2018-05-14 15:44:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “የእርገት በዓለ መሬት ላይ በእግራችን በመቆም ወደ ሰማይ እንድንመለከት ይረዳናል”።


የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ያረገበት የዕርገት በዓል በትላንትናው እለት ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙት ስብከት መሰረቱን አድጎ የነበረው ኢየሱስ ሐዋሪያቱን “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” (ማርቆስ 16፡15-20) በሚለው የቅዱሱ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የእርገት በዓል ሁለት ዋና ዋና መሰረታዊ ክፍሎች እንዳሉት ገልጸው በአንድ በኩል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ክብር በቀኝ በኩል ወደ ተቀመጠበት ወደ ሰማይ ዓይናችንን እንዲያመራ ያደርጋል በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያን ተልእኮ ጅማሬ ያሳስበናል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። 

የእዚህን አስተንትኖ ሙልዩ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በጣሊያን እና በሌሎች ብዙ ሀገሮች የጌታ እርገት ክብር በዓል ይከበራል። ይህ በዓል ሁለት ዋና ዋና መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን አቅፎ ይዙዋል። በአንድ በኩል ይህ ክበረ በዓል ዓይናችንን ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ በክብር ወደ ተቀመጠበት ወደ ሰማይ እንዲያመራ ያደርጋል። በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያን ተልዕኮ እንደ ተጀመረ ያስታውሰናል። ይህም የሆነበት ምክንያት ከሙትና የተነሳው እና ወደ ሰማይ ያረገው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያቱን ወደ ዓለም ሁሉ በመሄድ ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም እንዲያበስሩ ስለላካቸው ነው። ከእዚህ ከእርገት በዓል በኃላ እይታችንን ወደ ሰማይ በማድረግ ከእዚያን በመቀጠል ደግሞ ወደ ምድር በመመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአደራ የሰጠንን ተልዕኮ መተግበር ይገባናል።

ይሄ እኛ ዛሬ የሰማነው የቅዱስ ወንጌል ምንባብ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ሐዋሪያቱ እንዲያከናውኑት በአደራ የሰጣቸው ተልእኮ ነው። ይህ ድንበር የለሽ ተልዕኮ ነው! ማለትም ከሰው አቅም በላይ የሆነ ወሰን የለሽ ተልዕኮ ነው ማለት ነው።   ኢየሱስ በእርግጥወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ለሁሉም ፍጥረታት አብስሩ” (ማርቆስ 1615) ይለናል። በእርግጥም ኢየሱስ በጣም ጥቂት ለሆኑት ተራ ሰዎች እና ምንም ዓይነት ስነ-አእምሮኣዊ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች ይህንን ተልዕኮ በአደራ መስጠቱ ድፍረት የተሞላው ነገር ይመስላል! ወይም ደግሞ ይህ የመነመነ ቡድን በዓለም ታላላቅ ኃይሎች ዘንድ የማይረባ ነገር ተደርጎ የሚቆጠረውን የኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅርና የምሕረት መልእክት ወደ ሁሉም አቅጣጫው ለማድረስ ይላካል። ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር ለሐዋሪያቱ የሰጠው ተልዕኮ ተግባራዊ የሚሆነው እግዚኣብሔር ራሱ ለሐዋሪያቱ በሚሰጠው ኃይል ብቻ ነው። ይህም ማለት ይህ ተልዕኮ የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ እንደማይለየው ኢየሱስ ራሱ  ለሐዋሪያቱ አረጋግጦላቸዋል። እንዲሁም ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁብሎዋቸው ነበር። ስለዚህ ይህ ተልዕኮ እውን የሆነው በእዚሁ መልኩ ነው፣ ሐዋሪያት ይህንን ተልዕኮ አስጀምረውታል ከእዚያም የእነርሱ ተተኪዎች ይህንን ተልዕኮ እያስቀጠሉት ይገኛሉ። ኢየሱስ ለሐዋርያቱ በአደራ የሰጠው ተልዕኮ በዘመናት ውስጥ ቀጥሎ ይገኛል፣ ዛሬም ይቀጥላል፣ ይህ ተልዕኮ የሁላችንንም ትብብር ይጠይቃል። በእርግጥ እያንዳንዳችን ምስጢረ ጥምቀት በተቀበልንበት ወቅት በተቀበልነው የመንፈስ ቅድሱ ስጦታ አማክይነት ቅዱስ ወንጌል የማብስር ተልዕኮዋችንን እያንዳንዳችን መወጣት ይኖርብናል። ለእኛ ኃይል የሚሰጠን እና የወንጌል ሰባኪዎች እንድንሆን የሚያበረታታን ምስጢረ ጥምቀት በተቀበልንበት ወቅት የተሰጠን መንፈስ ነው።

የጌታ ወደ ሰማይ ማዕረግ ኢየሱስ በአዲስ መልክ በእኛ መካከል እንደ ሚገኝ በር የሚከፍት አጋጣሚ ሲሆን እርሱን ለማገልገል እና እርሱን ለመመስከር ዓይንና ልብ እንዲኖረን ይጠይቃል። የጌታ ዕርገት ተካፋይ የሆንን ሰዎች እንድንሆን ይጠይቀናል፣ ይህም ማለት በዘመናችን ውስጥ ኢየሱስን መፈለግ እና የኢየሱስን የደኽንነት ቃል እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ማብሰር ማለት ነው። በዚህ ጉዞ ውስጥ ክርስቶስን በወንድሞቻችን ውስጥ በተለይም በድኾች ውስጥ፣ በድሮ እና በአዲሱ ስርዓቶች የተነሳ በተፈጠረው ድኽነት በሚሠቃዩ ሰዎች ውስጥ ኢየሱስን እናገኛለን። ከሙትና የተነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያዎቹን ሐዋሪያት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተው እንደ ላካቸው ሁሉ ዛሬም ቢሆን በተመሳሳይ ኃይል ተሞልተን፣ ተጨባጭ በሆነ ምልክት ታግዘን በተስፋ ምልክት ተሞልተን ተልዕኮውን እንድናስቀጥል ሁላችንንም ይልከናል። ምክንያቱም ኢየሱስ ተስፋን ስለሰጠ፣ ወደ ሰማይ ሄዶ የሰማይን ደጃፎች ስለከፈተልን እና እኛም በእዚያ እንደ ምንገኝ ተስፋን ስለሰጠን ነው። የመጀመሪያዎቹን ሐዋሪያት  እምነት ያነሳሳች፣ በስረዓተ ቃዳሴ ወቅት እንደ ምንለውለባችንን ወደ ሰማይ ከፍ ማድረግእንችል ዘንድ እንድትረዳን ከሙታን የተነሳው እና ወደ ሰማይ ያረገው እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምን ልንማጸናት ይገባል። በተመሳሳይ መልኩም እግሮቻችንን በምድር ላይ በማድረግ በታላቅ ብርታት ተጨባጭ በሆነ መልኩ በሕይወታችን ዘመን እና በታሪክ ውስጥ የቅዱስ ወንጌል ቃል ለመዝራት ትርዳን።








All the contents on this site are copyrighted ©.