2018-06-23 10:10:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ እርስ በእርስ ስንዋደድ እና ይቅር ስንባባል እግዚኣብሔር ይደሰታል።


ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም 23ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ  ወደ ሲውዘርላንድ ማቅናታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በወቅቱ በሲውዘርላን በሰኔ 14/2010 ዓ.ም እየተከበረ በነበረው ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት 70ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ለመገኘት ወደ እዚያው ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በውቅቱ በሲውዘርላንድ ዋና ከተማ በጄኔቫ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እርስ በእርስ ስንዋደድ እና ይቅር ስንባባል እግዚኣብሔር ይደሰታል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 6 ላይ ተወስዶ በተነበበው “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ታልይ ተመርኩዘው ያደርጉትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ተርጉመነዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ እርስ በእርስ ስንዋደድ እና ይቅር ስንባባል እግዚኣብሔር ይደሰታል።

በዛሬው ዕለት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል አባት፣ እንጀራ፣ ይቅርታ የሚሉትን ሦስት ዋና ዋን ቃላትን አቅፎ የያዘ ምንባብ ነው። እኛን ወደ እምነት ልብ የሚያደርሱን ሦስት ቃላት።

ጸሎቱ አባታችን ሆይ በማለት ይጀምራል። ከእዚያን በኃላ በሌሎች ቃላቶች ልንቀጥል እንችላለን፣ ነገር ግን ይህን የመጀመሪያውን ቃል መርሳት አንችልም፣ ምክንያቱም "አባት" የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ልብ ለመክፈት ቁልፍ በመሆኑ የተነሳ ነው። እንዲሁ በቀላሉ አባትበማለት በመጸለያችን ብቻ የክርስትና ቋንቋን እንጠቀማለን ማለት ነው። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን የምንጸልየው ለአንድ ፍጥረት ሳይሆን ነገር ግን ከሁሉም በላይ አባታችን ወደ ሆነው አምላክ እንጸልያለን። ኢየሱስ "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ" በማለት እንድንጸልይ ነው ያስተማረን እንጂ "የሰማይ አምላክ፣ አባት የሆንክ በማለት ግን አልንበረም። ከሁሉም በፊት እግዚአብሔር ዘለአለማዊ እና ረቂቂ ነው፣ ብለን ከመጸለያችን በፊት እግዚአብሔር አባት ነው ብለን እንጀምራለን።

ሁሉም የአባትነት እና የእናትነት መንፈስ የመነጩት ከእርሱ ነው (ኤፌሶን 315) እርሱ የጥሩነት እና የሕይወት ምንጭ ነው።አባትየሚለው ቃል ማንነታችን የሚገልጽ እና የሕይወታችንን ትርጉም የሚያሳይ ነው፡ ተወዳጅ የእግዚኣብሔር ልጆች እንደ ሆንን ያሳየናል። ከእነዚህ ቃላት ራሳችንን ከማግለል እና ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች የሚሰማቸው ዓይነት ስሜት እንድንላቀቅ ያደርገናል። አባት የሆነውን እግዚኣብሔርን እና ወንድም፣ እህቶቻችንን ሳይቀር እንድንወድ በማድረግ ምን መስራት እንደ ሚኖርብን ያስተምረናል። አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት የእኛ እና የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ነው። ስለእኔ እና የራሴ ስለሆኑ ነገሮች ሳይሆን፣ ሁሉም ነገር በአንተ በእግዚኣብሔር (“በስምህበመንግሥትህበፍቃድህ”) ውስጥ ነው ያለው ማለት ነው። በመጀመሪያ በብዝሃ ቁጥር ይናገራል። አባታችን ሆይ እነዚህ ሁለት ቀልል ያሉ ቃላት የመንፈሳዊ ሕይወት ፍኖተ ካርታን ናቸው በእየለቱ በቀኑ መጀመሪያ ላይ ራሳችንን በመስቀል ምልክት በምናማትብበት ወቅት ወይም ማንኛውንም ጠቃሚ የሚባል ሥራ ከማከናወናችን በፊት አባታችን ሆይ በምንልባቸው ወቅቶች ሁሉ ስር መሰረታችንን እንስታውሳለን። በእዚህ ሥር አልባ በሆነ ማኅበርሰብ ውስጥ ሥር መስረታችንን ማስታወስ በጣም ቃሚ የሆነ ነገር ነው። አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ሥር መሰረታችንን ያጠናክረዋል። አባት ባለበት ቦታ ሁሉ ማንም አይገለልም፣ ፍርሃት እና ጥርጣሬ ሊያሰንፉን በፍጹም አይችሉም። በድንገት ሁሉንም መልካም ነገሮች እናስታውሳለን ምክንያቱም በአባታችን ልብ ውስጥ እኛ ባዕዳን አይደለንም ነገር ግን የእርሱ ተወዳጅ ልጆቹ ነን። እርሱ እንዲሁ በቡድን ሰብስቦን በአንድ ቦታ አከማችቶን የሚያስቀምጠን አምላክ ሳይሆን፣ ነገር ግን በተቃራኒው አዲስ የሆነ ሕይወት በመስጠት አንድ ሰፊ የሆነ ቤተሰብ እንድንሆን ያደርገናል።

አባታችን ሆይ ከማለት በፍጹም መታከት አይኖርብንም።  ያለ አባት ልጆች እንደ ማይኖሩ እና በእዚህ ዓለም ውስጥ ማነኛችንም ብቻችንን እንዳልሆንን በሚገባ እንድናስታውስ ያደርገናል። በተጨማሪም ያለ ልጆች አባት እንደማይኖር እንድናስታውስ ያደርገናል፣ እኛ ብቻ አይደለንም አንድኛ ልጁ። አባታችን ሆይ በምንልበት ወቅት ሁሉ እያንዳንዱ የሰው ልጅ የእኛ አካል እንደ ሆነ እናስታውሳለን፣ በእዚህም የተነሳ አባታችንን በምንበድልበት ወቅት ሁሉ፣ እኛ የእርሱ ልጆች እንደ መሆናችን መጠን እንደ ወንድም እና እንደ እህት በመሆን ይህንን በደል መቃወም ይኖርብናል። ቤተሰባችንን በሚገባ በጥንቃቄ እንድንጠብቅ ተጠርተናል፣ ይህም በወንድሞቻችን መካከል ያለውን ልዩነት እንድናጠብ ይረዳናል። ይህ እንክብካቤ በማሕጸን ውስጥ ያሉ ገና ያልተወለዱ፣ በእርጅና ምክንያት መናገር የተሳናቸው ሰዎችን፣ ይቅርታ ለመድረግ በጣም የከበደን ሰው፣ ድኾችን እና የተገለሉ ሰዎችን ያካትታል። ይህንን ነው አባታችን እንድንፈጽም የሚጠይቀን፣ በእርግጥ እንድንፈጽም የሚያዘን፡ እያንዳንዳችን እንደ ወንድም እና እንደ እህት ከልብ እንድንዋደድ፣ በወንድሞች እና በእህቶች መካከል ፍቅር እንዲኖር።

እንጀራ ኢየሱስ አባታችንን የእለት እንጀራችንን እንዲሰጠን እንድንተይቀው አስተምሮናል። ሌላ ተጨማሪ ነገር ሳይሆን እንጀራ እንድንጠይቀው ነው ያስተማረን፣ ይህም ማለት በሌላ ቃል ለሕይወታችን አስፈላጊ የሆነ ነገር ማለት ነው።  ከሁሉም በላይ ጤናማ እንድንሆን እና ሥራችንን በአግባቡ እንድናከናውን የሚረዳን እንጀራ ነው፣ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ግን በጣም ብዙ የሚባሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ይህንን እንጀራ አጥተው በመሰቃየት ላይ የገኛሉ። እዚህ ላይ እንጀራ እንዳይገኝ የምታደርጉ ሰዎች ወየውላችሁ! ለማለት እወዳለሁ። ሰዎች ለዕለታዊ ኑሮዋቸው የሚያስፈልጉዋቸው መሠረታዊ ምግቦች ለሁሉም ሰው ተደራሽ መሆን ይኖርባቸዋል።

በተጨማሪም የእለት እንጀራችንን መጠየቅ ማለትአባት ሆይ ተመሳሳይ የሆነ ሕይወት እመራ ዘንድ አግዘኝእንደ ማለት ነው። ሕይወት በጣም የተወሳሰበ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ብዙዎች የስልክ ጥሪዎች እና ጽሑፎች ላይ በማተኮራቸው ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ እየተንሸራተቱ የሚሄዱ የመስላል። የሌሎች ሰዎችን ፊቶች ለማየት ጊዜ አይኖራቸውም፣ ውስብስብ እና በተከታታይ ተለዋዋጭ ችግሮች ውስጥ በመግባት በውጥረት የተሞሉ ሆነው እየኖሩ ይገኛሉ። አስቸጋሪነት የሆነ የአኗኗር ዘይቤን፣ የደነዘዘ ዓይነት የሕይወት ዘይቤ እንመርጣለን። የእኛን ሕይወት ሙሉ እንድትሆን የሚያደርጉ፣ ነገር ግን ልባችንን ባዶ የሚያደርጉ ነገሮችን እንሻለን። ወንድሞቼ እና እህቶቼ በጣም ቀለል ያለ ሕይወት ለመኖር እንምረጥ፣ በዝምታ እና በጸሎት እንኑር፣ እውነተኛ ሰብዓዊ እርሾ በመሆን ለመኖር እንሞክር። ከነገሮች ይልቅ ሰዎችን እንምረጥ፣ ምናባዊ ከሆኑ ነገሮች ይልቅ የፊት ለፊት ግንኙነቶችን እናዳብር። በአካባቢያችን የሚታወቀውን የህይወት ሽታ ለመለማመድ እንምረጥ። በሕጻንነቴ ቤት በነበርኩበት ወቅት አንድ እንጀራ/ዳቦ ከጠረጴዛው ላይ ቢወድቅ፣ አንስተነው ስምነው እንድንበላ ወላጆቻችን አስተምረውናል። በእየለቱ በሕወታችን የሚገጥሙንን እንዲህ ዓይነት ትናንሽ ገጠመኞች ዋጋ እንስጣቸው፣ ተጠቅመን መጣል ሳይሆን የሚኖርብን ማድነቅ እና ለእነርሱም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።

የእለት እንጀራችንን የሚለው ቃል ኢየሱስ ራሱ መሆኑን በፍጹም መዘንጋት አይኖርብንም። ያለ ኢየሱስ ምንም ነገር ለማደርግ አንችልም (ዩሐንስ 155) ጤናማ ለሆነ ኑሮ የእኛ መደበኛ ምግብ ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ኢየሱስን እንደ አንድ ከምግብ ጎን እንደ ተቀመጠ ትንሽዬ ምግብ አድርገን እንመለከተዋለን። ግን እርሱ የእኛ የዕለት እንጀራ ካልሆነ እያንዳንዱ እስትንፋሳችን እያንዳንዱ ቀናችን  ሁሉም ነገር ዋጋ የለውም፣ ሁሉም ነገር ሁለተኛ ነገር ይሆናል ማለት ነው። በእየለቱ ለእለት እንጀራ በምንጸልይበት ወቅት ራሳችንን በማሳሰብ አባታችንን ቀለል ያለ ሕይወት፣ በአከባቢያችን ለሚገኙ ነገሮች ሁሉ እንክብካቤ ማድረግ እንድንችል፣ ሁሉም ነገሮቻችን በፊት መምጣት የሚኖርበት ኢየሱስ መሆን እንደ ሚገባው ማወቅ እንድንችል እንዲረዳን ልንጠይቀው ይገባል።

ይቅርታ ይርታ ማድረግ በጣም ቀላል የሆነ ነገር አይደልም። ሁልጊዜም የመራራነት ስሜት ወይም ቅሬታ እናሰማለን፣ እናም ይቅር የምንላቸው ሰዎች ቢያሳዝኑንም እንደ ገና ይቅር ማለታችን በጣም ያናድደን ይሆናል። ነገር ግን ጌታ እኛ ይቅርታችንን በስጦታ መልክ ለሌልቾ እንድንሰጥ የፈልጋል። አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት ትርጉሙን በሚገባ ማብራራት የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። እንዲሁ በቀላሉለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፣ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና; እናንተ ግን ይቅር ባትሉ የእናንተምን ኃጢኣት የሰማዩ አባታችሁ ይቅር አይልላችሁም” (ማቴ 614-15) ጌታ የሰጠው ማብራሪያ ይህ ብቻ ነው። ይቅርታ የአባታችን ሆይ ጸሎት ቁልፍ ሐረግ ነው። እግዚአብሔር ከኃጢያታችን ሁሉ ያነጻናል፣ እግዚአብሔር ሁሉንም እስከመጨረሻ ይቅር ይላል፣ እሱ ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የሚጠይቀን፣ እኛ ይቅር ካላልን እርሱም ፈጽሞ ይቅር አይለንም። እያንዳንዳችን ወንድሞቻችን ለፈጸሙብን ኃጢኣት በአጠቃላይ ስለማነኛውም ስህተት ይቀርታ ማድረግ ይኖርብናል። ልባችንን በጥልቀት በመመልከት፣ ይቅርታ እንዳናደርግ የሚከለክሉን ነገሮች ካሉ ሊፈነቀሉ የሚገባቸው ይቅርታ እንዳንደርግ የሚከለክሉን ነገሮች ካሉ ፈንቅለን ወይም ነቅለን ማውጣት ይጠበቅብናል። ከእዚያም በኃላ አባታችንን አይህ አይደል? ይህንን ድንጋይ ለአንተ እስረክባለሁ፣ ለእዚያ ሰው እጸልያለሁ፣ ለፈጸመው ነገር ይቅርታ ማድረግ ቢያቅጠኝም እንኳን ይቅር ማለት እንድችል ጥንካረሬውን እንድተሰጠኝ እለምናለሁ ማለት ይኖርብናል።

ይቅርታ ያድሳል፣ ይቅርታ ተዐምር ይሰራል። ሐዋሪያው ጴጥሮስ ከኢየሱስ ይቅርታ ካገኘ በኃላ የመንጋው ጠባቂ ለመሆን ችሉዋል። ሳውል እስጢፋኖስ ይቅርታን ካደርገለት በኃላ ጳውሎስ ሆነ። አባታችን ይቅር እንዳለን፣ ሁላችንም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ስንወድ ወደ አዲስ ፍጥረት እንለወጣለን። ከእዚያን በኃላ ብቻ ነው ለዓለም መልካም ዜና ማሰማት የምንችለው፣ ምክንያቱ ከይቅርታ የበለጠ የተሻለ መልካም ዜና የለምና፡ የእዚህ ዓይነቱ ይቅርታ ክፉ የሆነውን ነገር ወደ መልካም ይቀይረዋል። ይህንንም በክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ተመልክተነዋል። እርስ በእርሳችን ይቅር በመባባል፣ ወንድሞችና እህቶች መሆናችንን ረስተን ለምዕተ አመታት በፈጸምነው አለመግባባቶች እና ግጭቶችን በመፍታት ይቅር በምንባባልበት ወቅት ይህ ነገር እዴት የሚያስደስት ነገር ነው፣ ምነኛስ መልካም ነው! እግዚኣብሔርም መንፈሱን ይሰጠናል። የሌሎችን ሥራ እንዳናደንቅፍ እና ልባችንን እንዳናደነድን ቀጣይነት ባለው መልኩ ያቅርታ ማድረግ እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንጠይቀው የገባል። ይልቁኑ በመጀመርያ ደረጃ በጸሎት፣ በወንድማማች ግንኙነት፣ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ተግባርዊ ግንኙነት እንጀምር። በእዚህ መልኩ ሁላችንም በማይለካ መልኩ እንደ ሚወደን እንደ አባታችን እንሆናለን ማለት ነው። በእዚህም መልኩ የአንድነት መንፈስን ለሁሉም እናዳርሳለን።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.