2018-06-07 15:36:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “ተፈጥሮ ስጦታ እንጂ ርስት አይደለም” ማለታቸው ተገለጸ።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “ተፈጥሮ ስጦታ እንጂ ርስት አይደለም” ማለታቸው ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት በግሪክ ዋና ከተማ በአቴንስ የአከባቢ ጥበቃን በተመለከተ ሲፖዚዬም በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በስፍራው የቅድስት መንበርን በመወከል የተገኙት በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፒተር ተርክሰን መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ካርዲናል ፒተር ተርክሰን በስፍራዉ በመገኘት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ለሆኑት ፓትሪያርክ ቤርቴሌሜዎስ ቀዳማዊ የተላከውን የጽሑፍ መልእክት ለተሳታፊዎች ማንበባቸው የተገለጸ ሲሆን “ተፈጥሮ ለሰው ልጆች ከእግዚኣብሔር የሰጠ ስጦታ ነው እንጂ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚጠቀሙበት ርስት አይደልም” ማለታቸውም የተገለጸ ሲሆን ለተፈጥሮ ጥበቃ ማድረግ እንደ ሚገባ እና በተለይም ደግሞ ለጥቃት ተገላጭ የሆኑትን ፍጥረታት መንከባከብ እንደ ሚገባ ገልጹዋል።

ድንቅ እና ውብ የሆነ ባሕር በአሁኑ ወቅት “የወንዶች፣ የሴቶች እና የሕጻናት የቀብር ስፍራ እየሆነ መምጣቱን” በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህ በአሁኑ ወቅት በግሪክ ዋና ከተማ በአቴንስ “ምድራችንን እና በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን እንከባከብ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ዓለማቀፍ ሲፖዚዬም ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ በርካት ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ባልፉት ጊዜያት በግሪክ ሌስቮስ በመባል በሚታወቀው ስፍራ ተገኝተው በእዚያ የሚገኘውን የስደተኞች የመኖሪያ ስፍራ መመልከታቸውን በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በወቅቱ በእዚያ መገኘታቸው የስድተኞችን ወቅታዊ የሆነ ሁኔታ በአካል በመመልከት ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች እየኖሩት የሚገኘውን ነባራዊ ሁኔታ መመልከታቸውን በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “በእዚያ የሚገኘው ውብ የሆነ ባሕር በየሀገራቸው በተፈጠረ አስገዳጅ ሁኔታ የተነሳ የሚሰደዱ ሰዎች በሚገጥሙዋቸው የባሕር ላይ አደጋ የተነሳ የወንዶች፣ የሴቶች እና የልጆች የቀብር ስፍራ መሆኑን ሳስብ ግን በጣም ያሳዝነኛል” ነው ብለዋል።

ነገር ግን መልካም ባሕል ሰብዓዊ እሴቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚነጸባረቁበት ክርስቲያን የሆነ የግሪክ ማሕበርሰብ ምንም እንኳን ሀገራቸው በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ቢሆንም ቅሉ ያላቸውን ኃይል እና ጉልበት በመጠቀም በተቻላቸው መጠን በተለያዩ አስገዳጅ ሁኔታዎች የተነሳ ተሰደው የሚመጡ ሰዎችን ካላቸው በማክፈል መቀበላቸው በጣም ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ጉዳይ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በዓለማችን ላይ በአሁኑ ወቅት በከፍተኝ ሁኔታ እየታየ ያለውን የአከባቢ ብክለት በተመለከተ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እያንዳንዳችን አእምሮዋችንን በመመርመር በአሁኑ ወቅት በአከባቢያችን ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ከፍተኛ ውድመት ከግምት በማስገባት ለመጭው ትውልድ ተገቢ እና ጽዱ የሆነ መልካ ምድር ማስረከብ የምንችልበትን ሁኔታ ከአሁኑ ማመቻቸት እንደ ሚገባም ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገለጸዋል።

ከእኛ በኃላ እየመጡ ላሉ ታዳጊ ሕጻናት የምናወርሳቸው ምን ዓይነት ምድረ ነው? በማለት በመልእክታቸው ጥያቄን ያነሱት ቅዱስነታቸው ምድራችን ለተወስኑ ሰዎች ብቻ በውርስ መልክ የተሰጠች ሀብት ሳይሆን ሁላችንም በጋራ እና በጥንቃቄ እንድንጠቀምበት የተሰጠን የአምልክ ስጦታ በመሆኑ ይተነሳ እያንዳንዱ ሰው የጋራ የሆነችሁን ምድራችንን መንከባከብ ይገባዋል ብለዋል።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጪው መስክረም 1/2018 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጅ ለምድራችን ጸሎት የሚደርግበት ቀን እንደ ሆነ በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚሁ ለምድራችን በሚደረገው ዓለማቀፍ የጸሎት ቀን እርሳቸው እና ፓትሪያርክ በርቴሌሜዎስ በጋራ የሚያስተላፉትን መልእክት እንደ ተዘጋጀ ጠቅሰው “ምድራችንን የመንከባከቡ ተግብር የእያንዳንዱ በጎ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ተግባር መሆን እንደ ሚገባው በሰፊ መገለጻቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የካቶሊክ እምነት ተከታይ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከሆኑ ምዕመናን፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ከመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ከሆኑ የማኅበርሰብ ክፍሎች በጋራ በመሆን፣ በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ሁሉ ጋር በመሆን በምድራችን ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ከፍተኛ በደል በተጠናከረ መልኩ መዋጋት እንደ ሚገባ ጠቅሰው ዘላቂ በሆነ እና በተቀናጄ መልኩ ለምድራችን ጥበቃ ማድረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጳጳሳዊ ምክርበት ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፒተር ተርክሰን በኩል ባስተላአፉት የጽሑፍ መልእክት መገለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.