2018-05-11 10:43:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምታባለውን ከተማ መጎብኘታቸው የተገለጸ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግሮሴቶ ሀገረ ስብከት ሥር ያልቸውን ኖማዴልፊያ የተባለችሁን ትንሽ ከተማ በግንቦት 02/2010 ዓ.ም ተገኝተው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ካደርጉ በኃላ በመቀጠል  የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምታባለውን ከተማ መጎብኘታቸው የተገለጽ ሲሆን በእዚያ የሚገኘውን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም ስም የተሰየመውን የጸሎት ስፍራ ተገኘተው ከጎበኙ በኃላ የገል ጽሎት ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ቅዱስነታቸው በግል ካደርጉት ጸሎት በመቀጠል ባድረጉት አጭር ንግግር እንደ ግለጹት እነዚህን ሁለት ከተሞች የመጎብኘት ከፍተኛ የሆነ ጉጉት እንደ ነበራቸው አውስተው በተለይም ያላቸውን ጠንካራ የሥራ ባሕል እና የወንድማማችነት መንፈስ በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ሚያደንቁ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በሎፒያኖ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች ያላቸው ጠንካራ የወንድማማችነት እና የፍቅር መነፈስ የሚይስቀና እንደ ሆነ የገልጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ማኅበርሰብ ውስጥ የሚታየው ከፍተኛ ፍቅር የቅዱስ ወንጌል እሴት መገለጫ ነው ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የፊዞሌ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኘውን ሎፒያኖ የምታባለውን ከተማ መጎብኘታቸው የተገለጸ

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.