2018-06-21 15:41:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ፡ ማንኛውም ለሐይማኖት ሕብረት የሚደረግ እንቅስቃሴ በመንፈስ ቅዱስ ሊታገዝ ይገባዋል።


ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ፡ ማንኛውም ለሐይማኖት ሕብረት የሚደረግ እንቅስቃሴ በመንፈስ ቅዱስ ሊታገዝ ይገባዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከሲውዘርላድ ፌደራላዊ መንግሥት ርዕሰ ቢሔር ከሆኑት አቶ አሊየን ቤርሴት ጋር ከነበራቸው ቆይታ በመቀጠል ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ሕንጻን መጎብኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱም ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ዶክተር ኦላቪ ፋይኬስ ቴቬት ደማቅ አቀባበል ለቅዱስነታቸው ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በእዚያም ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ዝግጅቱ በጸሎት ከተጀመረ በኃላ ቅዱስነታቸው በሲውዘርላንድ የመጀመሪያውን ንግግር አድርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የብያተ ክርስቲያናት ኅበረት ምክር ቤት በጸጋጀው ጸሎት ላይ ያደርጉት ንግግር ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋዝባለን።

የተወዳዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

አሁን በተነበበልን የሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ገላቲያ ሰዎች (5፡16፣25) በጻፈው መልእክቱ  ውስጥ በገላቲያ ሕዝቦች መካከል መከፋፈል እና ጠብ ጠፈጥሮ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። በቡድን እርስ በርስ እየተፋጠጡ እና እየተካሰሱ ነበር። ይህ ጥል እና ፍጥጫ ባለበት ወቅት ነበር ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “በመንፈስ ተመላለሱ” በማለት ለሕዝቡ የጻፈው።

መመላለስ። እኛ የሰው ልጆች ቀጥይነት ባለው መልኩ በእንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን። በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ወደ ፊት እንድንራመድ ተጠርተናል፡ ከእናታችን ማሕጸን ጀምሮ በእያንዳንዱ የሕይወት ደረጃ ውስት ሳይቀር ከቤታችን ውስጥ በመውጣት ይሁን ከእዚህ ምድር እስከ ምንለይበት ቀን ደረስ በጉዞ ላይ እንገኛለን። የመራመድ ወይም የመመላለስ ዘይቤ የህይወታችንን እውነተኛ ትርጉም ያሳያል፣ ሕይወታችን ሙሉ እንዳልሆነ እና ነገር ግን ሕይወታችን ምልኣት እንድታገኝ የሚያስችላትን ታላቅ ኃይል በመፈለግ እናጓዘለን እንመላለሳለንም። ልባችን መራመዳችንን እንድንቀጥል እና ግብ ላይ ለመድረስ እንችል ዘንድ እንድንነሳሳ ያደርገናል።

መራመድ ስረዓት አለው ጥረት ይጠይቃል። መራመድ በእየለቱ  ትዕግስት እና አካልዊ  እንቅስቃሴን ይጠይቃል። ወደ ግብ የሚመራንን መመንገድ ለመምርጥ እንችል ዘንድ ሌሎች በርካት መንገዶችን ማለፍ ይኖርብናል። ከመንገድ ተሳተን እንዳንወጣ ግባችንን በቀጣይነት ከፊት ለፊታችን በማስቀምጥ መጓዝ ይኖርብናል። ወደ ፊት መራመድ አንዳንድ ጊዜ ወደ ኃላ ለመመለስ ትሕትና እንዲኖረን ያስፈልጋል። ወደ ፊት መጓዝ አብረውን ለሚጓዙ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባን ያሳስበናል፣ ምክንያቱም አብረን ስንጓዝ ብቻ ነው ውጤታማ ልንሆን የምንችለው። በቃላት አብረን ወደ ፊት መጓዝ እንችል ዘንድ ቀጣይነት ባለው መልኩ ንግግር ማድረግ ያስፈልጋል። ለእዚህም ነው በጣም ብዙ ሰዎች እነዚህን ነገሮች አሻፈረኝ በማለት እንቢ የሚሉት በእዚሁ ምክንያት ነው። በእዚህም ምክንያት የጉዞ ውጣ ውረድ ሳይጋፈጡ ሁኔታዎቻቸውን ለማስተዳደር ቀላል በሆነበት ቤታቸው ውስጥ ለመቆየት ይመርጣሉ። ነገር ግን ያ ልባችን የሚናፍቅበትን ሰላምና ደስታ መስጠት የማይችል ለጊዜው ዋስትና መቀበል ነው። ያ ደስታና ሰላም የሚገኘው ከራሳችን ብቻ በመውጣት ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ጊዜ አንስቶ እንድናደርግ የጠራን ይህንኑ ነው። አብርሃም ሀገሩን ትቶ እንዲሄድ የተደረገው በእግዚአብሄር ላይ ብቻ ባለው መተማመንን ታጥቆ ነበር። በተመሳሳይ መልኩ ሙሴ፣ ጴጥሮስ እና ጳውሎስ እና ሁሉ የጌታ ጓደኞች የነበሩ በሙሉ ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ ፊት የተጓዙት በጌታ በመተማመን ብቻ ነው። በእዚህ ረገድ ኢየሱስ ራሱ መልካም የሚባል አብነት አሳይቶናል። እርሱ ራሱ እኔ መንገድ ነኝ ብሎናል (ዩሐንስ 14፡6)። መልኮታዊ የሆነ ባሕሪይ በመተው ዝቅ ብሎ ወደ እኛ በመምጣት በመካከላችን ተጉዙዋል። ጌታችን እና አስተማሪያችን የእኛ ጠባቂ እና እንድግዳ ሆነ። ወደ አባቱም ሲመለስ መንፈሱን ሰጥቶን እኛም ወደ እርሱ እንድንጓዝ ጥንካሬን ሰጠን። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “በመንፈስ ተመላለሱ” ይለናል።

“በመንፈስ ተመላለሱ”። እኛ የሰው ልጆች ያለማቋረጥ እየተንቀሳቀስን ከሆንን፣ እናም ልባችንን ለሌላ ሰው በምንዘጋበት ወቅት የተጣለብንን ተልዕኮ እንረሳለን በእዚህ ረገድ ይህ ጉዳይ ለእኛ ክርስቲያኖች የበለጠ እንድናስብበት ያድርገናል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደ ሚለን የክርስቲያን ሕይወት የማያወላዳ ውሳኔ ከማድረግ ጋር በከፍተኛ መልኩ ይያያዛል። በጥምቀትያችን በተከፈተው መንገድ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መመላለስ እንችላለን አለበለዚያም "የሥጋን ምኞቶች ማርካት" ከሁለቱ መምረጥ ይኖርብናል። ይህ የመጨረሻው አባባል ምን ማለት ነው? ይህም ማለት ይህንን ጉዳይ ተፈጻሚነት እንዲኖረ የምናደርገው ንብረት በመሰብሰብ፣ በራስ ወዳድነት መንፈስ እዚሁ ጸንትን ለመኖር መፈለግ፣ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ እዚሁ ማከናወን የሚለውን ያስተጋባል። እራሳችንን በጸጥታ እግዚአብሄር ወደ ሚመራን ስፍራ እንድንጓዝ ከማድረግ ይልቅ፣ የእራሳችን መንገድ እንጓዛለን። ይህ መንገድ አስገራሚ በሆነ መንገድ መጥፋቱን መመልከት ደግሞ በራሱ በጣም ያሳዝናል። ለቁሳዊ ነገሮች ያለን ጥማት ለጎሬቤቶቻችን ያለንን ምልከታ በማንሸዋረር በዛሬው ጎዳናዎች ላይ የሚታይ የግድዬለሽነት ስሜት ይፈጥራል። በስሜቶቻችን መመራርት ለቁሳቁሶች ጥማት እንዲኖረን በማድረግ በውስጣችን ያለውን የእግዚኣብሔር ድምጽ ቀስ በቀስ እንዳይሰማ ያደርጋል። ሌሎች ሰዎች በተለይም እንደ ሕፃና እና አዛውንት ያሉቱ በራሳቸው መራመድ ላይ መራመድ የማይችሉ ከዚያ መንገድ ውጪ ይሆናሉ። ፍጥረታት ፍላጎታችንን ከማሟላት ሌላ ምንም ዓላማ እንደ ሌላቸው አድርገን እንቆጥራለን።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ የሐዋርያው ጳውሎስ ቃላት ይሞግተናል። በመንፈስ መመላለስ ማለት ዓለማዊነትን ማስወገድ ማለት ነው። ይህ ማለት አመለካከትን መቀየር እና ምሕረትን  መስፋፋትን መምረጥ ማለት ነው። ይህም ማለት በታሪክ ውስጥ የእኛን ድርሻ መጫወት ማለት ሲሆን እኛ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እኛ በሙስና አውሎ ነፋስ ውስጥ እንዳንወሰድ "ጎረቤትን እንደ እራስህ ውደድ" የሚለውን ምልዕክት በረጋ መንፈስ እያሳድግን መሄድ ይኖርብናል። የመንፈስ ቅዱስን መንገድ “ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ በጎነት፣ ደግነት፣ እምነት፣ ርኃርኄ እና ራስን መቆጣጠር” የተሰኙትን የቅዱስ ጳውሎስ  ወሳኝ መንገዶችን ለይተን እንድናውቅ ይረዳናል።

በዚህ መንገድ ላይ ለመጓዝ ተጠርተናል። ይህ ደግሞ ቋሚ የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ የሚፈልግ እና መንፈስ ቅዱስ አስተሳሰባችንን ለማደስ እንዲችል የግል አስተሳሰባችንን ማሳደስ ይጠይቃል። በታሪክ ውስጥ በክርስቲያኖች መካከል ያሉ ክፍፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ ይፈጠራሉ ምክንያቱም በኑሮዎቻችን ውስጥ እና በማህበረሰቦች ውስጥ ዓለማዊ አስተሳሰብ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዘልቆ በመግባቱ የተነሳ ነው። በመጀመሪያ ከክርስቶስ ይልቅ ትኩረት ለራሳችን ሰጥተናል። ይህ ነገር አንዴ ከተፈጠረ የእግዚአብሔርና የሰው ጠላቶች እኛን ለመለያየት ከፍተኛ ችግር አይገጥማቸውም ማለት ነው፣ ምክንያቱም የምንጓዝበት አቅጣጫ የስጋ ነው እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ባለመሆኑ የተነሳ። ቀደም ሲል እነዚያን ልዩነቶች ለማስወገድ ሙከራዎች ተደርገው የነበሩ ቢሆንም በአለማዊ አስተሳሰቦ ች የተሙሉ በመሆናቸው የተንሳ እነዚያ ሙከራዎች ሊሳኩ አልቻሉም። ሆኖም ግን የአለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መድረክ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ሕበረት እንዲኖር በማድረግ ላይ ይገኛል። ሕበርት የምናካሂደው የክርስትሶን ሐሳብ በመከተል ነው፣ ይህ ህብረት ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደገ ሊሄድ የሚችለው በክርስቶስ መንፈስ ስንመራ ብቻ ነው።

የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች  አንድነት እና ሰላም እንዲሰፍን አንደ አንድ መንፈሳዊ ነጋዲ ሰው በመሆን ወደ እናንተ መጥቻለሁ። ተመሳሳይ መነገድ ላይ በመጓዝ ላይ ያላችሁ ወንድሞችን እና እህቶችን እዚህ በማግኜቴ የተነሳ እግዚኣብሔርን ለማመስገን እፈልጋለሁ። ለእኛ ለክርስቲያኖች አብረን መጓዝ የራሳችን አቋም ለማጠናከር አይደለም፣ ነገር ግን ለጌታ ለመታዘዝ እና ለዓለማችን ያለን ፍቅር ለመግለጽ ነው። መንፈስን ቅዱስ በሚያሳየን መንገድ ላይ በብቃት መጓዝ እንችል ዘንድ የእግዚኣብሔርን እርዳታ እንጠይቅ። የክርስቶስ መስቀል በመንገዳችን ይምራን፣  ምክንያቱም በመስቀል አማካይነት ኢየሱስ የጥል ግድግዳን አፈራርሱዋል፣ የጠላትነት መንፈስ ተደምስሱዋል። በውድቀታችንም ቢሆን እናኳን ምንም ነገር ከእርሱ ፍቅር እንደ ማይለየን እናምናለን። 

 

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ቀደም ሲል ያሰማናችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የብያተ ክርስቲያናት ኅበረት ምክር ቤት በጸጋጀው ጸሎት ላይ ያደርጉት ንግግር ሙሉ ይዘቱን ነበር፣ አብራችሁን በመሆን ስለተከትተለችሁን ከልብ ኣናመስገናለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.