2018-05-23 16:02:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መነፈስ ቅዱስ ነው” ማለታቸው ተገለጸ።


ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መነፈስ ቅዱስ ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

ባለፉት ስድስት ሳምንታት በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ በተከታታይ ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው”፣ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው”፣ “ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው”፣ “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል”፣ ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ደግሞ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ስያደርጉት በነበረው የመጨረሻ ክፍል አስተምህሮ  “የክርስትና እናት እና የክርስትና አባት” የክርስትና ልጆቻቸው የእምነት ጎዳናን ተከትለው ያድጉ ዘንድ ልያስተምሩዋቸው እና ሊረዱዋችው የገባል” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የእዚህን ስርጭት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ

በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 15/2010 ዓ.ም ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ባለፈው እሁድ ማለትም በግንቦት 12/2010 ዓ.ም በተከበረው የጴንጤቆስጤ በዓል ላይ ተመረኩዘው መንፈስ ቅዱስ በምስጢረ ጥምቀት የእግዚኣብሔር ልጆች የሆኑትን ስዎች ሁሉ በሕይወት ጎዞዋቸው ይረዳቸዋል በማለት ምስጢረ ጥምቀት ከተቀበልን በኃላ በምስጢረ ጥምቀት የተቀበልነውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ይበልጡኑ በሚረጋገጥበት በምስጢረ ሜሮን ላይ ትኩረቱን ያደርገ አስተምህሮ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “የምድር ጨው እና ብርሃን እንድንሆን ኃይልን የሚሰጠን መነፈስ ቅዱስ ነው” ማለታቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በግንቦት 15/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ካደርግነው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በእነዚህ ቀናት ውስጥ የተከበረው የጴንጤቆስጤ ክብረ በዓል መንፈስ ቅዱስ ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበሉ ክርስቲያኖች ውስጥ በመግባት መንፈስ ቅዱስ የሚያነሳሳቸውን የምስክርነት ቃላቶች እንድናስብ ያደርጉናል፣ ሕይወታችን በእንቅስቃሴ ላይ እንድትሆን በማድረግ ለሌሎች መልካም አገልግሎ እንድናውል ያደርገናል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፣ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” (ማቴ 5፡13-16) በማለት ታላቅ ተልዕኮ በአደራ ሰጥቷቸዋል። እነዚህ ምስሎች ባህሪያችንን እንድናስብ የሚያደርጉን ምስሎች ናቸው፣ ምክንያቱም የጨው እጥረት ምግብ ጣዕም የለሽ እንዲሆን ያደርጋል እንዲሁም የብርሃን እጥረት ደግሞ በደንብ እንዳንመለከት ያደርገናል። በእርግጥ ከሙስና ተጠብቀን፣ ጣዕም ያለው ጨው እንድንሆን እና ለዓለም ማብራት የሚችል ብርሃን እንድንሆን የሚያደርገን የክርስቶስ መንፈስ ነው! ይህም ምስጢረ ሜሮንን በምንቀበልበት ወቅት በምንቀባው “ቅብዐ ቅዱስ” የሚሰጠን ጸጋ ነው፣ ዛሬ እዚህ ላይ ቆም ብየ በእዚህ ምስጢር ላይ አስተንትኖ ለማድረግ እፈልጋለሁ። ይህ ምስጢረ ሜሮን “በቅብዐ ቅዱስ” የመቀባት ስርዓት የሚደርግበት ምስጢር ሲሆን ጥምቀታዊ ጸጋን የማጎልበቱን ሂደት በማጠናቀቅ ጥምቀት መረጋገጡን ያሳያል (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህረተ ክርስቶስ ቁ. 1289)፣ በምንቀበለው መልካም መዓዛ ባለው እና በጳጳስ በተባረከ “ቅብዐ ቅዱስ” አማካይነት መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን፣ ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነው፣ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቱዋል ቅብዐ ቅዱስ የሚቀበል ሰው በመንፈስ ቅዱስን ይቀበላል ማለት ነው።

በምስጢረ ጥምቀት አማካይነት ዳግም መወለድ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን፣ ከእዚያን በኋላ እንደ እግዚአብሔር ልጆች በመሆን፣ ይህም ማለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሠራውን ክርስቶስን መከተል ማለት ነው፣ እርሱ በዓለም ውስጥ በሚሰጠው ተልዕኮ ውስጥ ተሳታፊ መሆን ማለት ነው። ለእዚህም ነው በመንፈስ ቅዱስ ቅብዐ ቅዱስ የምንቀባው፣ "ያለ እርሱ ኃይል በሰው ውስጥ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ካልታከለበት እኛ ብቻችንን ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፣ ወደ ፊት እንድንጓዝ ኃይልን የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ልክ ኢየሱስ ሕይወቱ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንደ ነበረ ሁሉ፣ በተመሳሳይ መልኩም በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ሆነ እያንዳንዱን የቤተክርስቲያን አባል የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ነው።

በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ከተወለደ በኃላ ኢየሱስ ተልዕኮውን የጀመረው በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከወጣ በኃላ በእርሱ ላይ በወረደው እና ከእርሱ ጋር ሁልጊዜ በነበረው በመንፈስ ቅድሱ ከተቀደሰ በኃላ ነው። ኢየሱስም ይህንን በናዝሬት ምኩራብ ውስጥ በግልጽ ያውጃል፡ በወቅቱ ኢየሱስ ይህን የገለጸበት አቀራረብ በጣም የሚያምር አቀራረብ ነበረ፣ ይህም በናዝሬት ምኩራን ውስጥ የኢየሱስ ማንነት መገለጫ የመታወቂያ ወረቀት ነበረ! እስቲ እርሱ እንዴ እንደገለጸው እንስማ፣ ግልጽ በሆነ መልኩ ነበር ያቀረበው እንዲህም አለ “የጌታ መነፈስ በእኔ ላይ ነው” ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።” (ሉቃስ 4፡18-19)። ኢየሱስ በገዛ መንደሩ በምኩራባቸው ውስጥ የተቀባ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተቀባ አድርጎ እራሱን ያቀርባል።

ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላና አብ ቃል የገባልን የመንፈስ ቅዱስ ምንጭ ነው። በእውነቱ በፋሲካ ምሽት ከሙታን የተነሳው ጌታ ለደቀመዛሙርቱ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” (ዩሐንስ 20፡11) በማለት ሰጥቶዋቸው ነበር። እንደ ምናውቀው የበዓለ ሃምሳ ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድነት፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው በነበረበት ወቅት ድንገትም በሚያስግርም ሁኔታ ሐዋሪያት መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ (የሐዋሪያት ሥራ 2፡1-4)።

ከሞት የተነሳው ክርስቶስ "እስትንፋስ" የቤተክርስቲያኗን ሳንባዎች በህይወት ይሞላሉ። በእርግጥ የደቀመዛሙርቱ ልሳኖች "በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው" ለሁም ፍጥረታት የእግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎች ማብሰር ጀመሩ።

ባሳለፍነው ሣምንት እሁድ ያካበርነው የጴንጤቆስጤ በዓል (የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ማለት ነው) ባሳለፍነው ሣምንት እሁድ ያከበርነው የጴንጤቆስጤ በዓል ቤተክርስቲያን ሆነች እንዲሁም ክርስቶስ በዮርዳኖስ የተቀበለውን የመንፈስ ቅዱስ ቅባት ለሌሎች ቅድስና እና ለእግዚኣብሔር ክብር ይሆን ዘንድ ሕይወታችንን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ እንድናውል ይጋብዘናል። በሁሉም ምስጢርት አማካይነት መነፈስ ቅዱስን የምንቀበል ሲሆን ነገር ግን ለየት ባለ ሁኔታ በምስጢረ ሜሮን አማካይነት “ምዕመኑ የእግዚኣብሔር ስጦታ የሆነውን መነፈስ ቅዱስ ይቀበላለሉ”። ምስጢረ ሜሮን በሚሰጥበት ወቅት ጳጳሱ “በስጦታ መልክ የተሰጠህን መንፈስ ቅዱስ ተቀበል” በማለት ይናገራል። ይህም መንፈስ ቅዱስ የእግዚኣብሔር ታላቅ ስጦታ ነው። ስለእዚህም እኛ ሁላችን በውስጣችን መንፈስ ቅዱስ ይገኛል። መንፍስ ቅዱስ በልባችን እና በነብሳችን ውስጥ ይገኛል። ጣዕም ያለው ጨው እንድንሆን እና ለሰዎች ትክክለኛ ብርሃን እንድንሆን በሕይወታችን የሚመራን መንፈስ ቅዱስ ነው።

በምስጢረ ጥምቀት አማካይነት በክርስቶስ ውስጥ ጠልቀን ከገባን፣ በምስጢረ ሜሮን አማካይነት ደግሞ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላናል፣ የእርሱ ምስክሮች እንድንሆን የቀድሰናል፣ በእርሱ ሕይወት እና ተልዕኮ ውስጥ ተካፋይ እንድንሆን ያደርገናል፣ በእግዚኣብሔር አብ የደኽንነት እቅድ ውስጥ ተካፋይ እንድንሆን ያደርገናል።  ምስጢረ ሜሮንን ለተቀበሉ ሰዎች የሚሰጠው ምስክርነት መንፈስ ቅዱስን መቀበላቸውን ያሳያል፣ የእርሱን ፈጣሪ የሆነ በደግነት የተሞላ አነሳሽነቱ ይታይባቸዋል። እስቲ ልጠይቃችሁ! የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን መቀበላችንን እንዴት እናውቃለን? ይህንን የምናውቀው የመንፈስ ቅዱስን ተግባር ስንሠራ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረንን ቃላት ብቻ ስንጠቀም ነው። የክርስቲያን ምስክርነት የሚያካትተው የክርስቶስ መንፈስ እንድንሰራ የሚጠይቀን ስራ ብቻ ስንሰራ ነው፣ ይህንንም ማድረግ እንችል ዘንድ ጥንካሬን ይሰጠናል። አመስግናለሁ!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.