Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ሁልጊዜ የተጨነቁ ሰዎችን ምስል በፊት ለፊታችሁ አኑሩ” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ - AP

29/06/2018 17:09

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ሁልጊዜ የተጨነቁ ሰዎችን ምስል በፊት ለፊታችሁ አኑሩ” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን ቀደም ሲል የጠቀሰውን  የተናግሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 21/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከ11 ሀገረት ለተውጣጡ ጳጳሳት የካርዲናልነትን ማዕረግ በሰጡበት ወቅት ባድርጉት ስብከት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት ስብከት በማርቆስ ወንጌል በምዕራፍ 10፡32-45 ላይ የተጠቀሰው ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት በነበረው ሁኔታ ላይ መስረቱን ያደገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለ14 አዳዲስ ካርዲናሎች ኢየሱስን መከተል እንደ ሚገባቸው ገልጸው ይህም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የራስን ጥቅም እና ሐሳብ ብቻ ለማራመድ ያለንን ከንቱ የሆነው ራስ ወዳድነት የሚንጸባረቅበት ሕይወት ማስወገድ እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ገለጸው በወቅቱ ከማርቆስ ወንጌል ከምዕራፍ 10፡32-45 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና የኢየሱስን የመጨረሻ የእዚህ ምድሮ ኖሮን በሚያመልክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የልብ መገለጽ

ወደ ኢየሩሳሌም ለመውጣት በመንገድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ አስቀድሞ ስለሞቱ ለሦስት ጊዜያት ያህል ከነገራቸው በኃላ ፊት ለፊታቸው ይሄድ በነበረበት ወቅት ደቀ መዛሙርቱ እና ሌሎች ይከተሉት የነበሩ ሰዎች ፈርተው እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነ ወቅት እንደ ሆነ ጠቅሰው “ልባችን በውስጣችን ያለውን ፍላጎትና ውጥረት መናገር ይችላል” ብለዋል። በደቀ-መዛሙርቱ ልብ ውስጥ ተደብቆ የነበረው “የክብር ቦታ የመፈለግ፣ የቅናት፣ የምቀኝነት፣ የክርክር፣ መሸሸግያ የመፈለግ እና ስምምነትን የማጣት” የመሳሰሉ  ምስጢሮች ሁሉ ኢየሱስ መከራውን ሊቀበል በተዘጋጀበት ወቅት ቀስ በቀስ መገለጥ መጀመራቸውን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ልቦናቸው ማስተዋል እንደ ሚገባው

ኢየሱስ በደቀ-መዛሙርቱ ድክመቶች ላይ ሳያተኩሩ ወደ ፊት መጓቱን ቀጥሎ እንደ ነበረ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ጌታ የደቀ-መዛሙርቱን ቀልብ ለመግዛት በመፈለግ ዓይኖቻቸውን እና ልቦቻቸውን እንዲከፍቱ ለማስቻል “በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋይ ይሁን” (ማርቆስ 10፡43) ብሎ መልሶላቸው እንደ ነበረ አስታውሰው ኢየሱስ ደቀ-መዛሙርቱ የነበራቸውን ከንቱ የሆነ እና ራስ ተኮር የሆነ አስተሳሰብ ማስወገድ እንደ ሚግባቸው ገልጸው በአንጻሩ ግን መልካም የሆኑ የደቀ መዛሙርቱን ማኅበር ሊገናባ የሚችል መልካም የሚባሉ አስተሳሰቦችን በልባቸው እንዲያሳድሩ ገልጾላቸው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ልባቸው መንፍሳዊ ለውጥ ማምጣት ይኖርበታል

“ኢየሱስ የሚያስተምረው ትምህርት ሁሉ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ የሚረዳን ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የራሱን ጥቅም እና ፍላጎት ከማስቀደም ይልቅ እግዚኣብሔር አብን እንድትሻ በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ሚረዳት ገልጸው እውነተኛው ማንነታችን የሚገለጸው ከተጨነቁ እና ከተጠበቡ ሰዎች ጋር ፊት ለፊት በምንገናኝበት ወቅት እንደ ሆነ ጠቅሰው የተጨነቁ እና የተጠበቡ ሰዎችን ምስል ከፊት ለፊታችን ማኖር ቤተ ክርስቲያንን የሰጠችንን ተልዕኮ በአግባቡ እንድንወጣ እንደ ሚያስችል ጠቁመው ነገር ግን ከእዚህ በተቃራኒ በመሄድ የተጎሳቆሉ እና የተጠበቡ ሰዎችን ምስል ከፊታችን በምናስወግድበት ወቅት ሁሉ የራሳችንን ጥቅሞች እና ምቾቶች ብቻ ማሳደድ እንጀምራለን ብለዋል።

ልባችን ለአገልግሎት መዋል ይኖርበታል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከ11 ሀገራት ለተውጣጡ 14  ካርዲናሎች የካርዲናልነት ማዕረግ በሰጡበት ወቅት ባሰሙት ስብከት ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት ኢየሱስ ከእነርሱ ፊት ለፊት እየተጓዘ እንደ ሚሄድ ገልጸው ኢየሱስ በትህትና የደቀ-መዛሙርቱን እግር ዝቅ ብሎ አጥቦ እንደ ነበረ፣ እንዲሁም በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት ራሱን ዝቅ አድርጎ እንደ ነበረም አስታውሰው ካርዲናሎችም የተጠሩት በተመሳሳይ መልኩ ኢየሱስ ያሳየውን ትህትና እና ራስን ዝቅ የማድረግ መንፈስ ለመተግበር መሆኑን ቅዱስነታቸው ጨምረው ከገለጹ በኃላ “ለእኛ ሊሰጠን ከሚችለው የላቀ ክብር ማግኘት የምንችለው፣ ለእኛ ሊሰጥ ከሚችል ታላቅ ሽልማት የሚገኘው ክርስቶስ ታማኝ ሕዝቡን እንዳገለገለ ሁሉ እኛም የክርስቶስን ታማኝ ህዝብ ስናገለግል ብቻ ነው” ካሉ በኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

29/06/2018 17:09