2018-06-21 09:14:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ፡ እግዚኣብሔር ገዢ ሳይሆን አባት ነው።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ፡ እግዚኣብሔር ገዢ ሳይሆን አባት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህ መሰረት በሰኔ 13/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የእግዚኣብሔርን ቃል ኪዳን በሕይወታችን በመተግበር ለመኖር የሚያስችሉንን 10 ቃላት ዙሪያ ያተኮረ አስተምህሮ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በሰኔ 13/3010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

 

በእለቱ የተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል፡

“ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም። 6እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን፤ ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ ነጻነት አለ” (1ቆሮ. 3፡ 5-6, 17)።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እለት በእግዚኣብሔር ትዕዛዛት ላይ መሰረቱን ያደርገ አንድ አዲስ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መጀመራችን ያታወሳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እዚህ ምድር የመጣወ ሕግን ለመሻር ሳይሆን ሕግን ተፈጻሚ ለማድረግ መምጣቱን ተመልክተናል። ይህንን አመለካከት በተሻለ መልኩ መረዳት ይኖርብናል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ትዕዛዛት ለራሳቸው የሚኖሩ አይደለም፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ያለው የቃል ኪዳን ዝምድና አካል ናቸው። በኦሪት ዘጸዐት መጽሐፍ ውስጥ በምዕራፍ 20 1 ላይእግዚአብሔር እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረበማለት ይጀምራል።

እንዲሁ ቀለል ባለ ሁኔታ የተጀመረ ይመስል ይሆናል። ነገር ግን ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልእነዚህ ትዕዛዛትብሎ ሳይሆን የጀመረውእነዚህን ቃሎችበማለት ነበር። የአይሁድ ባህል እነዚህን ቃላት "አሥሩ ቃላት" በማለት ይገልጻቸዋል። እነዚህ “"አሥሩ ቃላት" በእዚሁ መልክ ተገልጸዋል። ነገር ግን እነርሱ የህግ መሰረት አላቸው፣ ግባቸውም ትዕዛዝ ነው። ለእዚህም ነው ታዲያ የእዚህ መጽሐፍ ጸሐፊአሥሩ ቃላት" የሚለውን ቃል እንጂዐስርቱ ትዕዛዛትየሚለውን ቃል ያልተጠቀመው በእዚሁ ምክንያት ነው።

በአንድ ትእዛዝ እና በአንድ ቃል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ትዕዛዝ ተገናኝቶ መደራደር የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። ቃል ግን ከእዚህ በተለየ መልኩ የሚቀመጥ ነገር ሲሆን ተገናኝቶ መወያየትን ያሳያል። እግዚኣብሔር አባታችን በቃሉ አማካይነት ይፈጥራል፣ የእርሱ ቃል የነበረው ልጁ ሥጋ እንዲለብስ አድርጉዋል። ፍቅር በቃላት ይገለጻል፣ በእዚህም መልኩ ያስተምራል መተባበርን ይፈጥራል። ፍቅር የሌላቸው ሁለት ሰዎች እርስ በርስ መግባባት አይችሉም። አንድ ሰው ለልባችን ሲናገር ብቸኝነታችን በእዚያው ያበቃል።

ሌላው ትዕዛዝ መቀበል ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ከእኛ ጋር ለመነጋገር የሚመክር ይሆናል።አንድ ውይይት ተገናኝቶ ስለ አንድ እውነታ ከማውራት በላይ የሆነ ነገር ነው። እርስ በርስ በሚዋደዱ ሰዎች መካከል በቃላት እርስ በርስ በሚነጋገሩበት ወቅት ደስታና ተግባራዊ የሆነ ደግነቱ የተረጋገጠ ነው። ይህ መላክምነት የተገኘው ነገሮችን ባካተተ መልኩ ሳይሆን፣ ነገር ግን እርስ በርስ በሚነጋገሩ ሰዎች መካከል የሚፈጠር በጎነት ነው።

ከመጀመሪያው ጊዜ አንስቶ ፈታኙ ወንዶችንና ሴቶችን በዚህ ነጥብ ላይ ለማታለል ይፈልጋል: እግዚኣብሔር መልካሙን እና ክፉን ነገር ለይቶ ማወቅ ከሚያስችለው የዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ እንደ ከለከላቸው በመገለጽ  እርሱ ያንን ፍሬ እንዲበሉ ለማታለል እና በእርሱ ቁጥጥር ሥር ሊያደርጋቸው ሞክሩዋል። እዚህ ጋር ነው እንግዲህ የሰው ልጅ ተግዳሮት፡ በመጀመሪያ እግዚኣብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ሕግ የሚከለክል እና በኃይል የሚያግድ ስርዓት ነው ወይስ ልጆቹን እንደ ሚንከባከብ እና እራሳቸውን በራሳቸው ከማጥፋት የሚያድናቸው የአንድ አባት እንክብካቤ ነው? እጅግ የሚያሳዝነው ነገር እባቡ ሔዋንን ካታለላት ውሸቶች መካከል  በምቀኝነት ላይ የተመረኮዘ መልኮታዊ ነገር እንደ ምታገኝ እና ሁሉንም ነገሮች ለይታ ማወቅ እንደ ምትችል ያሳስባታል። የእባቡ ሁኔታ ውሸት መሆኑን የሚያረጋግጡ ውሸቶች ናቸው።

የሰው ልጅ አምላክ ነገሮችን በእኔ ላይ በአስገዳጅነት ይጭናል ወይ? ወይም ደግሞ አምላክ እኔን ይንከባከባል? በሚሉት ሁለት አጣብቂኝ ውስጥ ይገኛል። የእርሱ ትእዛዛት ህግ ብቻ ናቸው ወይስ ቅላትን አቅፈው የያዙ ናቸው? እግዚኣብሔር ባለቤት ነው ወይስ አባት ነው? እኛ ተገዢዎች ነን ወይስ ልጆቹ ነን? ይህ ውስጣዊም እና ውጫዊ የሆነ ውጊያ ያለማቋረጥ በውስጣችን ይከሰታል፡ ባሪያ ነን ወይም ደግሞ ልጆቹ ነን ከሚለው መካከል መምረጥ ይኖርብናል።

መንፍስ ቅዱስ የልጁ የኢየሱስ መንፈስ ነው። የባርነት መንፈስ ሕጉን በተጨባጭ መንገድ ብቻ ሊቀበለው ይችላል፡ ሁለት ተቃራኒ ውጤቶችንም ሊያመጣ ይችላል ይህም ማለት በኃላፊነቶች እና ግዴታዎች የተሞላ ህይወት ወይም በአመፅ  እና በተቃውሞ የተሞላ ሕይወት። የክርስትና ሕይወት ማለት በሕግ ከተሞላ ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ  ወደ ተሞላ ሕይወት መሻገር ማለት ነው። ኢየሱስ የአብ ቃል ነው እንጂ የአብ ቅጣት አይደለም። አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ይህን አንቀፅ ሲኖሩ ወይም ሲተላለፍ ይታያል። አንድ ክርስቲያን እንደ አንድ ልጅ ወይም እንደ ባሪያ መሆን አለመሆኑን ሰዎች ይገነዘባሉ። የእኛ አስተማሪዎች እኛን እንደ ሚንከባከቡ ወይም ደግሞ በእኛ ላይ ሕጎችን ብቻ የሚጭኑ መሆን አለመሆናቸውን ለመረዳት እንችላለን። ለዓለም የሚያስፈልገው ሕጋዊነት ብቻ ሳይሆን ጥንቃቄ ጭምር ነው። በልጅነት መንፈስ የተሞላ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች በዓለማችን ውስጥ ያስፈልጋሉ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.