2018-06-16 11:17:00

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ስድብ የወደፊት ሕይወትን ይገድላልና ከቅናት ወደ ጓደኝነት መሻገር ያስፈልጋል”


ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ስድብ የወደፊት ሕይወትን ይገድላልና ከቅናት ወደ ጓደኝነት መሻገር ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የተናገሩት በሰኔ 07/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “ስድብ የሰውን መሰረታዊ መብት ይገፋል፣ ኢየሱስ እርቅ እንድናወርድ ይጠይቀናል፣ “ስድብ የማንሳደብ ከሆነ ሌሎች ሰዎች እንዲያድጉ መንገድ እንከፍታለን ብለዋል።

በቅናት ስሜት ተነሳስተን ስድብ በምንሳደብበት ወቅት ሌሎች ሰዎችን እንደ መግደል ይቆጠራል፣ ሊከበር እና በፍጹም ሊገረሰስ የማይገባው የሰው ልጅ መብትን እንደ መርገጥ ይቆጠራል፣ በእዚህም ድርጊታችን መጪውን ጊዜ ተስፋ እንደ መግደል ይቆጠራል።

ኢየሱስ ከእኛ የሚጠብቀው ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት እርቅ እንድናደርግ እና የሌላውን እና የእኛን ሰብዓዊ መብት እንድናከብር እንደ ሚጠይቀን በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5፡20-26 ላይ ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ፍትህ ማድረግ እንደ ሚገባን፣ ሌሎችን መሳደብ መልካም ነገር ባለመሆኑ እና ፍርድ ልያስፍርድብን የሚችል ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑ የተነሳ እርቅ መፍጠር መልካም እንደ ሆነ በገለጸበት የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መስረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ወደ ፍርድ ሳትሄድ በፊት ከባለአንጣህ ጋር እርቅ ፍጠር

“የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ለአሳሪ አሳልፎ እንዳይሰጥህ፣ በወህኒም እንዳትጣል፣ በመንገድ ላይ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ” በማለት ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ ተናግሮ እንደ ነበር በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የሰው ልጅ ጥበብ፡ ከመልካም ፍርድ ይልቅ ግድፈት ያለው ስምምነት ይሻላል” ብሎ እንደ ሚያምን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱነታቸው ኢየሱስ ፍቅርን እና ለወንድሞቻችን ልናሳየው የሚገባውን ርኅራኄን በተመለከተ ያስተማራቸውን አስተምህሮ በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ  በዕለታዊ ኑሮዋችን የምናደርጋቸውን ተግባራት በምሳሌነት በመጠቀም እና ከእዚያም ባሻገር በመሄድ ስድብን የተመለክቱ ችግሮችን ስያብራራ እናገኘዋለን ብለዋል።

“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል” (ማቴ 5፡21-22) የሚለውን በመጥቀስ ምን አልባትም እነዚህ ስድቦች ኢየሱስ በነበረበት ወቅት የነበሩ ጥንታዊ ስድቦች ሊሆኑ ይችል ይሆናል በማለት ፈገግታ በተቀላቀለበት መልኩ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ጌታ እንደ ሚለው ስድብ ከተሳደብን በኃላ እዚያው የሚያበቃ ጉዳይ ሳይሆን ነገር ግን በተቃራኒው ሌላ አዲስ መዘዝ ይዞ እንደ ሚመጣ ገልጸው ይህም ሰዎችን ከመግደል የተናነሰ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

ምክንያቱም አሉ ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለመግለጽ በማሰብ ምክንያቱም ስድብ ሰዎችን የመግደል የመጀመሪያ ደረጃ እንደ ሆነ ገለጸው ይህም ሌሎች ሰዎችን በማሳጣት መከበር ያለበትን ሰብዓዊ መብታቸውን በመግፈፍ፣ ሰውን በማግለል ማኅበረሰብን ጭምር የሚገድል ተግባር ነው ብለዋል።

“እኛ የስድብ ውርጅብኝ የተቀላቀለ አየር መተንፈስ ተለማምደናል” በማለት ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ በሥራ መግቢያ እና ከሥራ መውጫ ሰዓት አከባቢ በትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ ብዙ የስድብ ናዳ እንደ ሚወርድ የገለጹት ቅዱስነታቸው ሰዎች ስድቦችን እየፈጠሩ እና እያሻሻሉ ስድብን ስድብ በማይመስል መልኩ በማቅረብ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት እየገፈፍን በምንገኝበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ያሉት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነት ስድቦችን ለመስማት ጆሮዎቻችንን መክፈት አይገባንም ብለዋል።

ስድብ በጣም አደገኛ የሆነ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ብዙን ጊዜ ስድብ የሚመነጨው ከፍተኛ ከሆነ ቅናት መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ አካላዊ ወይም አእምሮኣዊ እክል ያለው ሰው በእኛ ላይ ስጋት የሚፈጥር ባለመሆኑ የተንሳ እርሱን የመሳደብ ፍላጎት እንደ ማያድርብን ገለጸው ይህንን ሐሳባቸውን ለመጽናት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ነገር ግን አንድ የአካል፣ የአእምሮ፣ የማኅበራዊ፣ የቤተሰብ እክል ያለው ሰው ወይም ከማኅበርሰቡ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር የማይችል እንከን ያለው ሰው የማልወደውን ነገር በእኔ ላይ በሚፈጽምበት ወቅት “ጉዳተኛ” ብዬ ቀለል አድርጌ በመሳደብ አልፈው ይሆናል. . .በእዚህም ምክንያት ሰውየውን እና የወደፊት ተስፋውን እንደ መገደል ይቆጠራል፣ የሰው ልጆችን የሕይወት ሂደ ማኮላሸት ይሆናል። በሩን የሚከፈተው ቅናት ነው፣ ምክንያቱም አንድ ሰው እኔን የሚያስፈራራኝ ነገር ካለው ወይም ከእኔ የሚበልጥ ነገር ካለው፣ ምቀኝነት እርሱን እንድሳደብ ያደርገኛል። በእዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ምቀኝነት ሁሌም ይኖራል።

መጽሐፈ ጥበብ “በሰይጣን ቅናት ምክንያት ሞት ወደ ዓለም ውስጥ እንደ ገባ እንደ ሚገልጽ” ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህም መስረት ቅናት ሞትን እንደ ሚያመጣ ገልጸው “እኔ በማንም ሰው ላይ አልቀናም” ብለን በምንናገርበት ወቅት በደንብ ማስብ ይኖርብናል ምክንያቱ ያ ቅናት በውስጣችን ተደብቆ ይገኛል፣ ቅናት በውስጣችን ተደብቆ ከቆየ ደግሞ በጣም አደገኛ ወይም ኃይለኛ እንድንሆን ያደረገናል መልካችን እንዲለወጥ በማድረግ የተቀላቀለ ስሜት በውስጣችን በመፍጠር ስድብ እንድንሳደብ ያነሳሳናል ፣ በእዚህም ተግባራችን ሌልውን ሰው እናስከፋለን ብለዋል።

ኢየስሱ የእዚህን ዓይነት ተግባር እንደ ማይቀበለው እና አስፈላጊ ያልሆነ ተግባር በመሆኑ የተነሳ ማስወገድ እንደ ሚገባን እንደ ሚያሳስበን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጸሎት በምታድርግበት ወቅት ወይም ደግሞ መስዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ በምንሄድበት ወቅት የበደልነው ሰው እንዳለ ካስታወስን ጸሎታችንን ባለበት ቦታ በመተው በቅድሚያ ከወንድሞቻችን ጋር እርቅ መፍጠር እንደ ሚገባን ኢየሱስ እንደ ሚያሳስበን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ይህንን ሐስባቸውን ለማጽናት በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

ኢየሱስ በጣም ሥር-ነቀል ለውጥ እንድናደርግ ይጠይቀናል። እርቅን ማውረድ መልካም የሚባል የአኗኗር ባህሪያት አይደለም፣ በፍጹም! ስር ነቀል የሆነ ለውጥ በማድረግ  የሌላውን ሰው እና የራሴንም ክብር ለማስከበር የሚፈልግ አመለካከት ማሳደር ማለት ነው። ከስድብ ወደ እርቅ፣ ከከፍተኛ ቅናት ወደ ጓደኝነት መሻገር ማለት ነው። ኢየሱስ ዛሬ የሚያሳየን መንገድ ይህ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.