Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም 23ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሲውዘርላንድ ማቅናታቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም 23ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሲውዘርላንድ ማቅናታቸው ተገለጸ። - AP

21/06/2018 15:46

ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም 23ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ  ወደ ሲውዘርላንድ ማቅናታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም 23ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ላይ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ታውቁዋል። እንደ ሚታወቀው ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው በማሪያም ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በአውሮፓ አህጉር በትልቅነቱ እና በጥንታዊነቱ በሚታወቀው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ በመባል በሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ በመባል የምታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ስር በመገኘት በትላንትናው እለት ይህ ሐዋሪያዊ ጉዞዋቸው የተሳክ ይሆን ዘንድ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ጥበቃ እንዳይለያቸው የመማጸኛ ጸሎት ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በአሁኑ ወቅት በሲውዘርላን በሰኔ 14/2010 ዓ.ም እየተከበረ በሚገኘው ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት 70ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ለመገኘት ወደ እዚያው ማቅናታቸው የሚታወቅ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላናትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ካደርጉት ሳምንታዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ለምዕመናኑ ባስተላላፉት መልእክት እንደ ገለጹት ይህ ቅዱስነታቸው በሲውዘርላድ የሚያደርጉት 23ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኚት የተሳክ ይሆን ዘንድ ምዕመኑ በጸሎት እንዲያስባቸው ጥሪ ማድረጋቸው ያታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም በሲውዘርላድ ያደርጉት ጉብኚት ከብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ እና ከቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ 2ኛ በመቀጠል በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተደረገ 3ኛው ሀዋሪያዊ ጉብኚት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1969 ዓ.ም በ50ኛ ዓመት ዓለማቀፍ የሰራተኞች የቀን የምስረታ በዓል ላይ መሳተፋቸው እና ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2004 ዓ.ም በእዚያው ተገኝተው ሐዋሪያዊ ጉብኚት ማድረጋቸው ያታወሳል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በመቀጠል የሲውዘርላንድ ዋና ከተማ በሆነችው በጄኔቫ የሚገኘውን የጄኔቫ ሀገረ ስብከት አጠቃላይ ሁኔታ እናስቃኛችኃለን። በጄኔቫ ሀገረ ስብከት የተቋቋመው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1821 ዓ.ም ሲሆን ነገር ግን በአጎራባች ክልል ከሚገኘው ከፊርበርግ ሀገረ ስብከት ጋር በመዋሃደ በአዲስ መልክ እንደ አዎርፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1924 ዓ.ም በአዲስ መልክ መመስረቱ ያታወቃል። ይህ የጄኔቫ ሀገረ ስብከት 5,566 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው እና 1.720,000 ነዋሪዎች የሚገኙበት እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ አጠቃላይ ነዋሪዎች ውስጥ 624,921 የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን እንደ ሆኑ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን 250 አብያተ ክርስቲያናት፣ 264 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 25 ቋሚ ዲያቆናት፣ 5 የዐብይ ዘረዓ ክህነት ተማሪዎች፣ 280 የተለያዩ መንፈሳዊ  ማኅበራት የወንዶች ገዳማት፣ 529 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የሴቶች ገዳማት፣ 22 በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ የትምህርት መስጫ ተቋማት፣ 9 በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ የርዳታ መስጫ ተቋማት፣ ባለፈው ዓመት ብቻ ደግሞ 3,184 ሰዎች ምስጢረ ጥምቀትን መቀበላቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰኔ 14/2010 ዓ.ም ጥዋት ላይ በኢትዮጲያ የቀን አቆጣጠር ከጥዋቱ 3 ሰዓት ገደማ በሮም ከተማ ከሚገኘው በሊዮናርዶ ዳቪንቺ ስም ከሚጠራው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው ወደ ዚውዘርላንድ በረራ ጀምረው እንደ ነበረ ከስፍራው ከደረሰን ዜን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን 700 ኪሎ ሜትሮችን በአየር ላይ አቆራርጠው የአንድ ሰዓት ከ40 ደቂቃ ጉዞ አድርገው በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 5፡10 ላይ በሲውዘርላንድ ዋና ከተማ በጂኔቫ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ መድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚያም የሀገሪቷ ፈዴራላዊ መንግሥት ርዕሰ ብሔር የሆኑት አቶ አሊየን ቤርሴት ደማቅ የሆነ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በመቀጠል ከሲውዘርላድ ፌደራላዊ መንግሥት ርዕሰ ቢሔር ከሆኑት አቶ አሊየን ቤርሴት ጋር ለተወሱኑ ደቂቃዎች ያህል የግል ቆይታ ማድረጋቸው እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝግ መነጋገራቸው ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ቅዱስነታቸው ከሲውዘርላድ ፌደራላዊ መንግሥት ርዕሰ ቢሔር ከሆኑት አቶ አሊየን ቤርሴት ጋር ከነበራቸው ቆይታ በመቀጠል ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ሕንጻን መጎብኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱም ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤቱ ውና ጸሐፊ የሆኑት ዶክተር ኦላቪ ፋይኬስ ቴቬት ደማቅ አቀባበል ለቅዱስነታቸው ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በእዚያም ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚሰራው የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ዝግጅቱ በጸሎት ከተጀመረ በኃላ ቅዱስነታቸው በሲውዘርላንድ የመጀመሪያውን ንግግር አድርገዋል።

 

21/06/2018 15:46