2018-06-14 17:23:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ወጣቶች ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል” ማለታቸው ተገለጹ።


ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ወጣቶች ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል” ማለታቸው ተገለጹ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህ መሰረት በሰኔ 06/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የእግዚኣብሔር ሕግ-ጋት ትዕዛዛት ላይ መስረቱን ያደርገ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መሆኑን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ወጣቶች ወዲህ ወዲያ እያሉ ከሚዋዢቁ ይልቅ ጤናማ መቃተት ቢኖራቸው ይሻላል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በሰኔ 06/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የፓዶቫው የቅዱስ አንጦኒዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ይከበራል። ከእናንተ መካከል አንጦኒዮስ ተብሎ የሚጠራ ሰው አለ ወይ? እስቲ አንጦኒዮስ ለሚባሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ጊዜ እናጨብጭብላቸው። በዛሬው ዕለት ትዕዛዛትን በተመለከተ አዲስ ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማድረግ እንጀምራለን። የእግዚኣብሔር ሕግ-ጋት ትዕዛዛት። ይህንን በሚገባ ለማብራራት አሁን ሲነበበብ በሰማነው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን ኢየሱስ ከአንድ ሰው ጋር መገናኘቱን የሚገልጸውን ቅዱስ ወንጌል ማስታወስ ያስፈልጋል-ይህም አንድ ወጣት የሆነ ሰው የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል በማለት በኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ተንበርክኮ መጠይቁን የሚገልጽ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ነው (ማርቆስ 10፡17-21)። እናም በዚያ ጥያቄ ውስጥ የእያንዳንዳችንን ሕልውና፣ ማለትም የእኛን ጨምሮ ማለት ነው የዘላለም ሕይወትን እና ሙሉ የሆነ ሕይወት ለማግኘት ያለንን ምኞት እናገኛለን። ታዲያ ወደ እዚያ እንዴት ነው ለመድረስ የምንችለው? የትኛውን መንገድ ነው መከተል የሚኖርብን? እውነተኛ የሆነ ኑሮ ለመኖር፣ ጥሩ የሆነ ኑሮ ለመኖር . . . ብዙ ወጣቶች "ለመኖር" ይሞክራሉ፣ ከዚያ በኋላ ጊዜያዊ የሆኑ ነገሮችን እና ተግባሮችን በመከተል ይጠፋሉ።

አንዳንዶች ይሄንን ሁኔታ ማጥፋት ይፈልጋሉ - የመኖር ተስፋ ስለሌለ፣ በሕይወት መኖር አደገኛ ስለሆነ ይህንን ለማጥፋት ይፈልጋሉ። በተለይም ለወጣቶች እንዲህ ማለት እፈልጋለሁ: -የእኛ ከፍተኛ ጠላት ተጨባጭ የሆኑ ችግሮቻችን፣ ከባድ እና ድራማዊ በሆነ መልኩ የሚያጋጥሙን ችግሮቻችን አይደሉም፣ በሕይወታችን ውስጥ የከፋው ጠላታችን እና ሕይወታችንን ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚከታት ነገር ትህትና የዋሕነት የሌለበት ነገር ግን በእኩይ ተግባራት የተሞላ እና በግብታዊነት ስሜት መኖር ነው። ዛሬ መልካም የማይባል ወጣት የወደፊቱ ወጣት አይደለም ወይ? እዚያው ባለበት ይቆያል,፣ አያድግም፣ ስኬታማ አይሆንም። መኩራት ወይም በሐፍረት መሞላት። የእዚህ ዓይንት ወጣቶች ብዙ ዓይነት ፍርሃቶች አሉባቸው፡ “በፍጹም እኔ እንዲህ ዓይነት ሰው አይደለሁም. . .የእዚህ ዓይነት ወጣቶች በፍጹም ወደ ፊት መራመድ አይችሉም።  ትህትና እና ኃይል የላቸውም፣ ዓይነ አፋር የሆነ እና ብዙ ችሎታ የሌለው ወጣት ወደ ፊት መራመድ አይችልም።  ወጣት የነበረው ብጹዕ ፒዬር ጆርጆ የሚባል ሰው እንዲህ ይል ነበር “መኖር እንጂ ማኗኗር አይኖርብንም” ይል ነበር። ኃይል የሌለው ሰው አኗኗሪ ሆኖ ይቀራል። ሕይወታችን በምትሰጠን ኃይል ታግዘን መኖር ይኖርብናል። ሰማያዊ የሆነው አባታችን በአሁኑ ዘመን ለሚኖሩ ወጣጦች ጤናማ የሆነ መቃተት ይኖራቸው ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጣቸው መጠየቅ ያስፈልጋል። ነገር ግን በቤት ውስጥ፣ በእየቤታችን፣ በእየቤተሰባችን ውስጥ ሳይቀር  አንድ ወጣት ቀኑን ሙሉ ተቀምጦ በሚውልበት ወቅት ምን አልባት አባቱ ወይም እናቱ “ይህ ወጣት ታሙዋል፣ ወይም የሆነ ነገር ገጥሞታል፣ ብለው በማሰብ ወደ ሕክምና መስጫ ተቋም ይወስዱታል። የወጣቶች ሕይወት ሊሆን የሚገባው ግን ወደ ፊት መጓዝ፣ የተረጋጋ መሆን፣ ጤናማ የሆነ መቃተት እንዲኖረን ማድረግ፣ ውበት በማይሰጥ ሕይወት ውስጥ ገብቶ አለመደሰት፣ ቀለማት የሌሉበት ሕይወት ውስጥ መኖር የለበትም። ወጣቶች እውነተኛ የሆነ ሕይወት ካልተራቡ እስቲ ልጠይቃችሁ፣ ሰብዓዊነታችን የት ጠፋ? ሰብዓዊነት ጸጥ ያሉ እና ግድየለሽ የሆኑ ወጣቶችን ይዞ የት መድረስ ይችላል?

አሁን ስነበብልን በነበረው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ወጣት ታሪክ በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ ይታያል፣ ሕይወታችን እንዴት ነው የምንኖረው፣ የተትረፈረፈ ሕይወት፣ በደስታ የተሞላ ሕይወት ነው ወይ እየኖርነው የምንገኘው? ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “ሁሉንም ትዕዛዛትን በደንብ ጠንቅቀህ ታውቃቸዋለህ” በማለት ዐስርቱን ትዕዛዛት አመላከተ። እሱ ወደ አንድ የተወሰነ ቦታ ሊመራው የሚፈልግበት የትምህርት አሰጣት ዘዴ ነበር ኢየሱስ የተከተለው፣ በእርግጥ ይህ ወጣት የነበረው ሰው ከጥያቄው ለመረዳት እንደ ሚቻለው ይህ ሰው ምልኣት ያለው ሕይወት እየኖረ እንዳልሆነ ያሳያል፣ ከእዚህ የተሻለ ምልኣት ያለው ሕይወት እየፈለገ እንደ ሚገኝ ያሳውቃል። ታዲያ ሊረዳው የሚገባው ጉዳይ ምንድነው? “መምሕር ሆይ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እኮ ከልጅነቴ ጀምሬ በደንብ ጠብቄኣቸዋለሁ” በማለት መለሰ።

ከወጣትነት ወደ ጉልማሳነት እንዴት መሻገር ይቻላል? ከወጣትነ ወደ ጎላማሳነት የምንሸጋገረው የእኛን ውስንነት መቀበል ስንጀምር ነው። የጎደለን ነገር ምን መሆኑን በንጽጽር በማየት ስንገነዘብ ወደ አዋቂነት እንሻገራለን። ይህ ሰው "ማድረግ" የሚችለውን ነገር ሁሉ ለማወቅ ፈለገ፣ ያደርገው ነገር ሁሉ "ከጣራ" ("ጣሪያ") ያልበለጠ መሆኑን ለመገንዘብ ይገደዳል፣ ከመጠን በላይ መሄድ አይችልምና።

ወንዶችንና ሴቶችን ማየቱ እንዴት ደስ ይላል! የእኛ ሕልውና ምን ያህል ውድ እንደ ሆነ ይሳያልና! በታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ ሊቅበለው ያልቻለው አንድ እውነታ አለ፣ ይህም የሰው ልጅ ገደብ እንዳለው አለማወቁ ነው።

በዛሬው ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ “ሕግንና የነቢያትን ቃል ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ለመፈጸም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” (ማቴ. 5፡17) በማለት የተናግረው ቃል እኛን ሊረዳን የሚችል ቃል ነው። ጌታ ኢየሱስ ለመፈፀም መቱዋል፣ ለዚህም ነው የመጣው። ያ ሰው በተናጥል መድረክ ላይ መወጣት ነበረበት፣ ይህም ማለት ራሱን፣ የእራሱ ስራን፣ የራሱን ንብረት እና - ህይወቱ ሙሉ - ጌታን ለመከተል ማንኛውንም ነገር መተው ማለት ነው። በጣም ጥልቅ እና አስገራሚ በሆነው  በኢየሱስ የመጨረሻ ጥሪ ውስጥ ድኽነትን የሚያመለክት ሳይሆን ነገር ግን እውነተኛ የሆነ ሕብትን የሚያመልክት ጥሪ መመልከት ደስ ይላል። ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሽጥ፤ ለድኾችም ስጥ፤ በሰማይ የተከማቸ ሀብት ታገኛለህ፤ ከዚያ በኋላ ና፤ ተከተለኝም” አለው።

ከእውነተኛው እና ቀቅጅ መካከል መምረጥ የሚችል አንድ ሰው ቅጂውን ይመርጣል ወይ? ይህ ነው እንግዲህ የእኛ ተግዳሮት፣ እውነተኛው እና ቅጂውን ለይቶ ማወቅ። ኢየሱስን ሊተካ የሚችል ምንም ነገር የለም፣ እርሱ ተተኪ የሌለውን እውነተኛ ህይወት፣ እውነተኛ ፍቅር፣ እውነተኛ ሃብት ይሰጣል! እኛ እውነተኛ የሆነውን ሐብት ስንመርጥ ያላዩ ወጣቶች፣ ታዲያ እንዴት ነው እኛን ሊከተሉ የሚችሉት? ለግማሽ መለኪያዎች ሱሰኛ መሆናችንን የተመለከቱ ወጣቶች እኛን እንዴት ሊከተሉን ይችላሉ? መጠናቸውን የሚያውቁ ክርስቲያኖችን ማግኘት ከባድ ነው፣ “ድንክ” የሚለውን ቃል እንድጠቀም ፍቀዱልኝ፣ እስከ ተወሰን ደረጃ የሚያድጉ፣ ነገር ግን ከእዚያን በኃላ ማደግ የሚያቆም ክርስቲያኖች አሉ። የተከፋፈለ እና የተዘጋ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች አሉ። የእዚህ ዓይነቱ ገጠመኝ በጣም መጥፎ የሆነ ገጠመኝ ነው። ከእዚህ ውስጥ ወጥቼ ወደ ሌላ ሕይወት እንድጓዝ የሚረዳኝ መልካም አብነት የሚያሳየኝ ሰው ያስፈልገኛል፣ ትንሽ እንዳድግ የሚረዳኝ ሰው ያስፈልጋል።

የጎደለውን መንገድ ኢየሱስ ይሞላዋል። ሕግንና የነቢያትን ቃል ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ለመፈጸም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” ብሉዋልና "የጠፉትን" ለመመለስ ከእውነታው መጀመር አለብን። ተራ የሆነውን ነገር በማስወገድ ለላቁ ነገሮች ልባችን ልንከፍት ያስፈልጋል።

በእነዚህ የትምሕርተ ክርስቶስ ክፍል ውስጥ የኢየሱስን እጅ ይዘው፣ ከትንሽነት ወደ ህይወት ወደ ሰማይ ካለው ውድ ሀብት ለመጓዝ፣ ኢየሱስ ያስተማረንን እና ሙሴ የሰጠን ትዕዛዛት ይዘን መጓዝ ይኖርብናል። እነዚህን ጥናታዊ እና በጥበብ የተሞሉ ሕግጋትን በማሰብ ሰማያዊ አባታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የከፈተልንን አዲስ ሰማይ በመመልከት ወደ እውነተኛ ሕይወት እንዲመራን ሊንጠይቀው የገባል የእርሱ ሕይወት የእግዚኣብሔር ልጆች ሕይወት ነውናን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.