2018-05-07 09:50:00

ካርዲናል ታግሌ “ሁላችንም ብንሆን በአንድ ወቅት ስደትኞች የነበርን መሆናችንን በፍጹም መርሳት የለብንም” ማለታቸው ተገለጸ።


የፍሊጲንሲ ዋና ከተማ ማኔላ ሊቀጳጳስ የሆኑት እና ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ (Caritas Internationalis) የተባለ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድርጎት ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ካርዲናል ሉዊስ ኣንቶኒኦ ታግሌ እንደ ገለጹት ስደተኞች ወደ ሀገራችን እንዳይገቡ ለማድረግ የግንብ አጥር መሥራት ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው ሁላችንም ብንሆን በአንድ ወቅት ስደተኞች የነበርን በመሆናችን የተነሳ በደማችን ውስጥ የስደተኛ ደም ይገኛል ማለታቸው ተገለጸ።

ባለፈው መስከረም 20/2010 ዓ.ም. በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት Share the journey በአማሪኛው “የስደተኞችን ጉዞ እንጋራ” በሚል መሪ ቃል ስደተኞችን የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያሳስብ ንቅናቄ መጀመሩን ያስታወሱት ካርዲናል ታግሌ  ይህንን ቅዱስነታቸው ባለፈው መስከረም ወር ያስጀመሩትን እና የስደተኞችን ጉዞ እንጋራ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው እንቅስቃሴ እርሳቸው የሚመሩት Caritas Internationalis የተሰኘው ዓለማቀፍ የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅት ይህንን ንቅናቄ በመደገፍ ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ የተጀመረውን ንቅናቄ ለመደገፍ በማሰብ ከሚቀጥለው ሰኔ 10-17/2010 ዓ.ም. ደረስ በዓለምቀፍ ደረጃ የተለያዩ ዓይነት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ለስደተኞች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል Caritas internationalis የበኩሉን አስተዋጾ ለማደረግ ቅድመ ዝግጅቱን እናዳጠናቀቀ ካሪዳንል ታግሌ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ share the journey የስደተኞችን ጉዞ እንጋራ  በሚል መሪ ቃል በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት ባለፈው መስከረም 10/2010 ዓ.ም የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ በመቀጠል በሚቀጥለው ሰኔ ወር ላይ caritas internationalis ያዘጋጀው የአንድ ሳምንት ንቅናቄ በአሁኑ ወቅት ስደተኞችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ የሚገኙ የማኅበርሰብ ክፍሎችን ለማበረታታት ታቅዶ የተዘጋጀ ዓለማቀፍ ንቅናቄ እንደ ሆነ የገለጹት ካርዲናል ታግሌ በተለይም ደግም ይህ ንቅናቄ ከእያንዳንዱ የካቶሊክ ቁምስናዎች በመጀመር፣ ስደተኞችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ የሚገኙ የማኅበርሰብ ክፍሎች ከስደተኞች ጋር ተቀራርበው እንዲመካከሩ እና የባሕል ግንኙነታቸው የሰፋ እንዲሆን ለማስቻል ከስደተኞች ጋር በጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ይወያዩ ዘንድ ለማስቻል ምሳ አብረው የሚቋደሱበት ዝግጅት እንደ ተዘገጀ ገልጸው ይህንን እና ይህንን የመሳሰሉ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ስደተኞች የተቀበሉዋቸውን የማኅበርሰብ ክፍል ባሕል ጋር እንዲዋሀዱ የበኩሉን አስተዋጾ የሚያደርግ ንቅናቄ መሆኑን ካርዲናል ታግሌ ጨምረው ገለጸዋል።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶ እና caritas Internationalis ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ ያስፈልጋል የሚለው አቋም ለምንድነው በጣም አስፈላጊ የሆነ አቋም የሆነው? በማለት የቫቲካን ጋዜጠኛ ለፍሊጲንሲ ዋና ከተማ ማኔላ ሊቀጳጳስ ለሆኑት እና ካሪታስ ኢንተርናሲኦናሊስ በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድርጎት ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ካርዲናል ሉዊስ ኣንቶኒዮ ታግሌ ላቀረበላቸው ጥያቄ ካርዲናል ታግሌ በሰጡት ምላሽ እንደ ገለጹት የሰዎች ዝውውር ክስተት አዲስ የሆነ ክስተት እንዳልሆነ ገልጸው ነገር ግን በዘመናችን እየተከሰተ ያለው የስደተኞች ሁኔት በቁጥር በጣም ከፍተኛ የሆነ በመሆኑና በአስገዳጅ ሁኔታዎች የተነሳ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ቀን በቀን እየጨምረ በመምጣቱ የተነሳ መሆኑን ካርዲናል ታግሌ ጨምረው ገለጽዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና caritas internationalsi ስደተኞችን በተመለከተ የምያሳዩት ቁርጠኝነት ከሁለት ነገሮች የመነጨ መሆኑን ጨምረ የገለጹት ካርዲናል ታግሌ አደኛው እና ዋነኛው ሰደተኞችን መነከባከብ ያስፈልጋል የሚለው አስተሳሰብ የመነጨው ከሰበዓዊ አስተሳሰብ የመነጨ እንደ ሆነ ገለጸዋል። “አዎን! ስደተኞችን በተመለከተ የሚነሱ ብዙ ክርክሮች፣ ጽንሰ-ሐሳብ እና መላምቶች በእየለቱ እየተሰጡ” እንደ ሚገኙ ያወሱት ካርዲናል ታግሌ ምንም ይሁን ምን ስደተኞች የሰው ልጆች ናቸው ከሚለው ሐሳብ በመነሳት ለእነዚ የሰው ልጆች ለሆኑት ስደተኞች ተገቢውን ሰብዐዊ ክብር መስጠት ያስፈልጋል የሚል መሰረት ያለው እንደ ሆነ ካርዲናል ታግሌ ጨምረው ገለጸዋል።

ለስደተኞች እንክብካቤ ማደርግ ያስፈልጋል የሚለው አቋም በሁለተኛ ደረጃ የመነጨው ከመንፈሳዊነት ወይም ከእምነት መሆኑን የገለጹት ካርዲና ታግሌ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ተጠቅሶ እንደ ምናገኘው የእስራኤል ሕዝቦች በግብጽ ሀገር ተሰደው መሄዳቸውን አስታውሰው ለእነዚህ በወቅቱ ድኽ እና ጎስቋላ ለነበሩ ስደተኛ የእስራኤል ሕዝቦች እግዚኣብሔር እንክብካቤ ያደርግላቸው እንደነበረ እንዲሁም ከባርነት ቀነበር ሥር በማውጣት ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደ መራቸው፣ ኢየሱስ ራሱን እንደ ስደተኛ እና እንደ መጤ አድርጎ ይቆጥር ሰለበረ በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉ በእምነት ላይ መሰረታቸውን ባደርጉ አስተሳሰቦች የመነጨ እንደ ሆነ ካሪድናል ታግሌ ጨምረው ገለጸዋል።

የፍሊጲንሲ ዋና ከተማ ማኔላ ሊቀጳጳስ ለሆኑት እና ካሪታስ ኢንተርናሲኦናሊስ በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድርጎት ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ካርዲናል ሉዊስ ኣንቶኒዮ ታግሌ “share the journeyየስደትኞችም ጉዞ እናጋራ በሚል መሪ ቃል caritas internationalsi በመጪው ሰኔ ወር ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ዓለማቀፍ ንቃንቄን አስመልከተ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆያ ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “ሁላችንም ታሪካችንን በፍጹም መርሳት አይኖርብንም፣ በአሁኑ ዘመን በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር ይባዛም ይነስም በአንድ ወቅት በእኛ ታሪክ ውስጥ ተከስቶ ያለፈ ነገር መሆኑን ማሰብ እንደ ሚገባ ገለጸው በእዚህም የተነሳ ስደተኞ የእኛ ወንድም እና እህቶቻችን መሆናቸውን በፍጹም መዘንጋት የለብንም ካሉ በኃላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.