2018-06-07 07:57:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “አንድ የታመመ ሰው እና አንድ የሚጠገን ማሽን አንድ አይደሉም”።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “አንድ የታመመ ሰው እና አንድ የሚጠገን ማሽን አንድ አይደሉም”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳለፍነው ሳምንት ከዓለማቀፍ የካቶሊክ የሕክምና ባለሙያ ማኅበር ፈዴሬሽን ተወካዮች ጋር በቫቲካን በሚገኘው በቅሌሜንጦስ የስብሰባ አዳራሽ ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት እንደ ገለጹት ለወንድማማችነት ፍቅር እና ለወንጌላዊነት ርህራሄ ምስክር እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የአንድ ክርስቲያን ምስክርነት የሚጀምረው "በሰዎች መካከል አንድነትን በፈጠር ሊሆን እንደ ሚገባ” በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም አንድነትን የመፍጠር ተግባር በእምነት መንፈስ በመሞላት መተግበር ይኖርበታል ብለዋል።

ከዓለማቀፍ የካቶሊክ የሕክምና ባለሙያ ማኅበር ፈዴሬሽን አባላት በቅርቡ 25ኛ አመት የምስረታ በዓላቸውን በማስመልከት ከባለፈው ረቡዕ ከግንቦት 22/2010 ዓ.ም- እስከ ግንቦት 25/2010 ዓ.ም ድረስ “ሕይወት ቅዱስ የሆነ ነገር ነው” በሚል መሪ ቃል ጉባሄ ማድረጋቸውንም ለመረዳት ተችሉዋል።

የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሕክምና ባለሙያ መሆን ማለት ቀጣይነት ባለው መልኩ የቅዱስ ወንጌል እሴቶች በመከተል መንፈሳዊ የሕነጻ ትምህርቶችን መውሰድ፣ ማራላዊ እና በተጨማሪም የስነ-ሕይወት ስነ-ምግባር መላበስ እንደ ሚኖርባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው  በተለይም ደግም በሕክምና ባለሙያ እና በአንድ የሕክምና ርዳታ ፈላጊ መካከል ያለው ግንኙነት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ እንደ ሆነ ጠቅሰው አንድ የሕክምና ባለሙያ ልክ እንደ አንድ የወንጌል ልዑክ በመሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕዝቦች የጤንነት ሁኔታ ለማሻሻል የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንደ ሚገባ ቅድስነታቸው አክለው ገለጸዋል።

“ቤተ ክርስቲያን ለሕይወት ጥብቅና ትቆማለች፣ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ሕይወትን የሚጻረሩ ነገሮች ቤተክርስቲያን የሚያሳስባት ነገር ነው፣ በተለይም ደግሞ ደካም እና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ነብሶችን እንዳያድጉ ወይም እንዳይፈጥሩ የሚያደርጉ ተግባራትን መዋጋት” እንደ ሚገባቸው ገልጸው የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሕክምና ባለሙያ መሆን ማለት የሕክምና ሙያችሁን እምነታችሁን በተመረኮዘ መልኩ ማከናወን እና ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሕብረት በመፍጠር ሙያዊ ክህሎቶቻችሁን እና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን  በማዳበር ተግባራችሁን በእዚሁ አግባብ ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

ግልጽ እና ድፍረትን በተላበሰ መልኩ ሙያዊ አገልግሎታችሁን መስጠት ይኖርባችኃል ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ከጽንስ እስከ ተፈጥሮኣዊ ሞት ድረስ ያለውን የሰው ልጆችን ነብስ መጠበቅ እንደ ሚገባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ደካማ እና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ በጽንስ ደረጃ የሚገኙ ነብሶችን መጠበቅ ክርስቲያናዊ የሆነ ግዴታ ነው ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.