2018-05-28 16:11:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “የቅድስት ስላሴ በዓል እግዚኣብሔር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ እና ቀዳሽ፣ በፍቅር የተሞላ” ነው


ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “የቅድስት ስላሴ በዓል እግዚኣብሔር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ እና ቀዳሽ፣ በፍቅር የተሞላ” እንደ ሆነ እንድናሰላስል ይረዳናል ማለታቸው ተገለጸ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያቱ የላከበት የጴራቂሊጦስ በዓል በተከበረ በሳምንቱ የቅድስት ስላሴ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 19/2010 ዓ.ም ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ የቅድስት ስላሴ በዓል በግንቦት 19/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርካታ ቄሳውስት እና ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የቅድስት ስላሴ በዓል እግዚኣብሔር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ እና ቀዳሽ፣ ሁልጊዜ በፍቅር እና ለፍቅር የሚኖር መሆኑን እንድናሰላስል በማድረግ፣ እርሱን ለሚቀበሉ ፍጡራን ሁሉ የእርሱን ውበት፣ በጎነት እና እውነት እንዲያንጸባርቁ እድሉን ይሰጣቸዋል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 19/2010 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ የቅድስት ስላሤ አመታዊ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት ወቅት በእዚያው ለተገኙ ምዕመናን ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁ በመሆን እናድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ

ዛሬ ከጴንጤ ቆስጤ ሰንበት በኋላ ያለውን  የቅድስት ስላሴን በዓል እናከብራለን። ይህ በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት ውስጥ የተገለጸውን አብ፣ ወልድ እና መንፍስ ቅድሱን ሦስት አካላት አንድ የሆኑበትን የእግዚኣብሔር ምስጢር የምናሰላስልበት እና የምናሞግስበት በዓል ነው። ሕይወቱን በነጻ ለእኛ ያቀርብልንና በአለም ውስጥ እንድናስፋፋው የሚጠይቀን ሁልጊዜ አዲስ የሆነውን የእግዚኣብሔር ፍቅር በአድናቆት እና በደስታ የምናከብርበት ቀን ነው።

ዛሬ የተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እግዚአብሔር እንዴት ለእኛ ራሱን የገለጸበት መንገድ እንድንረዳ በማድረግ እርሱ እንዲሁ ዝም ብሎ ያለ ወይም የሚኖር መሆኑን ብቻ እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን፣እርሱ ከእኛ ጋር ለእኛ ቅርብ፣ እኛን የሚወደን፣ ከእኛ ግራ የሚራመድ፣ ትናንሽ ከሚባሉ ሰዎች አንስቶ እስከ ተቸገሩ ሰዎች ድረስ በእኛ ግለሰባዊ በሆነ ታሪክ የሚመሰጥ እና እያንዳንዳችንን የሚንከባከብ አምላክ እንደ ሆነ ያመለክቱናል። እርሱበላይ በሰማይእንዲሁምበታችም በምድር” እግዚአብሔር እርሱ አምላክ መሆኑን ያሳዩናል (ኦሪት ዘዳግም 439) ስለዚህም እኛ የምናምነው አንድ ሩቅ በሆነ አካል አይደለም፣ በፍጹም አይደለም! እኛ የምናምነው አንድ ግድየለሽ በሆነ አንድ አከል አይደለም፣ በፍጹም አይደለም! ነገር ግን በተቃራኒው አጽናኝ ሰማይን እና ሕዝቡን በፍቅር በፈጠረው፣ ስጋን በለበሰው፣ በሞተው እና ከሙታን ለእኛ ሲል በተነሳው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ሁሉንም ነገር ወደ ሙሉነት በለወጠው አምላክ ነው የምናምነው።

ይህንን ፍፁም የሆነ እና የመቀየር ኃይል ያለውን የአምላክ-ፍቅር በሕይወቱ የተለማመደው የመጀመሪያው ሰው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሲሆን (ሮሜ 8:14-17) እግዚኣብሔርአባ፣ አባትተብሎ መጠራት እንደ ሚፈልግ በመግለጽ በእርግጥ እግዚኣብሔር የእኛ አባት ነው፣ ይህንንም ማድረግ የሚገባን ልክ እንደ አንድ ሕጻን ልጅ ሕይወትን በሰጠን ሰው እቅፍ ውስጥ ራሱን በማድረግ ሙሉ በሙሉ በመተማመን በእንደ ሚኖር ሕጻን አድርገን ለእግዚኣብሔር ራሳችንን ማቅረብ የገባናል።

መንፈስ ቅዱስ - ሐዋሪያው ጳውሎስ በድጋሚ ያስታውሰናል መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ገብቶ በመንቀሳቀስ  ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ የራቀ ባሕሪይ ያለው አምላክ ሳይሆን፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በጣም እንደተቀራረበን በእኛ ዘመን እንደነበረ እና በእግዚአብሔር የተወደድን ልጆች በመሆናችን የተነሳ ደስታኞች እንድንሆን ያደርገናል። በእርግጥ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ከሙታን የተነሳው ጌታ በእኛ ጋር ለዘለዓለም እንደ ሚኖር ቃል ገብቶልናል። እርሱ ከእኛ ጋር በመሆኑ እና ለመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምስጋና ይግባውና እርሱ ለእኛ በአደራ የሰጠውን ተልዕኮ በቋሚነት መፈጸም እንችላለን። ታዲያ የተሰጠን ተልዕኮ ምንድነው? ለሁሉም የእርሱን ቅዱስ ወንጌል ማብሰር እና መመስከር ከእሱ ጋር ኅብረትን በመፍጠር ከእርሱ የሚመጣ ደስታ ከሁሉም ጋር መቋደስ ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር በመራመድ በደስታ ይሞላናል፣ ደስታ ደግሞ 'የክርስትና የመጀመሪያ ቋንቋ ነው።

ስለዚህ የቅድስት ስላሴ በዓል እግዚኣብሔር አንድ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ እና ቀዳሽ፣ ሁልጊዜ በፍቅር እና ለፍቅር የሚኖር መሆንን እንድናሰላስል በማድረግ፣ እርሱን ለሚቀበሉ ፍጡራን ሁሉ የእርሱን ውበት፣ በጎነት እና እውነት እንዲያንጸባርቁ እድሉን ይሰጣቸዋል። እርሱ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሁልጊዜ ከሰዎች ጋር ለመጓዝ የመረጠ እና ለሕዝቦች ሁሉ እና ለእያንዳንዱ ሰው በበረከት የተሞላ ሕዝብ ለመፍጠር ፈልጉዋል። ክርስቲያን የሆነ አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች የተገለለ ሰው ሳይሆን፣ እግዚኣብሔር የፈጠራቸው የእግዚኣብሔር ሕዝብ አንድ አካል ነው። የእዚህ ዓይነት የአብሮነት መንፈስ ወይም ባሕሪይ ሳንላበስ ክርሲያን ተብለን ልንጠራ በፍጹም አንችልም። እኛ አንድ ህዝብ ነን፣ የእግዚኣብሔር ሕዝብ። በሁኑ ወቅት ፍቅርን በሚገባ በተጠማው በዓለማችን ውስጥ ኢየሱስ የሰጠንን ተልዕኮ በደስታ መወጣት እንችል ዘንድ፣ ሕይወት ጣዕም የሚኖራት ዘላለማዊ በሆነ ፍቅር መሆኑን፣ ተጨባጭ የሆነ ፍቅር የአብ፣ የወልድ እና የመነፈ ቅዱስ ፍቅር መሆኑን ለዓለም በደስታ መመስከር እንችል ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ትረዳን ዘንድ ልንማጸናት ይገባል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.