2018-06-29 17:12:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶስ፡ “የክርስቶስን ክብር ከመስቀሉ ለይተን ልንምለከት አንችልም” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶስ፡ “የክርስቶስን ክብር ከመስቀሉ ለይተን ልንምለከት አንችልም” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 22/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ በዓለ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በተከበረበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ቅዱስነታቸው ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሁላችንም ምልከታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማድረግ እንደ ሚገባን ገለጸው “የኢየሱስ ክብር እና የኢየሱስ መስቀል አብረው የሚሄዱ ሊነጣጠሉ የማይችሉ ሁለት እውነታዎች መሆናቸውን” ገለጸው በኢየሱስ ላይ አስተንትኖ ማድረግ እና ኢየሱስን መከተል ልባችንን በቅድሚያ ለእግዚኣብሔር መክፈትን የሚተይቅ ተግባር ነው ብለዋል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ፣ ቅዱስነታቸው በእዚህ አመት የተለያዩ ሀገራት ሊቀ ጳጳሳት አድርገው የሾሙዋቸው 30 ሊቀ ጳጳሳት እና በትላንትናው ዕለት ከ11 ሀገራት የተውጣጡ 14 አዲስ የተሾሙ ካርዲናሎች በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ መታደማቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክብር እና መስቀል

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የክርስቶስን ክብር ከክርስቶስ መስቀል ለይቶ ማየት በጣም አደገኛ የሆነ ነገር መሆኑን ገልጸው የክርስቶስን መስቀል ከክርስቶስ ክብር ለይተን የምናይ ከሆነ ግን እንዲሁ ፍቅር የለሽ፣ አገልግሎት፣ ርኅራኄ፣ ሕዝብ የሌሽ ባዶ የሆን አክብር ሆኖ ይቀራል ብለዋል። እነዚህን የክብር መገለጫ የሆኑትን ዋና ዋና ነገሮች ከግምት በማስገባት ኢየሱስ ባዶ የሆነ ክብር ማስወገድ እንደ ሚገባቸው ኢየሱስ ደቀ-መዛሙርቱ እና ቤተ ክርስቲያኑ ቦዶ ከሆነ እና መስቀል ከሌለው ክብር መጠበቅ እንደ ሚገባቸው አሳስቡዋቸው እንደ ነበረ ቅዱስነታችወ ጨምረው ገለጸዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

የኢየሱስ ክብር እና  የኢየሱስ መስቀል አብረው የሚሄዱ እና በፍጹም ሊነጣጠሉ የማይችሉ ነገሮች ናቸው፣ ምክንያቱም መስቀሉን ችላ ብለን አስደናቂ ወደ ሆነ የሚያምር ክብር ብንገባ ራሳችንን እናታልላለን፣ ምክንያቱም ይህ የእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን የጠላት ቀልድ ነው” ።

ኢየሱስ ከየትኛውም ዓይነት የባርነት ቀንበር ነጻ ያወጣል

“ኢየሱስ የተቀባ ነው፣ የጠፋውን እና የተጣለውን ለማንሳት በመመኘት ከመንደር ወደ መንደር ይጓዝ እንደ ነበረ” በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሞተውን፣ የታመመውን፣ ተስፋ የቆረጠውን ሰው ሁሉ በመቀባት ከማንኛውም ዓይነት የባርነት ቀንበር ሕዝቡን ነጻ ያወጣ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገለጸው ለእርሱ ቅባት ምስጋና ይግባውና ማነኛውም ዓይነት የባርነት ቀንበር ስብርብሩን ወቱዋል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል

በዚህ ዓይነት ሁኔታ ኢየሱስ ሁሉንም ኃጢአተኞች፣ የተሸነፉ ሰዎችን፣ የታመሙትን፣ አረማዊያንን ማነኛውንም የሚያገኛቸውን ሰዎች ሁሉ በመቀባት የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ሆነው እንዲሰማቸው አድርጉዋል። ኢየሱስ አካላዊ እንቅስቃሴውን በመጠቀም አንተ የእኔ ነህ ይላል። ልክ እንደ ጴጥሮስ እኛም የሰማነውን መመስከር ብቻ ሳይሆን፣ የህይወታችንን ተጨባጭ ልምዶች ከከንፈኞቻችን እና ከልባችን ጋር ልናመሳክር ይገባናል፣ እኛ ከሞት እንደ ተነሳን፣ እንክብካቤ እንደ ተደረገልን፣ በቅዱስ ቅባት የተቀባን እና በተስፋ የተሞላን መሆናችንን መገንዘብ እና በአፋችን መመስከር ይገባናል።

“የእዚህ ዓይነቱ መሕረታዊ ፍቅር በየአቅጣቸው በመሄድ በማነኛውም ዓይነት የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሳይቀር እንዲካፈሉት ልናደርግ እንደ ሚገብ በመገልጽ ስበክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ተገባር ግን ለራሳችን ምቾት መልካም ስም የማትረፊያ አካሄድ ሊሆን ግን አይገባው ብለዋል።

ክፉ ነገር የሚያንሾካሽከውን ነገር ማዳመጥ ዓይኖርብንም

የቅዱስ ጴጥሮስን ሕይወት እና ምስክርነት በምናሰላስልበት ወቅት የአንድ ሐዋሪያ ሕይወት እና ተገባር ምን ማለት እና ምን እንደ ሆነ መማር እንደ ሚጠበቅብን የገለጹት ቅዱስነታቸው ብዙን ጊዜ ከጌታ ቁስሎች ርቀን መጓዝ በመቻላችን ክርስቲያኖች እንደ ሆንን ሆኖ እንዲሰማን የሚያደርግ ስሜት ሊሰማን የሚችል ቢሆንም ነገር ግን በተቃራኒው ኢየሱስ የሰዎችን ስቆቃ ሁሉ ይነካ እንደ ነበረ ሁሉ እኛም የሰዎችን የእለት ተእለት ሰቆቃ ወረድን መመልከት ይኖርብናል ካሉ በኃላ የክርስቶስ ክብር ተካፋይ ለመሆን በቅድሚያ የእርሱ መስቀል ተካፋዮች ልንሆን ይገባል ካሉ በኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.