2018-06-25 15:55:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ቤተሰብ በሕይወት ቤተ መቅደስ ውስጥ የእግዚኣብሔር ተባባሪዎች ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ “ቤተሰብ በሕይወት ቤተ መቅደስ ውስጥ የእግዚኣብሔር ተባባሪዎች ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 17/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎ በዕለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከሉቃስ ወንጌል 1፡57-66.80 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጥመቁ ዩሐንስ መወለድን በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ደንብ መስረት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም እና የመጥቁ ዩሐንስ ልደቶች ብቻ የሚከበሩ ሲሆን የሌሎች ቅዱሳን ልደት በቅዱስ ዩሐንስ ልደት ውስጥ ተጠቃሎ የሚከበር እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 17/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ምከተለው ተጉመነዋል።  አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው ዕለት ስረዓተ አምልኮ የመጥመቁ  የቅዱስ የሐንስ ልደት እንድናከብር ይጋብዘናል። የእርሱ መወለድ የወላጆቹን ኤልሳቤጥ እና የዘካሪያስን ሕይወት እንዲበራ ያደርገ ሁኔታ ሲሆን ዘመዶቻቸውን እና ጎሬቤቶቻቸውን መደሰት እና መገረም ያካትታል። እነዚህ አረጋዊያን የነበሩ የእርሱ ቤተሰቦች ሕልም የነበራቸው ሰዎች የነበሩ እና ለእዚያም ቀን ዝግጁ የነበሩ ሰዎች ቢሆኑም፣ ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው ያንን ቀን በተስፋ መጠበቅ አቁመው ስለነበረ፣ የመገለል፣ የውርደት፣ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ደርሶባቸው ነበር።

አንድ ወንድ ልጅ እንደ ሚወልድ በተነገረው ወቅት ዘካሪያስ በጣም ተገርሞ ነበረ ምክንያቱም በጣም አርጅቶ ነበረ፣ ሁለቱ ቢሆኑ እድሜ ጠገብ ነበሩ፣ የተፈጥሮ ሕግጋት አይፈቅድላቸውም ነበር። በእዚህም የተነሳ ይህንን ጉዳይ አላመነም ነበር፣ ባለማመኑ የተነሳ ደግሞ ዲዳ እንዲሆን ተደረገ። ይህ ምልክት ነበረ። ነገር ግን እግዚአብሔር በሰው አስተሳሰብ እና በሰው ውስን የሰብአዊ ችሎታዎች ላይ አይወሰንም። በእግዚኣብሔር መተማመን እና በእግዚኣብሔር ምስጢር ፊት በዝምታ መጠበቅ መልካም የሆነ ነገር ነው፣ በትህትና እና በዝምታ የእርሱን ተግባር መጠባበቅ ይሻላል፣ ይህ ተግባሩ በታሪክ በተደጋጋሚ የተከሰተና የሰው ልጆች ከሚያስቡት በላይ ብዙ ታላቅ ነገር አድርጉዋል።

እናም አሁን በኤልሳቤጥ እና በዘካርያስ ሕይወት ውስጥ የተከናወነው ሁኔታ "ለእግዚአብሔር ምንም ነገር እንደ ማይሳነው" ተረድተው ለእርሱ ትልቅ ክብር ሲሰጡ እናያለን። ዛሬ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ሉቃስ 157-66.80) የሕጻኑን መወለድ ካበሰረ በኃላ በመቀጠል ለልጁ ስለሚወጣለት ስም ይናገራል። ኤሊሳቤጥም ከባሕላቸው ውጪ አስገራሚ በሆነ መልኩ በመሄድ ስሙዩሐንስ ተብሎ ይጠራልበማለት ይህ ሕጻን አሁን በእዚህ እድሜ ያልተጠበቀ በመሆኑ የተነሳ ነጻ የእግዚኣብሔር ስጦታ በማለት ትሰይመዋለች፣ ምክንያቱም ዩሐንስ ማለት ነጻእግዚአብሔር ጸጋን ሰጠንማለት ነው። እንዲሁም ይህ ሕፃን ጠንካራ እና በትዕግሥት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሚጠባበቁ ለድሆች ምስክር ነው።

ዘካሪያስም ባልተጠበቀ መልኩ ለሕጻኑ የመጠሪያ ስም ለማውጣት ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ በእዚያ ላይ የልጁን ስም ጻፈ፣ ምክንያቱም ዲዳ ስለነበረ ነው፣ እናምወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱ ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ መናገር ጀመረ

በአጠቃላይ መጥምቁ ዮሐንስ የተወለደበት ሁኔታ የሚያስደንቅ የደስታ ስሜት የፈጠረ፣ ድንገተኛ እና ምስጋና የተቸረው ሁኔታ ነበረ። ድንገተኛ፣ አስደናቂ እና ምስጋ። ሕዝቡ በታላቅ አግራሞት በመደነቅጎረቤቶቹም ሁሉ በፍርሀት ተሞሉ፤ ይህም ሁሉ ነገር በደጋማው የይሁዳ ምድር ሁሉ ተወራ

ወንድሞቼ እና እህቶቼ አማኛ የሆነው ሕዝብ አንድ የተደበቀ እና ትሁት የሆነ አንድ ታላቅ ነገር እየተከሰተ  እንደ ነበረ ስላወቀይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” በማለት ይጠይቃል። የእግዚአብሄር ታማኝ ህዝቦች በእምነት፣ በመደነቅ እና በመገረም እምነትቱን በደስታ መኖር ይችላል። በእዚያ የነበሩ ሕዝቦች በተከሰተው ታላቅ በሆነው ነገር ተገርመው ስያወሩ የነበሩትን ነገር እንመልከት፣ በመጥመቁ ዩሐንስ መወለድ የተነሳ ሕዝቡ ደስታ ሲሰማው፣ በጣም ሲገረም፣ በመደነቅም ጭምር በምስጋና ሲደሰት እናያለን። ይህን በመመልከትየእኔ እምነት እንዴት ነው? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። እምነቴ በደስታ የተሞላ ነው ወይስ እንዲያው ሁሌ ተመሳሳይ በሆነ እና ወጥ በሆነ መንገድ ላይ ብቻ ነው እየተጓዘ የሚገኘው? የእግዚኣብሔርን ድንቅ የሆነ ሥራ ስመለከት እደሰታለሁ ወይ? ስለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ስሰማ ወይም ደግሞ የአንድን ቅዱስ ሰው ሕይወት ስመለከት፣ ወይም በጣም ብዙ መልካም የሚባሉ ሰዎችን ስመለከት የጸጋ ስሜት በውስጤ ይሰማኛል ወይ? ወይስ ምንም ነገር በልቤ አይንቀሳቀስም? ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ማጽናኛ ይሰማኛል ወይስ የተዘጋው ነኝ? እያንዳንዳችን ሕሊናችንን በመመርመራእምነቴ እንዴት ነው? ለእግዚኣብሔር ድንቅ ተግባር ክፍት ነው ወይ? በማለት ራሳችንን እንጠይቅ፡ ምክንያቱም እግዚኣብሔር ሁሌም የሚያስገርመን አምላክ ነውና። የእግዚአብሔርን በሕይወቴ መገኛቱን በሚያስደንቅ ሁኔታ በአድናቆት ስሜት ውስጥ ሆኜ "አጣጥሜያለሁ" ወይ? የእመነት ቃላት የሆኑትን ደስታ፣ የመገረም ስሜት፣ የመደነቅ እና የማመስገን ስሜቶችን ልናጣጥም ይገባናል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የሕይወት ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር እንደ ሚገኝ ማመን እንችል ዘንድ ትርዳን። የእግዚኣብሔር እና የእኛ እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በማሳደግ ሂደት ውስጥ የእግዚኣብሔር የሥራ ተባባሪ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ትርዳቸው። እያንዳንዱ ቤተሰብ በሕይወት ቤተ መቅደስ ውስጥ የእግዚኣብሔር ተባባሪዎች ናቸው እያንዳንዱ ሕጻን በሚወለድበት ወቅት የደስታ፣ የመደነቅ ኣና የምስጋና ስሜት ሊፈጥር ይገባዋል።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.