Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፡ “ምድራችን ከመውደሟ በፊት የሚመለከታቸው አካላት በሕብረት መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል”።

ካርዲናል ፓሮሊን

06/07/2018 13:03

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፡ምድራችን ከመውደሟ በፊት የሚመለከታቸው አካላት በሕብረት መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል”።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ጴትሮ ጳሮሊን በአሁኑ ወቅት በሮም በመካሄድ ላይ ባለው ዓለምከፍ ጉባሄ ተስታፊዎች እንደ ገለጹት “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እና የወደፊቱ የምድር ላይ ሕይወት” በተመለከተ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሥነ ምሕዳር በተመለከተ ተያያዥነት ባለው መልኩ የሚያቀርቡት ሐስባ ሊመስገን የሚግባ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይለጊዮርጊስ

ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ይህንን የተናገሩት ከሰኔ 26/2010 ዓ.ም ጀምሮ በሮም ““የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እና የወደፊቱ የምድር ላይ ሕይወትን” እንከባከብ በሚል አርእስት በመካሄድ ላይ ባለው ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ እንደ ሆን አለመረዳት ተችሉዋል። ይህ ዓለማቀፍ ጉባሄ እየታካሄደ የሚገኘው በቅድስት መነበር ሥር በሚተዳደረው  የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት መነፈሳዊ ማኅበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም ውዳሴ ላንተ ይሁን በሚል አርእስት ለንባብ የበቁትን ሐዋሪያው መልእክት ሦስተኛ ዓመት የተዘከረበትን አጋጣሚ ተጠቅመው ባዘጋጀው ጉባሄ ላይ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ውዳሴ ላንተ ይሁን የሚለው የርእሰ ሊቃነ ጳጵእሳት ፍራንቸስኮስ ሐዋሪያዊ መልእክት የጋራ መኖሪያ የሆነችውን ምድራችንን ከብክለት እንከላከል የሚል ሐሳብ ያነገበ ሐዋሪያዊ መላክት ይታወሳል።

በእዚሁ ውዳሴ ላንተ ይሁን የሚለው የርእሰ ሊቃነ ጳጵሳት ፍራንቸስኮስ የዛሬ ሦስት ዓመት ይፋ ባደረጉት ሐዋሪያዊ መልእክት ላይ ተመርኩዘው በወቅት በጉባሄው ላይ ንግግር ያደርጉት የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን እንደ ገለጹት ይህ የቅዱስነታቸው ሐዋሪያዊ መልእክት በመላው ዓለም በመኢገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ስይንሲስቶችን ባካተተ መልኩ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጸው ይህ የሆነበት ምክንያት ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት ሁሉም ነገሮች ተያያዥነት እንዳላቸው አድርጎ በማቅረቡ የተነሳ እንደ ሆነ ካርዲናል ጴትሮ ጳሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ቫቲካን ስነ-ምዕዳርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ጉባሄ አስናዳች

ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተቀናጀ ስነ-ምዕዳርን፣ የጋራ መኖሪያችንን የመንከባከብ ቀዳሚ የሆነ ስፍራ ሊሰጠው ይገባል፣ የሰው ልጆችን እና ስነ-ምዕዳር ከፍተኛ የሆነ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ የተነሳ “ለሰብአዊው ቤተሰብ የማይነጣጠሉ ጉዳዮች መሆናቸውን”  በመግለጽ “ስለ ዓለም ተፈጥሮ ጥልቅ መንፈሳዊ እይታ እንዲኖር በማድረግ ስለ ፍጥረት 'ወንጌል' በመናገራቸው የተነሳ ከፍተኛ አድናቆት እንዳልቸው ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ተያያዥነት ያለው የስነ-ምህዳር አቀራረብ

የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን በንግግራቸው ጨምረው እንደ ገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ውስጥ ተያያዥነት ያለው የስነ-ምህዳር አቀራረብ እንዳለ ለዓለም በግልጽ ማሳየታቸውን ገለጸው “ከእግዚኣብሔር እና ከባልንጀሮቻችን ጋር ያለን ግንኙነት በተመሳሳይ መልኩ እናት ከሆነች ምድራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሊያካትት እንደ ሚገባው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቁልጭ አድርገው ማሳየታቸውን ካርዲናል ጳሮሊን ጨምረው ገለጸዋል።

ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚለው ሐዋሪያዊ መልእክታቸው በኀጢአት ምክንያት በሰው ልብ ውስጥ የሚፈጸመው አመፅ በተፈጥሮ ላይ በሚያስከትላቸው ችግሮች ላይ ተንጸባርቋል በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አመላክተው እንደ ነበረ የገለጹት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን በአሁኑ ወቅት ባለው ዓለማችን በከፍተኛ መልኩ እየተንጸባረቀ ባለው ተጠቅመህ ጣል “use and throwway” በሚለው ባሕል የተነሳ “በተፈጥሮ ላይ ከፍተኝ ጉዳት በማደርሱ የተነሳ ምድራችንን ለከፍተኛ አደጋ መዳረጉዋን” በመገለጽ አጣዳፊ በሆነ መልኩ “የሰው ልጆችን የእድገት ሂደት አመጣጥን፣ ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ሁኔታዎችን የምናስተዳድርበት ሁኔታ እና የአኗኗር ዘይቤአችንን መለወጥ? እንደ ሚገባን የሚያሳስቡ መሆናቸውን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን አሳስበዋል።

የካቶሊክ ዶክትሪን (አስተምህሮ)

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ስለ ፍጥረት በተመለከተ ያለው ግንዛቤ ዓለም እግዚአብሔር "ለፍጡራን ሁሉ የሰጠው ውድ ስጦታ እንደ ሆነ” አድጎ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የገለጹት ካርዲናል ፓሮሊን “አጽናፈ ሰማይ "እግዚአብሔር ሆን ብሎ የፈጥረው ነው ነገር ሲሆን የሰው ልጅ ከእዚያ ቀጥሎ የተሳሰበ ነገር ሳይሆን ነገር ግን የሰው ልጅ “የአጽናፈ ሰማያት መሠረታዊ ክፍል” በመሆኑ የተነሳ በእግዚኣብሔር አምሳያ በመፈጠራችን የተነሳ የሰው ልጅ ዋነኛው ጥሪ እግዚኣብሔር የፈጠረውን ፍጥረት መንከባከብ ነው እንጂ በተፈጥሮ ላይ የበላይነትን ማንጸባቅ እና ምድርን ማውደም አይደለም ብለዋል።

እኛ ሁላችን ተጠያቂዎች ነን

በንግግራቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቅድስት መነበር ዋነ ጸሐኢያ የሆኑት ካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርእስት የዛሬ ሦስት ዓመት ይፋ ያደርጉትን ሐዋሪያዊ መልእክት በተመለከተ እንደ ተናገሩት  ከእግዚኣብሔር፣ ከባልንጀራዎቻችን እና ከምድራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናክር እንደ ሚገብ ጠቅሰው ጥሪያችን እግዚኣብሔር የፈጥረውን መንከባከብ ነው፣ ኃላፊነታችን ደግሞ እግዚኣብሔር የሰጠንን ሥራ ማስፈጸም ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

06/07/2018 13:03