2018-06-04 16:44:00

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ተገለጸ።


የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 26/2010 ዓ.ም የደኽንነታችን ምንጭ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በትላንትናው እለት በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።

የእዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል ጥንታዊ የሆነ መሰረት ያለው እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ ከሚሰጣቸው መንፈሳዊ በዓላት ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ነው። ይህ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 26/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሆስቲያ በመባል በሚታወቀው ሥፍራ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተገኙበት በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በተከናወነ መስዋዕተ ቅዳሴ እና መስዋዕተ ቅዳሴውን ተከትሎ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ መገለጫ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን በመያዝ የውደት ሥነ-ስረዓት መካሄዱንም ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ በዓል በሮም ከተማ ሆስቲያ በሚባልበት ሥፋራ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1968 ዓ.ም. የዛሬ 50 አመት ገደማ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ጳውሎስ 6ኛ በስፍራው ተገኝተው ካከበሩት በዓል በመቀጠል በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አማካይነት ለሁለተኛ ጊዜ በሆስቲያ የተከበረ በዓል ነው።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በቅድስ ቁርባን ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ይገኛል በማለት በከፍተኛ እምነት የሚከበር በዓል ነው። ይህ በዓል ሥር መሰረቱን ያድርገው በ8ኛው ክፍለ ዘመን በቤልጄም ሀገር ይኖሩ በነበሩ አንድ ገድማዊት የነበራቸው ልዩ እና ምስጢራዊ ከሆነ መንፈሳዊ ተመክሮ ላይ መሰረቱን ያደርገ ሲሆን ቅድስት ጁሊያን ዘ ኮርኒሎን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1208 ዓ.ም ቅዱስ ቁርባንን በመንበሩ ውስጥ ሆኖ በሚመለከቱበት ወቅት በአንድ በኩል የነጭ ጨረቃ ምልክት ሆኖ ሲታያቸው በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ጥላ የሚመስል ነገር በቅዱስ ቁርባን ዙሪያ ይመለከታሉ።

ይህም ተዐምር ቅዱስ ለሆነው ለክርስቶስ ሥጋ እና ደም ለየት ባለ ሁኔታ ልዩ መንፈሳዊ አምልኮ ሊደርግ እንደ ሚገባ በወቅቱ ለቤተ-ክርስቲያን መልእክት ያስተላልፈ ክስተት ሲሆን በወቅቱ በቤልጄየም የነበረው ጳጳስ ለየት ባለ ሁኔታ ለክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ደም መንፈሳዊ አምልኮ የሚደርግበትን ቀን እና ሁኔታ በማመቻቸት የህንን መንፈሳዊ ክብረ በዓል በሀገረ ስብከታቸው ማስተዋወቅ ጀመሩ።

ለክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ለሆነው ደሙ መንፈሳዊ ስግደት እና አምልኮ የሚደርግበት በዓል በቀጥታ በጣሊያን ሀገር በላዚዮ አውራጃ በቪቴርቦ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ቦልሴና በመባል በምትታወቀው ትንሽዬ ከተማ ውስጥ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በታየው የቅዱስ ቁርባን ተዓምር ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ሲሆን በወቅቱ ወደ ሮም ከተማ ንግደት በማድረግ ላይ የነበረ አንድ ካህን በጉዞ ላይ በነበረበት ወቅት መስዋዕተ ቅዳሴን ለማሳረግ በቦልሴና ከተማ በሚገኘው አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን መሰዋት ይጀመራል። በወቅቱ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ሕብስቱን አንስቶ ከባረከ በኃላ በሚቆርስበት ወቅት “በእዚህ ሕብስት ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ይገኛል ወይ? ወይስ አይገኝም?” በሚል አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ መጠራጠር ይጀምራል ካህኑ። በውቅቱ ካህኑ በእዚህ ጥርጣሬ ውስጥ ሆኖ ሕብስቱን በሚቆርስበት ወቅት ወዲያውኑ ከሕብስቱ ውስጥ የደም ጠብታዎች መውጣት ይጀምራሉ፣ መስዋዕተ ቅዳሴ በሚሰዋበት መንበረ ታቦት ላይ የነበረው ጨርቅ ከሕብስቱ በወጣው ደም ይርሳል፣ ከእዚያም አልፎ መንበረ ታቦቱ የተሰራበት ድንጋይ በደም ይርሳል። በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት አርባን 15ኛ እርሳቸው ራሳቸው በልጄማዊ በመሆናቸው ከእዚህ ቀደም በቤልጄይም ሀገር ቅድስት ጁሊያን ዘ ኮርኒሎን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1208 ዓ.ም ቅዱስ ቁርባንን በመንበሩ ውስጥ ሆኖ በሚያመልኩበት ወቅት በአንድ በኩል የነጭ ጨረቃ ምልክት ሆኖ ሲታያቸው በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ጥላ የሚመስል ነገር በቅዱስ ቁርባን ዙሪያ የታየበት ተዐምር በማስታወስ እርሳቸው ራሳቸው ቤልጄሚያዊ በመሆናቸው የተነሳ የእዚህን ተዓምር ታሪክ አሳምረው የሚያቁ በመሆኑ የተነሳ በመላው ዓለም በምትገኘው የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙ መንፈሳዊ አምልኮ የሚደርግበትን ቀን ይፋ በማድረግ በመላው የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያንት ዘንድ ይህ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት እና ሁደት እንዲከበር በማሰብ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1264 ዓ.ም ባወጅቱ አዋጅ መስረት ይህ በዓል የጴጤቆስጤ ወይም በዓለ አምሳ ከተከበርበት ቀን በመቀጠል ባለው ሐሙስ ቀን እንዲከበር ባወጁት መሰረት እነሆ ይህ በዓል በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በእየአመቱ እየተከበረ እየተዘከረ ይገኛል። በእዚህ መስረት ይህ በዓል ባለፈው ሐሙስ ቀን ማለትም በግንቦት 23/2010 ዓ.ም. መከበር የነበረበት ቢሆንም ነገር ግን ሐዋሪያዊ በሆኑ ምክንያቶች የተነሳ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍታንቸስኮ ሐሙስ ቀን የሥራ ቀን በመሆኑ የተነሳ ይህንን ከግምት ባስገባ መልኩ ከሐሙስ ቀን ይልቅ ሰዎች ከሥራ ነጻ በሚሆኑበት በእሁድ ቀን ይህ በዓል እንዲከበር ባልፈው ዓመት በመውሰናቸው የተነሳ ቀደም ሲል እንደ ገለጽነው በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 26/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሆስቲያ በሚባል ስፍራ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእርሳቸው መሪነት በቅድስት ሞኒካ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ በጊዜያዊነት በተሰራ መንበረ ታቦት ላይ በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ በኃላ የክርስቶስን ክቡር እና ቅዱስ የሆነውን ሥጋ የሚገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በመያዝ መንፈስዊ ስግደት እና አምልኮ ከተድረገ በኃላ በጸሎት የታገዘ ሁደት እንደ ተደረገ ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን የክርስቶስ ቅዱስ የሆነ ሥጋው እና ክቡር ለሆነው ደሙ ሐይማኖታዊ ስግደት እና አምልኮ የሚደርግበት ቀን በተመለከ ቀደም ባሉት አመታት እንደ ገለጹት “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ለእኛ እንደሰጠን ሁሉ እኛም ራሳችንን ለሌሎች ቆርሰን እንድንሰጥ ኃይል የሚሰጠን ቅዱስ ቁርባን ነው” ማለታቸው ይታወሳል። በውቅቱ ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለው ነበር . . .”ልጆቻቸውን በሚገባ ለማሳደግ በማሰብ በእየቤታቸው በሚገኘው የምግብ ጠሬጴዛዎች ላይ የሚቆረሱ ዳቦዎችን  ለማግኘት የሚለፉ እና ልባቸውን ቆርሰው የሚሰጡ ስንት እናቶች እና ስንት አባቶች አሉ! እንደ አንድ ኃላፊነት እንደ ሚሰማው ዜጋ የሌሎች ሰዎችን ሰብሐዊ መብት በተለይም ደግሞ የድኾችን፣ የስደተኞችን እና የተገለሉ ሰዎችን መብት ለማስከበር በማሰብ ሕይወታቸውን ቆርሰው የሚሰጡ ስንት ክርስቲያኖች ናቸው!” በማለት በግንቦት 19/2008 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም አመታዊ ከብረ በዓል በተከበረበት ወቅት ባደርጉት ስብከት ላይ መናገራቸው ይታወሳል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.