2018-05-01 12:25:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የክርስቲያኖች ፍቅር የመነጨው ከርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰብ ሳይሆን ከኢየሱስ ነው”


የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ አምስተኛው የትንሳኤ ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት አምስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የክርስቲያኖች ፍቅር የመነጨው ከርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰብ ሳይሆን ከኢየሱስ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በእዚህ ባለንበት አምስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት የተነበቡልን የእግዚኣብሔር ቃላት ከሙታን የተነሳው ጌታ ማኅበር አባላት እንድንሆን የሚያስችሉንን መንገዶች እና ሁኔታዎች ማመላክቱን ቀጥሉዋል። ባለፈው ሳምንት የነበረው የእግዚኣብሔ ቃል በአማኞች እና መልካም እረኛ በሆነ በኢየሱስ መካከል ያለው ግንኙነት ተብራርቶ ነበር። ዛሬ የተነበበልን የወንጌል ክፍል (ዩሐንስ 151-8) ውስጥ ኢየሱስ ራሱን እንደ እውነተኛ የወይን ግንድ አድርጎ በማቅረብ ከእርሱ ጋር ኅብረት መስርተን እንድንኖር ይጋብዘናል። የወይን ተክል በርክት ያሉ ቅርንጫፎ ያሉት እና ሁሉም ቅርንጫፎች ከግንዱ ጋር የተያያዘ ተክል ነው፣ እነዚህ ቅርንጫፎች ፍሬያማ ሊሆኑ የሚችሉት ከግንዱ ጋር አብረው መኖር ሲችሉ ብቻ ነው። ይህ አብሮነት የክርስትና ሕይወት ምስጢር ሲሆን የወንጌሉ ጸሐፊ ዮሐንስ "አብሮ መኖር" ከሚለው ግስ ጋር አዛምዶታል፣ ይህም ቃል በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሰባት ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል።በእኔ ብትኖሩይላል ጌታ በእርሱ ውስጥ ጸንተን እንኖራለን።

ከጌታ ጋር አብሮ መኖር ማለት ከራሳችን ከምቾታችን፣ ከተከለሉ እና ጥበቃ እየተደረገባቸው ከሚገኙ ቦታዎቻችን ውስጥ እንድንወጣ ብርታትን በመስጠት፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ፍላጎት እንድንሻገር ለማድረግ እና ለዓለም ክርስቲያናዊ ምስክርነትን ሰፋ አድርገን ለመስጠት እንድንችል ያበረታታናል። ይህ ከራሳችን ውስጥ በመውጣት እና ለሌሎች ሰዎች ፍልጎቶች ራሳችንን ማቅረብ የሚያስችለን ብርታት የሚመነጨው ከሙታን ከተነሳው  ከኢየሱስ እና በታሪካች ውስጥ መነፈስ ቅዱስ አብሮን እንደ ሚጓዝ ከለን እርግጠኛነት የተነሳ ነው። በእርግጥ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት በመፍጠራችን ምክንያት ከምናገኘው የበሰሉ ፍሬዎች መካከል አንዱ ኢየሱስ እኛን እንደ ወደደን እኛም ለባልንጀሮቻችን የምናሳየው ልግስና እና የራሳችንን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ለወንድሞቻችን አገልግሎት ራሳችንን ማዘጋጀት የሚለው ቀዳሚ ፍሬ ነው። ምዕመኑ የሚያከናውነው የፍቅር ተግባር የሚመነጨው ስልታዊ አስተሳሰቦች፣ ከውጫዊ ፍላጎቶች የመነጨ እና ከማኅበራዊ ጽነሰ-ሐሳቦች የፈለቀ ሳይሆን ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር በምናደርገው ግንኙነት እና ከኢየሱስ ጋር አብሮ ከመኖር የመነጨ ነው። እርሱ ለእኛ የሕይወት ግንዳችን በመሆን በማኅበረሰቡ ውስጥ ለየት ባለ ሁኔታ በመኖር ራሳችንን ለማኅበረሰቡ አገልግሎት በማዋል የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ሰዎች ቀዳሚ የሆነ ስፍራ እንድንሰጣቸው ያበረታታናል።

ቅርንጫፎች በጣም የተዛመዱ እና ከግንዱ ጋር የተገናኙ እንደ ሆኑ ሁሉ አንድ ሰው በተመሳሳይ መልኩ ከጌታ ጋር ግንኙነት ያለው ከሆነ ከሙታን ከተነሳው ጌታ የመነጩትን እና የአዲስ ሕይወት ፍሬ የሆኑትን  ምሕረት፣ ፍትህ እና ሰላም የማረጋገጥ ችሎታ ይኖረዋል። ቅዱሳን ሕይወታቸውን በምልኣት የኖሩ እና ምስክርነታቸውን በልግስና የገለጹ እውነተኛ ግንድ የሆነው የጌታ ቅርንጫፎች ነበሩ። ነገር ግን ቅዱስ ለመሆን የግድጳጳስ፣ ካህን፣ ገዳማዊ/ገዳሚት መሆን አይጠበቅብንምእኛ ሁላችን፣ ሁሉም ሰው በፍቅር በመኖር እና እያንዳንዳችን በእየለቱ በእያለንበት ቦታ በምናከናውናቸው እለታዊ ተግባሮቻችን ውስጥ ምስክርነትን በመስጠት የቅድስና ሕይወት እንድንኖር ተጠርተናል። እያንዳንዳችን ከሙታን የተነሳው ጌታ በሚሰጠን ሃብት ታግዘን ቅዱሳን እንድንሆን ተጠርተናል። እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፣ እያንዳንዱ ሥራ እና እረፍት፣ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ በሆነ ሕይወት ውስጥ፣ በተሰጠን ፖሌቲካዊ ኃላፊነት ውስጥ በባህላችን እና በኢኮኖሚ ውስጥ በአጠቃላይ ይነስም ይብዛም በሁሉም እንቅስቃሴ ውስጥ ከኢየሱስ ግራ ኅብረት በመፍጠር የምንኖር እና የፍቅር እና የአገልግሎት ባህሪይ በመላበስ የምንኖር ከሆንን በምስጢረ ጥምቀትን እና ወንጌላዊ ቅድስናን ሙሉ በሙሉ የመኖር እድል ይፈጥርልናል ማለት ነው።

የቅዱሳን ሁሉ ንግሥት የሆነችው እና መለኮታዊ ከሆነው ልጇ ጋር ፍጹም የሆነ ኅብረት በመፍጠር አብነት የሆነችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትርዳን። የወይን ቅርንጫፍ ከግንዱ እንደ ማይለይ ሁሉ እኛም ከኢየሱስ ጋር አብረን በመኖር ከእርሱ ፍቅር ፈጽሞ እንዳንለያይ ታስተምረናለች። እንዲያውም ከእርሱ በቀር ምንም ማድረግ አንችልም፣ ምክንያቱም ህይወታችን በቤተክርስቲያኒቷ እና በዓለም ውስጥ የሚኖረው ክርስቶስ በመሆኑ የተነሳ ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.