2018-06-18 16:10:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየመን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየመን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሰራት ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ቅዱስነታቸው በሰኔ 03/2010 ዓ.ም ለዓለም ያስተላላፉት ሳምንታዊ መልእክት. . .

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ ካደርጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ደንግል ማሪያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነው፣ ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ የሚደገመው የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን እንዳበሰራት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሰለመሆኑ በሚዘክረው የገብርኤል ብሥራት ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት  በአሁኑ ወቅት በየመን በአዲስ መልክ በተቀሰቀሰው ግጭት እና ጦርነት ምክንያት በጣም ብዙ የሚባሉ ሰዎች በከፍተኛ ስቃይ ወስጥ እንደ ሚገኙ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው የዓለማቀፉ ማኅበርሰብ ይህንን ግጭት ለማስወገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እንዲደርግ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል።

ከጦርነት ተጠቃሚ የሚሆን ማንም ሰው እንደ ሌለ በማውሳት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለው የሰዎች ስቃይ ይቀረፍ ዘንድ ባለድርሻ አካለት የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንደ ሚጠበቅባቸው ጥሪ ያቀርቡት ቅዱስነታቸው ሁላችንም በየመን ሰላም ይስፍን ዘንድ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጸሎት ማድረግ እንደ ሚገባ ጨምረው ገለጸዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.