2018-06-08 15:47:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “የምሕረት ተግባራት ኢየሱስ ያስተማረን የፍቅር መንገድ ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “የምሕረት ተግባራት ኢየሱስ ያስተማረን የፍቅር መንገድ ናቸው” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ማለትም በሰኔ 01/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እግዚኣብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ገደብ የለሽ ፍቅር እንደ ሆነ ገለጸው የእግዚኣብሔር ታላቅነት የሚለካው ራሱን ዝቅ በማድረጉ እና ለእኛ ባለው ርኅራኄ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ሆነ ገለጸው ፍቅርን በተመለከተ ክርስቶስ ከእኛ ታላላቅ የሚባሉ ተገባሮችን ሳይሆን የሚጠብቀው ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሆን በእየ ዕለቱ በምናደርጋቸው ትናንሽ ተጨባጭ በሆነ መንገድ መተግበር እንዳለብን ይጠይቀናል ብለዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር የላቲን ስረዓተ አምልኮ በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በዛሬው ቀን ማለትም በሰኔ 01/2010 ዓ.ም የልበ ኢየሱስ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ያደርጉት አስተንትኖ በእዚሁ በልበ ኢየሱስ በዓል ላይ ተኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

አስቀድሞ የሚወደን እግዚኣብሔር ነው!

“እግዚኣብሔርን አስቀድመን የምንወደው እኛ አይደለንም፣ ነገር ግን አስቀድሞ የሚወደን እግዚኣብሔር ራሱ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነብያት እግዚኣብሔር አስቀድሞ እኛን መውደዱን በተመለከተ በሚገባ ለመግለጽ በማሰብ በጸደይ ወራት ከሁሉም አበቦች አስቀድሞ የሚያብበው የኦቾሎኒ አበባ እንደ ሆነ በመግለጽ ይህንን ተምሳሌታዊ በሆነ አኳሃን በመጠቀም በተመሳሳይ መልኩ ሁል ጊዜም ቢሆን እኛን አስቀድሞ የሚወደን እግዚኣብሔር መሆኑን፣ ቀድሞ የሚጠብቀን፣ ቀድሞ የሚወደን፣ ቀድሞ የሚጠብቀን  እግዚኣብሔር ነው እንጂ እኛ አይደለንም በማለት ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የእግዚኣብሔር ፍቅር ገደብ የለሽ ነው

“ነገር ግን የእግዚኣብሔርን ፍቅር በደንብ መረዳት ቀላል የሆነ ነገር አይደለም፣ ዛሬ በቀዳሚነት ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በምዕራፍ 3፡8-12, 14-19 ላይ ሲነበብ እንደ ሰማነው “የማይመረመረው የክርስቶስን ባለጠግነት” በማለት የእግዚኣብሔርን ፍቅር ተመራምረን የምንደርስበት ነገር እንዳልሆነ ያሳየናል” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ይህንን ፍቅር ለመረዳት ባጣም ያዳግታል። የክርስቶስ ፍቅር ከሕሊናችን በላይ የሆነ ፍቅር ነው። ከሁሉም በላይ ነው። የእግዚኣብሔር ፍቅር እንዲህ በጣም ታላቅ የሆነ ፍቅር ነው። አንድ ገጣም ይህንን የእግዚኣብሔር ፍቅር በተመለከተ ሲናገርዳርቻው እና ጥልቀቱ የማይታወቅ ውቂያኖስን ይመስላልበማለት ገልጾት ነበር። ይህንን ዓይነቱን ፍቅር ነው ታዲያ እኛ መረዳት እና መቀበል የሚገባን።

 

የእግዚኣብሔር የማስተማር ዘዴ

በደኽንነት ታሪክ ውስጥ እግዚኣብሔር የእርሱን ፍቅር ገልጾልን እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ይህንን የእርሱን ፍቅር በታሪክ ውስጥ ቀስ በቀስ በመገለጹ የተነሳ “ታላቅ የሆነ አስተማሪ” መሆኑን አስመስክሩዋል ያሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ በቀዳሚነት ከትንቢተ ሆሴ ከምዕራፍ 11፡1-9 ላይ ተወስዶ በተነበበው የእለቱ የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ተመርኩዘው  ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር የነበረውን ፍቅር የገለጸው በኃይል እንዳልሆነ ገልጸው “ሕዝቤን እጁን ይዤ፣ እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤ እንከባከባቸውም ነበር” በማለት እንደ እግዚኣብሔር ተናግሮ እነ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

እግዚኣብሔር ፍቅሩን የሚገልጸው እንዴት ነው? በታላልቅ ነገሮች አማካይነት ነው ወይ? በፍጹም አይደለም! እግዚኣብሔር ፍቅሩን የሚገልጸው ራሱን በትንሽ በማድረግ ነው፣ ራሱን በማሳነስ፣ በርኅራኄ እና በመልካም ተግባሩ ነው ፍቅሩን የሚገልጸው። እኛን ይቀርበናል። በእዚህ ቅረበት እና በእዚህ ትህትና እርሱ ለእኛ ያለውን ታላቅ የሆነ ፍቅር እንድንረዳ ያደርገናል። ታላቅነቱን የምንረዳው በትንሽነቱ ነው።

እግዚኣብሔር ታላቅነቱን የሚገለጸው ትንሽ በመሆን ነው።

እግዚኣብሔር ልጁን ወደ እኛ መላኩን፣ የላከውም የሰውን ሥጋ እንዲለብስ አድርጎ እንደ ሆነ፣ ልጁም ራሱን በትህትና እስከ ሞት ድረስ ዝቅ አድርጎ እንደ ነበረ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ የእግዚኣብሔር ምስጢራዊ ፍቅር መገለጫ እንደ ሆነ ጠቅሰው ታላቅነቱን የሚያሳይ ታላቅነት በትህትናው ተገልጹዋል ካሉ በኃላ የአንድ ክርስቲያን አካሄድ በእዚሁ መልክ ሊገለጽ ይገባዋል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

ኢየሱስ የአንድ ክርስቲያን ባሕሪይ ምን መሆን እንዳለበት ባስተማረን ወቅት የተናገረው በጣም ጥቂት የሚባሉ ቃላትን ብቻ ነበር፣ ይህንንም ያደርገው እኛ ሁላችን የምንዳኝበትን መመዘኛ ብቻ በመጥቀስ ነበር። ታዲያ ይህንን በተመለከተ ምን አለ? “እግዚኣብሔር እንዲህ ነው ብየ አስባለሁ። የእግዚኣብሔርን ፍቅር ተረድቻለሁበፍጹም አላለም። በፍጹም! የእግዚኣብሔርን ፍቅር ራሴን ዝቅ በማድረግ ገልጫለሁኝ። ለተራበው ምግብን፣ ለተጠማው መጠጥን፣ ለታረዘው ልብስን፣ የታስረውን በመጎብኘት። እነዚህ ኢየሱስ ያስተማረን የምሕረት ተግባራት የእግዚአብሔር ፍቅር በዘላቂነት የሚያስተምሩን የፍቅር መንገድ ናቸው።

ስለ ፍቅር ማውራት ሳይሆን የምኖርብን ነገር ግን ተጨባጭ በሆነ መንገድ ስለፍቅር መግለጽ ይንሮብናል።

ስለፍቅር ታላላቅ የሆኑ ሐሳቦችን እና ታሪኮችን በማንሳት ማውራት በራሱ ብዙ ፋይዳ እንደ ሌለው በመጥቀስ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ኢየሱስ ባሳየን ትህትና በመታገዝ ትናንሽ በሚባሉ፣ ነገር ግን ተጨባጭ በሆነ መልኩ ፍቅርን በተግባር መገለጽ የምንችል ሰዎች ልንሆን እንደ ሚገባን ገልጸው በእየለቱ የምናደርጋቸው የምሕረት ተግባራት፣ ትህትናን እንድንላበስ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የክርስቶስን ፍቅር እንድንኖር በማድረግ በቅድሚያ ለእኛ በመቀጠል ደግሞ ለሌሎች ይህንን የክርስቶስ ፍቅር ማዳረስ እንችላለን ካሉ በኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.