2018-05-11 15:35:00

“ስር መስረታችሁን ጠብቃችሁ፣ መጪው ጊዜ በተስፋ እና በእምነት ተሞልታችሁ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርባችኃል”


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 02/2010 ዓ.ም ከሃያዎቹ ጣሊያን አውራጃዎች ውስጥ ሁለቱን ማለትም የግሮሴቶ እና የፍሎረንስ አምራጃዎችን መጎብኘታቸውን መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን በግሮሴቶ  ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ኖማዴልፊያ የተሰኘችውን ትንሽ ከተማ እና  በፍሎሬንስ አዋራጃ የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምትባል ከተማ ተገኝተው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን በትላንትናው እለት መዘገባችን ይታወሳል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጭወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 02/2010 ዓ.ም ያደረጉትን ሐዋሪያዊ ጉብኝት የጀመሩት በግሮሴቶ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ኖማዴልፊያ የተሰኘችውን ትንሽ ከተማ በመጎብኘት እንደ ነበረ በትላንትናው እለት መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግሮሴቶ ሀገረ ስብከት ሥር ያለቸውን ኖማዴልፊያ የተባለችሁን ትንሽ ከተማ ተገኝተው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ካደርጉ በኃላ በመቀጠል  የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምታባለውን ከተማ መጎብኘታቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በሎፒያኖ በነበራቸው ቆይታ የFocular እንቅስቃሴ ማኅበር አባላት ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው እና በወቅቱ ቅዱስነታቸው ከ7000 በላይ ለሚሆኑ የFocular እንቅስቃሴ ማኅበር አባላት ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን “ስር መስረታችሁን ጠብቃችሁ፣ መጪው ጊዜ በተስፋ እና በእምነት ተሞልታችሁ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርባችኃል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ይህ የfocular movment በመባል የሚታወቀው ዓለማቀፍ ንቅናቄ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጀመረ ወይዘሮ ኪያራ ሉቢክ በሚባሉ አንድ ሴት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1943 ዓ.ም በጣሊያን ቴሬንቶ ተብሎ በሚታወቅበት ሥፍራ የተመሰረተ ንቅናቄ ሲሆን ይህም በወቅቱ በነበረው የሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት የቴሬንቶ ከተማ ከደረሰባት ከፍተኛ የቦንብ ድብደባ ማግሥት የተመስረተ  ምዕመናን በከፍተኛ ሁኔታ የሚሳተፉበት ንቅናቄ እንደ ሆነ ይታወቃል። የእዚህ ንቅናቄ መስራች የሆኑት ወይዘሮ ኪያራ ሉቢክ በጦርነት ሳቢያ በሚደርሰው አደጋ ከፈተኛ የሆነ የንብረት ውድመት የሚከሰት እና ሕዝቡ ለከፍተኛ ቁሳዊ ነገሮች እጥረት እንዲዳረግ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው ነገር ግን ጦርነት የእግዚኣብሔርን እና የፍቅር እጥረት ሊያስከትል በፍጹም አይችልም በማለት አዘውትረው ይናገሩ እንደ ነበረ ይታወሳል።

በእዚህም መሰረት የእዚህ የፎኮላር የምዕመናን ንቅናቄ ማኅበር አባላት በዩሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 17:21 ላይ ኢየሱስ “አባት ሆይ፤ አንተ በእኔ፣ እኔም በአንተ እንዳለሁ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ዘንድ እለምንሃለው” ብሎ ለሰዎች አንድነት መጸለዩን በማስታወስ በሕዝቦች መካከል አንድነት እና ፍቅር እንዲጠናከር የሚሰራ ዓለማቀፍ የምዕመናን ንቅናቄ ማኅበር እንደ ሆን የሚታወቅ ሲሆን የማንኛውም ሐይማኖት አባላት የሚሳተፉበት፣ ውይይት የሚደርግበት በተለያዩ ባሕሎች መካከል መግባባት እንዲፈጠር በውይይት ላይ መስረቱን ያደርገ የግጽጭት አፈታት ሁኔታዎችን የሚያመቻች በካቶሊክ ቤተክርስቲይና ጥላ ሥር የሚተዳደር የምዕመናን ንቅናቄ ማኅበር ነው የፎክላር ንቅናቄ።

ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 02/2010 ዓ.ም  በሎፒያኖ ባደረጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ወቅት ለእነዚህ ቀደም ሲል ለገለጽነው ከ7000 በላይ ለሚሆኑ የFocular እንቅስቃሴ ማኅበር አባላት ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ቀደም ሲል መገለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት የእዚህን የፎኮላር የምዕመናን ንቅናቄ ማኅበር ዓላማ ጠብቃችሁ እና መጪው ጊዜ በተስፋና በእመንት በመሞላት ወደ ፊት መጓዝ ይኖርባችኃል ማለታቸው ተገልጹዋል።

የፎኩላር የምዕመናን ንቅናቄ ማኅበር ዓለም አቀፋዊ አንድነትን እና ሰላምን ለመገንባት የሚያግዙ ውይይቶችን እንዲበረታቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ሰላምን እና አንድነትን የሚፈጥሩ የአኗኗር ዘይቤ የሚከተል ንቅናቄ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዓለማቀፍ ደረጃ ከ2 ሚልዮን ሕዝብ በላይ የእዚህን ማኅበር ዓለማ በመደገፍ የተለያዩ ዓይነት እንቅስቃሴዎች በአሁኑ ወቅት እያደርጉ እንደ ሚገኝ ይታወቃል፣ የእዚህ የፎኩላር ንቅናቄ አባላት አብዛኞቹ የተውጣጡት ከክርስቲያን አብያተክርስቲያንት ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የክርስትናን እመንት የማይከተሉ ሰዎች እንደ ሚገኙበት ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ የፎኩላር ንቅናቄ ማኅበር በዓለም ደረጃ ከ1000 በላይ የተለዩዩ ፕሮጄክቶችን እያንቀሳቀሰ የሚገኝ ማሕበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህን ፕሮጀክቶች በፋይናንስ የሚደግፉ 800 የሚሆኑ የገንዘብ ማስገኛ ድርጆቶች እንዳላቸውም ይታወቃል።

ቅዱስነታቸው በሎፒያኖ ባደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት የፎኩላር ናቅናቄ ማኅበር በተገኙበት እና 850 ያህል የሎፒያኖ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት ባድረጉት ንግግር እንደ ገለጹት በሎፒያኖ የሚገኙ የማኅበርሰብ ክፍሎች በውስጣቸው ያላቸው የማኅበራዊ ሕይወት የአኑዋናዋር ዘይቤ ሕበረትን እና የወንድማማችነት መንፈስን የሚያጠናክር የአኗኗር ዘደ በመሆኑ የተንሳ ተጠናክሮ መቀጠል እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ገልጸው ይህም ለሌላው የማኅበርሰብ ክፍል በአብነት የሚጠቀስ የአኗኗር ዘይቤ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በአድናቆት ተናግረዋል።

በሎፒያኖ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቬርሲቲዎች በመግባባት እና በፍቅር መንፈስ በተሞላው መልኩ የሚታደሩ መሆናቸውን በማንሳት ያወደሱት ቅዱስነታቸው ይህ የአብሮነት ጉዞ፣ አብሮ የምስራት ባሕል እና በመካከላቸው የሚታየው ፍቅር መልካም በመሆኑ የተነሳ ሌሎች የማኅበርሰብ ክፍሎች በአብነት ሊጠቀሙበት እንደ ሚገባ ገለጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.