2018-05-21 15:55:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት 14 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸው ተገለጸ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት 14 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት 14 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እነዚህ አዳዲስ ካሪድናሎች በመጪው ሰኔ 22/2010 ዓ.ም በይፋ የካርዲናልነት ማዕረግ እንደ ሚቀበሉ ተገለጸ። የእነዚህ አዲስ የተሾሙ ካሪዲናሎች መመረጥ የቤተክርስቲያን ሁለንተናዊነት የሚገልጸውን በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ምህረት ፍቅር የማስተጋባት ኃላፊነት እንደ ተጣለባችው የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ አዳዲስ ከርዲናሎች መሾም በቅዱስ ጴጥሮስ መነበር እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ያሳያል ብለዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለወን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በመጪው ሰኔ 22/2010 ዓ.ም በይፋ የካርዲናልነት ማዕረግ የሚቀበሉ  ካርዲናሎች ስም እና የመጡበት አከባቢ የሚከተለው ይሆናል።

  1. በኢራቅ የባቢሎን የቄልቄዶን ስረዓተ አምልኮን በምትከተለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ብጹዕ ፓትሪያርክ ሉዊዝ ራፋኤል ኢሳቅ
  2. በቅድስት መንበር የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ብጹዕ አቡነ ሉዊዝ ላዳሪያ
  3. የሮም ሀገረ ስብከት እንደራሴ የሆኑት ብጹዕ አቡነ አንጄሎ ዴ ዶናቲዝ
  4. የቅድስት መንበር መክትል ጸሐፊ የሆኑት ብጹዕ አቡነ አንጄሎ ቤቹ
  5. ለቅድስት መነበር የሚሰጡትን ሐዋሪያዊ ምጽዋዕቶች የሚንከባከበው ቢሮ ዋና ኃላፊ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኮናርድ ካርጄዋስኪ
  6. በፓኪስታን የካራቺ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ኩቱስ
  7. በፖርቹጋል የሊዬሪያ ፋጢማ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ አንቶኒዮ ዶስ ሳንቶስ ማርቶ
  8. በፔሩ የሁንካዮ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ፔድሮ ባሬቶ
  9. በማዳጋስካር ቶዋማዚና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ዴዝሬ ጻራዛና
  10. በጣሊያን የአኩዊላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ጁሴጴ ፔትሮኪ
  11. በጃፓን የኦሳካ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቶማስ አኩዊናስ ማንዮ
  12. በሜክሲኮ የቀድሞ የኃላፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ሴርጆ ኦቤዞ ሪቬራ
  13. በቦሊቪያ የኮርኮሮ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘው ሐዋሪያው ማኅበር የበላይ አስተዳዳሪ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቶሪቢዮ ቲኮና ፖርኮ
  14. በጣሊያን የመነኩሳት ማኅበር የነገረ መለኮት ተቋም ዋና ኃልፊ የሆኑት ብጹዕ አቡነ አኩሊኖ ቦኮስ ሜሪኖ መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህ አዲስ የተሾሙት ካርዲናሎች ማኅሪ እና ታማኝ ሊቀ ካህን ለሆነ ለከርስቶስ ታማኝ በመሆን አገልግሎታቸውን ይወጡ ዘንድ እና የሮም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆንኩኝ እኔን ቅዱስ ለሆነው የእግዚኣብሔር ሕዝብ በምሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የእኔ አጋዥ ሆነው ይቀጥሉ ዘንድ መጸለይ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።  







All the contents on this site are copyrighted ©.