Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ዓለም አክብሮት መስጠት የሚጀምረው ለሰው አካል ክብር በመስጠት ነው”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጳጳሳዊ የስነ-ሕይወት ተቋም ባዘጋጀው ጉባሄ ላይ በተካፈሉበት ወቅት

26/06/2018 16:03

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ዓለም አክብሮት መስጠት የሚጀምረው ለሰው አካል ክብር በመስጠት ነው”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን ቀደም ሲል ያነበባችሁትን የተናገሩት በአሁኑ ወቅት ከሰኔ 18 እሰክ 19/2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ያህል  እየተካሄደ በሚገኛው ጳጳሳዊ የስነ-ሕይወት ተቋም ባዘጋጀው አጠቃላይ ጉባሄ ላይ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አንድ መንደር በመሆን ላይ በምትገኘው ዓለማችን ውስጥ ስነ-ሕይወትን በተመለከተ ያለውን አመለካከት ለመገምገም የተጠራ አጠቃላይ ጉባሄ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “እኩል የሆነ አጀማመር። ግን ከእዚያን በኃላስ? ዓለም አቀፍ ኃላፊነት” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት የሚደረግ አጠቃላይ ጉባሄ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

"የሰው ልጅ ሥነ ምህዳር" በሁሉም ደረጃዎች የሚገኙትን "ሥነ-ምግባራዊና መንፈሳዊ ባህሪያትን" እንዲያመላክት እና እንዲያበረታታ እንደሚገባው በመጥቀስ ንግግራቸውን የጀመሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰው ልጆች ሕይወት ዙሪያ የሚደረጉት ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገለጸው ነገር ግን የሰው ልጆችን አፈጣጠር ሰፋ ባለ መልኩ ማካተት ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስነታቸው "የሰው ልጅ ሕይወት በቃልና በአስተሳሰብ፣ በፍቅር እና በመንፈስ የዓለምን ትዕይንት ፈንጥቆ እንደ ሚያሳይ" ጨምረው ገለጸዋል።

ሕፃናት ለእጦት እና ለጦርነት ሲጋለጡ፣ አረጋዊያን ሲዘነጉ "እኛ ግን በተቃራኒው ሞትን የሚያቀላጥፍ " ቆሻሻ የሆኑ ተግባራትን እንፈጽማለን” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ክርስቲያኖች በአመለካከታቸው ጠንካራ በመሆን እና ከመቼው ጊዜ በላይ ራሳቸውን በማዘጋጀት እንዲህ ዓይንቱን በኃጢይት በተደግገፉ ክፉ ተግባራት የተነሳ እይተከሰቱ የሚገኙ ተግባራትን  ለመቀልበስ እና ለመዋጋት መነሳሳት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ክርስቲያንዊ የሆነ ሕይወት ስነ-ምግባር ጥናት እና ምርምር በአንድ ከታመመ ሰው በማድረግ መጀመር እንደ ማይገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያናዊ የሕይወት ሰነ-ምግባር ጥናት ሊጀምር የሚገባው “በማይቀለበስ የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት ዙሪያ ላይ እና በተለያዩ ደረጃዎች እና የታሪክ ሂደቶች ውስጥ  የሚገኘውን የሰው ልጆችን ሕይወት እግዚኣብሔር እንደ ሚወድ ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ከሰው ልጆች አካል በመጀመር የተሟላ እይታ የሰው ልጆች ያላቸውን ግንኙነት እና በሕይወት ውስጥ  ያላቸውን ልዩነት በእነዚህ ግንኙነቶች እና ልዩነቶች ላይ ባተኮረ መልኩ ሊወሰድ እንድ አሚገባው የጠቀሱት ቅዱስነታቸው የሰው ልጅ ከአከባቢው ጋር እና ከሌሎች ስነ-ፍጥረታት ጋር ሊገናኝ የሚችለው በአካሉ አማካይነት እንደ ሆነ ጠቅሰው ዓለም የእግዚኣብሔር ስጦታ እንደ ሆነ የሚያምኑ ሰዎች በቅድሚያ አካላችን የእግዚኣብሔር ስጦታ እንደ ሆነ ማመን ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የሕይወት ባሕል ሁልጊዜ ወደ ሕይወት የመጨረሻው መድረሻ እንደ ሚያመልከት የገለጹት ቅዱስነታቸው ማንኛውም የክርስቲያን ጥበብ “የሰው ልጅ በእግዚኣብሔር ሕይወት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን መጠራታቸውን” ከሞት በኃላ በእግዚኣብሔር ዘላለማዊ ፍቅር ውስጥ እንደ ምንኖር፣ በሚታይ እና በማይታይ መልኩ በእግዚኣብሔር ውስጥ እንደ ምንኖር መመስከር ይኖርበታል ካሉ በኃላ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

ጳጳሳዊ የስነ-ሕይወት ተቋም በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደር እና እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1994 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ የቋቋመ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ዓላማውም “የምድብለ ዘር ምንድስና በሕይውት ላይ የሚኖረውን ተጽኖ ማጥናት እና በሕይወት ላይ የሚቃጡ ማንኛውንም ተግባሮች መከላከል፣ ሕይወትን በተመለከተ ቤተክርስቲያን ያወጣችሁን አስተምህሮ ማስቀጠል እና ሕይወትን በተመለከተ የክርስቲያን ሰነ-ምግባር አስተምህሮችን” የሚሰጥ ጳጳሳዊት ተቋም እንደ ሆነ ይታወቃል።

 

 

26/06/2018 16:03