2018-05-17 13:35:00

በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት በጋዛ እይተከሰተ የሚገኘው ግጭት ሊቀረፍ የሚችል ግጭት ነው ማለታቸው ተገለጸ


በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት በጋዛ እይተከሰተ የሚገኘው ግጭት ሊቀረፍ የሚችል ግጭት ነው ማለታቸው ተገለጸ።

በቅድስቲቷ ሀገር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት በዛሬው እለት በግንቦት 09/2010 ዓ.ም በጋዛ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጡት መግለጫ እንደ ግለጹት አሁን በጋዛ እይተከሰተ የሚገኘው ከፍተኛ የሆነ ግጭት ሊቀረፍ የሚችል ግጭት እንደ ነበረ መገለጻቸውን ካወጡት መገለጫ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘቱን ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በቅድስቲቷ ሀገር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት የእስራኤል የጦር ኃይል እየወሰደ በሚገኘው ከፍተኛ እና ያልተመጣጠነ ኃይል የተቀላቀለበት እንቅስቃሴ እንደ ሚያወግዙ ካወጡት መገለጫ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ለእዚህ ብጥብጥ መንሴ የሆነው በቅርቡ የአማሪካ መንግሥት ኤንባሲውን ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም በማዛወሩ የተነሳ እንደ ሆነ በመጥቀስ ይህንን ድርጊት እንደ ሚቃወሙት ብጹዕን ጳጳሳቱ ገልጸው በእዚህ ድርጊት የተነሳ ይህንን በሚቃወሙ ፍልስጤማዊያን እና በእስራኤል የጦር ኃይል መካከል በተለይም ደግሞ በጋዝ በተነሳው ብጥብጥ ከፍተኛ እልቂት መደረሱ እዳሳዘናቸው በቅድስቲቷ ሀገር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት በመገለጫቸው ጠቅሰዋል።

የአሜሪካ መነገሥት ኤምባሲውን ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሩ ምክንያት እና በተለያዩ ተመሳሳይ ድርጊቶች ምክንያት ጥላ ያጠላበት የሰላም ሂደት ላይ በድጋሚ አደጋ የሚጥል ድርጊ እንደ ሆነ ጠቅሰው ሰላምን ከማረጋገጥ እና ከመገንባት ይልቅ ሰላምን የሚያሳጣ እና በቀጠናው አለመረጋጋትን የሚፈጥር ተግባር እንደ ሆነ የገለጸው መግለጫው በቀጠናው ሰላምን ለማምጣት እና የሰው ልጆችን እልቂት ለመቀነስ ኢየሩሳሌም የእስራኤል እና የፍልስጤማዊያን የጋራ ዋና ከተማቸው ሆና መቀጠል ይገባታል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የቫቲካን የዜና ምንጭ የሆነው ፊዴስ ይህንን በተመለከተ ካጠናከረው ዘገባ ለመረዳት እንደ ተቻለው በቅድስት ሀገር የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ካደርጉት አስቸኳይ ስብሰባ በኃላ ባወጡት መገለጫ እንዳሳሰቡት በቅድሚያ ይህ ብጥብጥ እና ግጭት እንዲቆም፣ በመቀጠልም በጋዛ ስርጥ የሚገኙ ከሁለት ሚልዮን በላይ የሆኑ ፍልስጤማዊያን አፋጣኝ የሆነ ሰብኣዊ እርዳት ይደረግላቸው ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸውን ከመግለጫው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የቀጠናውን ሰላም በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ እንዲጋለጥ ያደርገው አሜርካ ኤንባሲዋን ከቴላቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማዘዋወር ያደርገችው የአሜሪካን የተናጥል ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር በመሆኑ የተነሳ ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ እንደ ሆነ በአጽኖት ገለጸዋል።

የእየሩሳሌምን እጣ ፈንታ በተመለከተ በቅርቡ የቫቲካን አቋሟን መገለጹ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መስረት ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከቅድስት መንበር ከወጣው መግለጫ ለመረዳት እንደ ተቻለው ቫቲካን ቅድስቲቷ ከተማ እየሩሳሌም የእስራኤል እና የፍልስጤም የጋራ ዋና ከተማቸው ሆና ለሁለቱም ሕዝቦች ክፍት የሆነች ከተማ ሆና እንድትቀጥል ፍላጎቷ መሆኑን ከቅድስት መንበር ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህንን በቅርቡ ቅድስት መንበር እየሩሳሌምን አስመልክቶ ያወጣችሁን መግለጫ በዋቢነት በመጥቀስ አሁን ስላለው ሁኔታ መገለጫ ያወጡት በቅድስቲቷ ሀገር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት እየሩሳሌም በአንዱ አምላክ የሚያምኑ የሦስት ሐይማኖቶች መቅመጫ ቦታ በመሆኗ የተነሳ ለሁሉም ክፍት የሆነች ከተማ እንድትሆን እንደ ሚፈልጉም ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

እየሩሳሌም የእስራኤል እና የፍልስጤም ዋና ከተማ ሆና ከመቀጠል የሚያግዳት ምንም ነገር እንደ ሌለ የጠቀሱት በቅድስቲቷ ሀገር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ሁለቱ አካላት ይህንን ጉዳይ በድርድር እና እርስ በርስ በመከባበር ላይ በተመሰረት መልኩ ሊፈቱት እንደ ሚገባ አክለው መገለጻቸውን የቫቲካን የዜና ምንጭ የሆነው ፊደስ ካወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.