስ የሚገባው ስደተኞች በብዛት የሚመጥባቸው ሀገራት እየገጠማቸው የሚገኘውን ተግዳሮት በስፋት መመልከት እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጻናት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ዛሬ በሰፊው ለሚታየው የስደተኞች ተግዳሮት ቀጥተኛ መልስ የሚሆነው የማኅበራዊ ትብብር መፍጠር እና ርኅራኄ ማሳየት ብቻ ነው፡ ይህም መልስ ብዙ ስሌት የሚጠይቅ መልስ ሳይሆን ነገር ግን ኅላፊነቶችን በጋር በመውሰድ ሀቀኛ እና በእውነተኛ መንፈስ የተሞላ ግመገማ በማድረግ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል። ፖሌቲካ ትክክለኛ ሊሆን የሚችለው ለሕዝብ አገልግሎት ሲውል ብቻ ነው፣ ሁሉንም ሰዎች ሲያካትት ብቻ ነው። ይህም ማኅበራዊ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ መብትን በማክበር ሊተገበር የሚገባው ጉዳይ ሲሆን ከገዛ ሀገሩ ማሕበራዊ ዋስታና በመጀመር በእዚያው ሳይታቀብ ከእዚያ ውጪ ያሉትን የሌሎችን ሀገሮች ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን በመመልከት የተሳሰረ አንድ ዓለም መፍጠር ይገባል።

ስደተኞች የተቀበሉዋቸውን ሀገሮች ባሕል፣ ሕግ እና ስነ-ስረዓት ጠብቀው ተዋህደው ሊኖሩ ይገባል

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠናቀቂያ ላይ እንደ ገለጹት ስደተኞ በእንግድነት የተቀበሉዋቸውን ሀገሮች ባህል፣ ሕግ እና ሰነ-ስረዓት ጠበቀው ከማኅበርሰቡ ጋር ተዋሕደው ሊኖሩ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ማሳሰባቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እንደ ደጉ ሳምራዊ ሰው በመሆን ስደተኞችን በመንከባከብ ላይ የሚገኙ ገለሰቦችን እና ተቋማትን አመስግነው እና የተስፋ ምንጭ መሆናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማበረታቻ ሰጥተው ሰደትኞችም በበኩላቸው የተቀበሉዋቸውን ማሕበረሰብ ስነ-ስረዓት፣ ባሕል እና ሕግ ጠብቀው መጓዝ እንደ ሚኖርባቸው ከገለጹ በኃላ ለወቅቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል። 

 

06/07/2018 16:46