Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

“እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” በሚል አርእስት በዶሜንክ ዎልተን የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ መብቃቱ ተገለጸ።

“እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” በሚል አርእስት በዶሜንክ ዎልተን የተጻፈ መጽሐፍ ለንባብ መብቃቱ ተገለጸ። - RV

28/04/2018 10:35

በሚያዝያ 16/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር ከሆነው ፈረንሳዊ ዶሜንክ ዎልተን ጋር በተደጋጋሚ አድርገውት የነበረውን ቃለ ምልልስ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ታውቁዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር እና የማኅበራዊ መገናኛ አውታር ጽንሰ ሐሳብ አፋልቂ ከሆነው ፈራንሳዊ ዶሜንክ ዎልቶን ጋር ለአንድ አመት ያህል በተደጋጋሚ መገናኘታቸው እና በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳያች፣ ስለሰላም፣ ስለፖሌቲካ፣ ስለ ዓለማቀፍዊ ጥምረት ወይም ግሎባላይዜሽን፣ ስለሐይማኖት አክራሪነት፣ ማኅበራዊ ፍትህ መጓደሉን፣ በዘመናችን ገንዘብ ጌታ ስለመሆኑ፣ ማንኛውም ኢኮኖሚ የሰው ልጆችን ማዕከል ያደርገ መሆን እንደ ሚገባው፣ ስለስደተኞች፣ ስለአውሮፓ፣ በክርስቲያኖች እና በሌለች ሐያማኖቶች መካከል ሊደርግ ስለሚገባው ውይይት እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ሐሳቦችን አንስተው መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ መጽሀፍ እነዚህን ሐሳቦች አቅፎ መያዙ ተገልጹዋል።

ይህ መጽሐፍ በቅዱስ ወንጌል ስለሚገኘው ደስታ በአጽኖት የሚገልጽ እንደ ሆነ የመጽሐፉ ደራሲ መገለጻቸው የታወቀ ሲሆን በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየታየ ያለውን ጦርነትን የማፋፋም ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ የሚተች መጽሐፍ እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የራሳቸው ምዕመናን (የካቶሊክ) ብቻ ለመሆን ሳይሆን የሚፈልጉት በአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ መሆን እንደ ሚፈልጉ የግራ ዘመም የፖሌቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆኑ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚታዩት ኢፍታዊነት፣ ራስ ወዳድነት፣ የጦር መሳሪያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉ በዓለማችን ውስጥ ከፍተኛ ስጋት እየደቀኑ የሚገኙ ክስተቶች እና ስህተቶች መቋጫ ያገኙ ዘንድ የሚሰሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳት መሆናቸውን የመጽሐፉ ጸሐፊ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ጠበት የሆኑት  ዶሜኒክ ዎልቶን የገለጹ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሊቃን ከሆኑ ሰዎች ይልቅ ተራ በሆኑ ሰዎች እንደ ሚተማመኑ ጨምሮው ገልጸዋል።

የእዚህ መጽሀፍ ጸሐፊ የሆኑት በማኅበራዊ ሳይንስ እና በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጽንሰ-ሐሳብ አፍላቂ የሆኑት ዶሜኒክ ዎልቶን በሚያዝያ 16/2010 ዓ.ም. በቫቲካን ሬዲዮ የመስብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው ለጋዜጤኞች በሰጡት መግለጫ እንደ ገለጹት ከጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2016-2017 ዓ.ም. ድረስ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት እና በተለያዩ አርእስቶች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር ለዐስራ ሁለት ጊዜያት ያህል መገናኘቱን ጨምሮ ገልጹዋል። በእነዚህ 12 ግንኙነቶች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር በያንዳንዱ ግንኙነት ከአንድ ሰዓት በላይ ውይይት ማድረጋቸውን የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር እና የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጽንሰ-ሐሳብ አፍላቂ የሆኑት ዶሜኒክ ዎልተን የገለጹ ሲሆን በግንኙነቱ ወቅት የነበሩትን ውይይቶች ያካተተ እና 250 ገጾች ያለው “ፖሌቲካ እና ማኅበረሰብ” በሚል አርእስት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም በፈረንሳይኛ ቋንቋ መጽሐፍ ማሳተማቸውን በጋዜጣዊ መገለጫው ወቅት ገልጸው ይህ መጽሐፍ በጣሊያነኛ ቋንቋ “እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” በሚል አርእስት ተተርጉሞ ለንባብ መብቃቱንም ጨምረው ገልጸዋል።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የነበረኝ ቆይታ በሳቅ የተሞላ እና በመግባባት መንፈስ የተደረገ ቃለ ምልልስ እንደ ነበረ የገለጹት የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር እና የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጽንሰ-ሐሳብ አፍላቂ የሆኑት ዶሜኒክ ዎልተን በመተማመን መንፈስ የተደርገ ውይይት እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እጅግ በጣም ሰብአዊነት የሚሰማቸው እንደ ሆኑ፣ ከቤተክርስቲያን መሪዎች እና እንዲሁም ከፖሌቲከኞች ጋር በሚደርጉ ውይይቶች ብዙን ጊዜ የማይታየው የጓደኝነት እና አካልዊ ንኪኪ ያካተተ ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹት ዶሜንክ ዎልተን በውይይቱ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “እኔ እረኛ ነኝ እንጂ ፕሮፌስር አይደለሁኝም” ይሉ እንደ ነበረ አስታውሰዋል።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር 12 ጊዜያት ያህል ተገናኝተው ካደርጉት ቃለ ምልልስ በኃላ “እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” በሚል አርእስት 250 ገጾች ያሉት መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ፈረንሳዊው የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር እና የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጽንሰ-ሐሳብ አፍላቂ የሆኑት ዶሜኒክ ዎልተን በሚያዝያ 16/2010 ዓ.ም. በሬዲዮ ቫቲካን የመሰንሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው  በይፋ ለንብባ የበቃውን መጽሐፍ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ እንደ ገለጹት “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ፣ ለድኾች እና ለኃጢያተኞች ጥብቅና የምትቆም በአጠቃላይ የወንጌል እሴቶች በተጨባጭ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን እንደ እንደ ሚሹ በተደጋጋሚ መገልጻቸውን አስታውሰዋል።

“እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” የሚለውን አርእስት ለጣሊያነኛ ትርጉም እንዲሆን የመረጡበትን ምክንያት ያብራሩት የመጽሐፉ ጸሐፊ ዶሜኒክ ዎልተን እንደ ገለጹት ግጥም ስሜትን የሚነካ፣ ምስጢራዊ የሆነ ነገር እና ጠለቅ ብሎ በመግባት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ለመመርመር መንገድ የሚከፍት በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ገልጸው በእዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ፍጹም ምናባዊ እና ሕልም የሚመስሉ ነገሮችን ተጨባጭ በሆነ መልኩ በግለጽ እንደ ሚቻል ታላቅ የሆነ እመንት ስላላቸው መሆኑን ዶመኢንክ ዎለተን ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት ቤተክርስትያን “ነጻ እና ደስተኛ” እንድትሆን  ምኞታቸው እንደ ሆነ የገለጹት ዶመኒክ ዎልተን በተለይም ደግሞ ቤተክርስትያን በሐዘን ስሜት የተሞላች ሳትሆን ነገር ግን በደስታ የተሞላ ሥፍራ ሊሆን እንደ ሚገባ አጽኖት ስጥተው ቅዱስነታቸው ይናገሩ እንደ ነበረ ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ብዙኃኑን ሕዝብ በጣም እንደ ሚወዱ፣ የሸንጎ አባላት የሚመስሉ ካህናትን እና ዓለማዊያንን የሚመስሉ ቄሳውስትን ግን እንደ ሚጠሉ” የገለጹት ዶሜኒክ ዎልተን “ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሕል ማለት አንድ የማይንቀሳቀስ ነገር ማለት እንዳልሆነ ገልጸው በአንጻሩ በሕህል እየታደሰ የሚሄድ ነገር ነው እንጂ በአንድ ቦታ ቀጥ ብሎ የቆመ ነገር እንዳልሆነ በተደጋጋሚ እንደ ገለጹ “እግዚኣብሔር ገጣሚ ነው” በሚል አርእስት 250 ገጾች ያለውን መጽሐፍ በሚያዝያ 16/2010 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት ፈረንሳዊው የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር እና የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጽንሰ-ሐሳብ አፍላቂ የሆኑት ዶሜኒክ ዎልተን ጨምረው ገልጸዋል።

 

28/04/2018 10:35