2018-06-04 16:41:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው”።


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው”።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 26/2010 ዓ.ም የደኽንነታችን ምንጭ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በትላንትናው እለት በታላቅ መንፈሳዊነት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።

ይህ በዓል በግንቦት 26/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሆስቲያ በሚባል ስፍራ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእርሳቸው መሪነት በቅድስት ሞኒካ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ በጊዜያዊነት በተሰራ መንበረ ታቦት ላይ በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ በኃላ የክርስቶስን ክቡር እና ቅዱስ የሆነውን ሥጋ የሚገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በመያዝ መንፈስዊ ስግደት እና አምልኮ ከተድረገ በኃላ በጸሎት  የታገዘ ሁደት እንደ ተድረግ አለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ቅዱስ ቁርባን በመንግሥተ ሰማይ አስቀድመን ቦታ እንድንይዝ የሚረዳን ምስጢር ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 26/2010 ዓ.ም የደኽንነታችን ምንጭ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደሙ የሚዘከርበት መንፈሳዊ በዓል በተከበረበት ወቅት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ያድረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ዛሬ በሰማነው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ማርቆስ 1412-16, 22-26) ስለ መጨረሻው እራት ሲናግር እንደ ነበረ መስማታችን የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ከመጨረሻው እራት ይልቅ በይበልጥ የሚናገረው ስለመጨረሻው እራቱ ዝግጅት ነው። ማዘጋጀትየሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ሰምተናል።  ለምሳሌም ደቀ-መዛሙርቱ ኢየሱስን የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?”(ማርቆስ 1412) በማለት ሲጠይቁት እንሰማለን። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ግልጽ የሆኑ መመሪያዎችን በመስጠት በሰገነቱ ላይ የተሰናዳና የተነጠፈ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል፣ በእዚያም አዘጋጁ (ማርቆስ 1415) በማለት ደቀ- መዛሙርቱን ይልካቸዋል። ደቀ መዛሙርቱ ለመዘጋጀት ሄዱ፣ ነገር ግን ጌታ የራሱን ዝግጅት ቀደም ብሎ አድርጉዋል።

ኢየሱስ ከትንሳኤው በኃላ ለደቀ-መዛሙርቱ ለሦስተኛ ጊዜ በተገለጠበት ወቅት ተመሳሳይ የሆን ነገር ተከስቶ ነበር። እነርሱ ዓሳ በማጥመድ ላይ በነበርቡበት ወቅት ከተገለጠላቸው በኃላ እነርሱ በማጥመድ ላይ እያሉ እነርሱ ግን እንጀራ እና የተጠበሰ ዓሣ አዘግጅቶ በባህር ዳርቻ ላይ ይጠብቃቸው ነበር። እንደዚያም ሆኖ፣ እርሱ እንዴት ዓሳ ማጥመድ እንደ አለባቸው ለደቀ-መዝሙርቱ ካሳያቸው በኃላ ያገኙትን ዓሣ ይዘው በመጡበት ወቅት ካጠመዱት ዓሳ የተወሰኑትን እንዲሰጡት ደቀ-መዛሙርቱን ጠይቆ ነበር (ዩሐንስ 216.9-10) ኢየሱስ ቀድሞውኑ ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸው ነበር፣ እናም ደቀ መዛሙርቱን እንዲተባበሩ ጠይቋል። አሁንም እንደገና የፋሲካ እራት ከመመገባቸው በፊት ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ ይላቸዋል: የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው (. . .) እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ (ዩሐንስ 142.3) ብሎዋቸው ነበር። የሚያዘጋጀው ኢየሱስ ራሱ ነው፣ ነገር ግን ከፋሲካ በዓል በፊት በአስቸኳይ፣ ተግጻጾችን እና ምሳሌያዊ አነጋገሮችን በመጠቀም እንድንዘጋጅ፣ ሁሌም ዝግጁዎች ሆነን እንድንኖር ይጠይቀናል (ማቴዎስ 2444, ሉቃስ 1240)

ስለዚህ ኢየሱስ ለእኛ አዘጋጅቱዋል፣ እኛም እንድንዘጋጅ ይጠይቀናል። ኢየሱስ ለእኛ ምን ያዘጋጅልናል? እርሱ ለእኛ አንድ ቦታና ምግብ ያዘጋጃልናል። ከወንጌሉ ውስጥ ከተጠቀሰው ““በሰገነቱ ላይ የተሰናዳና የተነጠፈ ሰፊ አዳራሽ”  እጅግ የሚልቅ ስፍራ ያዘጋጅልናል። ይህም ቦታ ሰፊ ቦታ ያለው እና በእዚሁ በምድር ላይ  የምትገኘው ቤክርስቲያን የሚወክል ሲሆን በእዚህም ስፍራ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሆን ስፍራ ሊኖር ይገባል። ነገር ግን ከእርሱ ጋር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ለዘለዓለም የምንኖርበትን ስፍራ በላይ በመንግሥተ ሰማይ ላይ አዘጋጅቶልናል። ከቦታው በተጨማሪ እራሱ ይህንን ተቀበሉ ስጋዬ ነውና  (ማርቆስ 1422) በማለት ሥጋውን በዳቦ መልክ ያቀርብልናል። እነዚህ ሁለቱ ስጦታዎች ማለትም የመኖሪያ ስፍራ እና ምግብ ለመኖር የግድ የሚያስፈልጉን ነገሮች ናቸው። የመኖሪያ ስፍራ እና ምግብ በጣም ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ናቸው። የምኖሪያ ስፍራ እና ምግብ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ለእኛ ተሰጥተውናል።

ኢየሱስ በእዚህ ምድር ላይ የመኖሪያ ስፍራ አዘጋጅቶልናል፣ ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን የቤተክርስቲያን የልብ ምት ነውና። ቤተክርስቲያን እንድትወለድ እና ዳግም እንድትወለድ ያደርጋታል፣ ቤተክስቲያንን እንድትሰበሰብ በማድረግ ብርታቱን ያሰጣታል። በተጨማሪም ቅዱስ ቁርባን የሰማይ ምግብ በመሆኑ የተነሳ ለዘለዓለም እንድንኖር በሰማይ ላይ ስፍራን ያዘጋጅልናል። ከሰማይ ስለወረደ በሚድር ዘላለማዊ ሆኖ የሚኖር ብቸኛው ነገር እርሱ ነው። እርሱም ለሚመጣው ጊዜ ሳይቀር እንጄራ ነው፣  አሁንም ቢሆን ተስፋ ልናደርግ ወይም ልንገምተው ከምንችላቸው በላይ እጅግ የላቀውን የወደፊቱን ቅምሻ ይሰጠናል። ከሁሉም የላቀ ሁኔታ በጉጉት የምንጠብቀውን እና ምርጥ ሕልማችንን ይመግበናል። ያም ማለት ቃል በቃል የዘላለም ሕይወት ቃል ኪዳን ነው - በቃ ተስፋ ብቻ ሳይሆን እዚያ ምን እንደሚጠብቀን ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ የሚገልጽልን ነገር ነው። ቅዱስ ቁርባን የሰማያዊው ግብዣ ተቋዳሽ እንድንሆን ያስችለናል፣  ወደ ዘለአለም ህይወት እና ደስታ የምናደርገውን ጉዞ የሚመግበው ኢየሱስ ራሱ ነው።

በተቀደሰው ሕብስት ውስጥ ከመኖሪያ ቦታ ባሻገር ኢየሱስ ለእኛ ምግብ በማዘጋጀት ይመግበናል። በሕይወት ውስጥ ዘወትር ምግብ መመገብ ያስፈልገናል; በተጨማሪም ሕይወት በምግብ ብቻ ሳይሆን በእቅዶች፣ በፍላጎቶች እና በተስፋ ጭምር ልትመገብ ያስፈልጋል። ፍቅርን ተርበናል። በጣም ደስ የሚያሰኝ ሙገሳ፣ ምርጥ ስጦታዎች እና በጣም የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም በአራሱ በቂ አይደሉም፣ ሙሉ በሙሉ እርካታ አያስገኙልንም። ቅዱስ ቁርባን ቀላል የሆነ ምግብ ነው፣ እንደ አንድ እንጄራ ነው፣ ነገር ግን እኛን ሊያጠገበን የሚችል ልዩ የሆነ ምግብ ነው፣ ምክንያቱም ከእዛ የላቀ ታላቅ ፍቅር የለምና። በእዚያ ውስጥ ኢየሱስ እናገኛለን፣ እኛ የእርሱን ሕይወት እንጋራለን እናም የእርሱ ፍቅር ይሰማናል። ከእዚያም የእርሱ ሞትና ትንሳኤ ለእኛ የተደረገ መስዋዕት እንደ ሆነ ለመረዳት እንችላለን። በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ለኢየሱስ ስንሰግድ  ከእሱ መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን ሰላም እና ደስታን እናገኛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ, ይህንን የሕይወት ምግብ እንምረጥ። መስዋዕተ ቅዳሴን መሳተፍ ተቀዳሚ ተግባራችን እናድርግ። በማኅበረሰቦቻችን ውስጥ የቅዱስ ቁርባን ስግደት ወይም አምልኮ እንደገና እንጀምር! ለእኛ ያዘጋጀልንን ነገር ለመቀበል የሚያስቸልንን ምኞት እንዲሰጠን እግዚአብሄርን መራብ የምንችልበት ጸጋ እንዲሰጠን እንጠይቀው። ልክ ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ኢየሱስ እኛም እንድንዘጋጅ ይጠይቀናል። እንደ ደቀመዛሙርቱ "ጌታ ሆይ የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋልህ?" ብለን እንጠይቀው። የት እናዘጋጅ! ኢየሱስ ሌለችን የሚያገል፣ ለተወሱኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን የተመረጠ ቦታ አይፈልግም። እርሱ የሚፈልገው በፍቅር ያልተነኩ ቦታዎችን እና ተሰፋ የሌለባቸውን ስፍራዎች ይሻል። ወደ እነዚያ ለእኛ ደስ የማያሰኙ ቦታዎች በመሄድ በእነዚያ እንድናዘገጅ ይጠይቀናል። ተስማሚ ቤት የሌላቸው ወይም ምግብ የማይመገቡ ሰዎች ስንት ይሆኑ! ሁላችንም በብቸኛነት፣ በመከራ እና በችግር ውስጥ እየኖሩ የሚገኙ ሰዎች ምን ያህል እንደ ሆኑ እናውቃለን። ከኢየሱስ የሞኖሪያ ሥፍራ እና እንጀራ የተቀበልን እኛ ለእነዚህ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቦታ እና ምግብ ማዘጋጀት ይኖርብናል። ኢየሱስ ስለእኛ ሲል የሚቆረሰ እንጀራ ሆነ፣ እኛም በተራችን እራሳችንን ለሌሎች እንድንሰጥ ከራሳችን ይልቅ ለሌላው እንዲኖረን ይፈልጋል። በእዚህ መንገድ "በቅዱስ ቁርባን" ውስጥ እንኖራለ፣ ከጌታ ሥጋ የሚመነጨውን ፍቅር በዓለም ውስጥ በማሰራጨት እና በማስፋፋት እንኖራልን። ቅዱስ ቁርባንን በሕይወታችን ውስጥ ትርጉም ሊያገኝ የሚችለው ከራሳችን ባሻገር በመሄድ ራሳችንን ለሌሎች አገልግሎት ስናውል ብቻ ነው።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል ደቀመዛሙርቱ ምግብ ለማዘጋጀት ወደ ከተማ እንደ ሄዱ ይናገራል (ማርቆስ 14) ጌታ ዛሬ የእርሱን ዳግም መምጣት በምንጠብቀበት በዛሬው ወቅት እኛ ርቀን መጠበቅ ሳይሆን የሚኖርብን ወደ ከተማዎቻችን በመግባት ተዘገጅተን መጠበቅ እንደ ሚገባን  ጥሪ ያደርግልናል። ጌታ ሆይ ምን ያህል በሮችን እንድንከፍትልህ ትፈልጋለህ? ጌታ ሆይ ስንት ግድግዳዎች እንድንደረምስ ትፈልጋልህ? ኢየሱስ የግድዬለሽነት ግድግዳ እንዲደረመስ፣ የጭቆና እና የእብሪት ተግባራት እንዲጠፉ፣ ለፍትህ፣ ለስነ ምግባር እና ለህጋዊነት የተዘጋጁ መነገዶች ላይ እንድንጓዝ  ይፈልጋል። ቅዱስ ቁርባኑ በኢየሱስ የባሕር ምዕበል እንድንወሰድ ይጋብዘናል።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል የተደመደመዉደቀመዛሙርቱ ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡበማለት ነበር። እኛም መስዋዕተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኃላ ወደ ውጪ እንወጣለን፣ በየከተማው መንገድ ላይ ከሚዘዋወረው ከኢየሱስ ጋር ሆነን ወደ ፊት እንጓዛለን። ኢየሱስ በመካከላችን ሊሆን ይፈልጋል። እርሱ የእኛ የሕይወት አካል ሆኖ ለመኖር ይፈልጋል፣ በቤትህ ውስጥ በመግባት ነጻ የሚያወጣን ምሕረቱን በመስጠት በቡራኬ እና በመጽናናት ሕይወትህን ሊሞላው ይፈለግል። በጣም መጥፎ የነበረ የሕይወት ተመክሮ የነበረህ ሰው ከሆንክ ጌታ ሊቀርብህ ይፈልግላል። ልባችንን ለእርሱ በመክፈት እንዲህ እንበል. . .

ጌታ ሆይ መጥተህ ጎብኘን።

ወደ ልባችን፣ ወደ ቤተሰባችን እና ወደ ከተማችን በምትመጣበት ወቅት እንቀበልሃለን።

በመንግሥትህ ውስጥ ምግብ እና የምኖሪያ ስፍራ ስላዘጋጀህልን ከልብ እናመስግንሃለን።

ከእህት እና ከወንድሞቻችን ጋር በመሆን መንገድኽን በማዘገጀት ሂደት ውስጥ ተሳታፊ በመሆን ለሌሎች የወንድማማችነት፣ የፍትህ፣ የሰላም መንገዶችን በየከተሞቻችን ላይ መገንባት እንችል ዘንድ አግዘን። አሜን!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.