Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ከኢየሱስ ጋራ ጠንካራ የሆነ ግንኙነት የማንፈጥር ከሆንን በተለያዩ ሐሳቦች እንወሰዳለን”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከአዳዲስ ካህናት ጋር - REUTERS

23/04/2018 16:07

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ አራተኛው ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት አራተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በዓለማቀፍ ደረጃ 55ኛው ለመነፈሳዊ ጥሪ ጸሎት የሚደርግበት የመላክም እረኛ ሰንበት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህም የመልካም እረኛ ሰንበት በመባል የሚጠራው ሰንበት በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዚያ 14/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለ16 አዳዲስ ካህናት ከሰጡት የማዕረገ ክህነት በመቀጠል እንደ ተለመደው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች  በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ባሰሙት አስተንትኖ “ከኢየሱስ ግራ ጠንካራ የሆነ ግንኙነት የማንፈጥር ከሆንን የተለያዩ መንገዶችን የሚጠቁሙን አስተሳሰቦች ሰልባ እንሆናልን” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላሁ!

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 14/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕማናን እን የሀገር ጎብኚዎች ያደርጉትን የወንጌል ላይ አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

በዚህ የፋሲካ አራተኛ እሑድ ስርዓተ አምልኮ ቀን ላይ ከሙታን ከተነሳው ጌታ ጋር እኛ የእርሱ የሆንን ደቀ-መዛሙርት ማንነታችንን ለይተን እንድናውቅ ይጋብዘናል። በሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ለኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ሽባ እና ለማኝ የሆነውን ሰው የፈወሰው በኢየሱስ ስም እንደ ሆነ በመገልጽ ምክንያቱምድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና” (የሐዋሪያት ሥራ 412) በማለት ይናገራል። በእዚያ በተፈወሰው ሰው ውስጥ እያንዳንዳችን እንገኛለን- የተፈወሰው ሰው የእኛ አምሳል ነው፣፣ እኛ ሁላችን በእርሱ ውስጥ እንገኛለን-ማኅበራሰባችንም ሳይቀር በእዚያ ውስጥ ይገኛል፡ እያንዳንዱ ሰው ካለበት የተለያየ ዓይነት መንፈሳዊ ድክመቶች  የግል ምኞት፣ ስንፍና፣ ኩራት ከመሳሰሉ ነገሮች ውስጥ ለመውጣት የራሱን የመኖር ሕልውና ከሙታን ለተነሳው ጌታ በመተማመን ካስርከበው ከእነዚህ ነገሮች ሊፈወስ ይችላል።ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና’ (የሐዋሪያት ሥራ 4:10) በማለት ሐዋሪያው ጴጥሮስ ማረጋገጫ ያቀርብላችዋል። ነገር ግን ይህ የሚያድነው ኢየሱስ ማን ነው? በእርሱ መፈወስ ማለት ምን ምን ነገሮችን አጠቃሎ ይዙዋል? ከምንድነው የሚፈውሰን? በምን ዓይነት በሀርይ ነው የሚፈውሰን?

የእነዚህን ጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስእኔ መልካም እረኛ  ነኝባለበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ እናገኛለን። (ዩሐንስ 1011-18) መልካም እረኛ የራሱን ነብስ ለሌሎች አስላፎ ይሰጣል። ይህ ኢየሱስ ራሱን በራሱ ያቀረበበት አገላለጽ፣ በስሜታዊነት የተሞላ ሐሳብ ሳይሆን ግልጽ በሆነንና ተጨባጭ በሆነ መልኩ የተገለጸ ንግግር ነው! ኢየሱስ ሕይወትን የሚሰጠን እርሱ ራሱ ሕይወቱን ለእኛ አስላፎ የሚሰጥ እረኛ በመሆን ነው። ለእኛ ሲል ሕይወቱን አስልፎ በመስጠት፣ ኢየሱስ ለእኛ ለእያንዳንዳችን እንዲህ ያላልሕይወትህ ለእኔ በጣም ዋጋ ያለው ነው፣አንተን ለማዳን እራሴን እሰጣለሁ " ይለናል። ይህ ራሱን የመስጠቱ ሁኔታ ነው እንግዲህ እርሱ ከሁሉም ለየተ ያለ መልካም እረኛ መሆኑን ያሳያል፣ አዳኝ መሆኑን ያሳያል፣ ውብ የሆነ እና ፍሬያም የሆነ ሕይወት እንድንኖር የሚያስችለን እርሱ ነው።

በተመሳሳይ መልኩም በሁለተኛው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ውስጥ ኢየሱስ እኛን ሊፈውስ እና ህይወታችንን ደስተኛ እና ፍሬያማ እንዲሆን ሊያደርግ የሚችለው እንዴት እንደ ሆነ በመግለጽመልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፤ ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ” (ዩሐንስ 1011-18) ይለናል። ኢየሱስ ሰለ አንድ አእምሮኣዊ  እውቀት አልተናግረም፣ በፍጹም አለተናግረም! ነገር ግን እርሱ የተናገረው በግለሰብ ደረጃ ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንድንመሰርት እርስ በርስ የመተሳሰብ ስሜት በእሱና በአብ መካከል አንድ ዓይነት የሆነ የፍቅር ግንኙነት ነጸብራቅ እንዲኖረን ነው። ይህ ማለት ከኢየሱስ ጋር ያለን ህይወት የሚገለፅበት ባህሪ ነው፣ እርሱ በሚገባ እንዲያውቀን ለእርሱ ራሳችንን መስጠት የሚለውን ያሰማል። ራሳችንን በራሳችን ዘግተን መኖር ማለት ሳይሆን ኢየሱስ በሚገባ እንዲያውቀን ለእርሱ ራሳችንን መክፈት የገባናል ማለት ነው። እርሱ ለእያንዳንዳችን ትኩረት ይሰጣል፣ ልባችንን በጥልቀት ያውቃል፡ ድክመቶቻችንን እና ስህተቶቻችንን፣ ከእዚህ ቀደም ያከናወናቸውን መልካም ነገሮችን እና እንዲሁም በከንቱ ያለፉትን የተስፋ ጊዜያትን እርሱ በሚገባ ያውቃቸዋል። እንዲሁ እንዳለን ከእነ ሁለንተናችን ይቀበለናል፣ ከእነ ኃጢኣታችን ይቀበለናል፣ ልያድነን፣ ሊፈውሰን፣ በፍቅር ሊመራን ይፈልጋል ምክንያቱም በመንገድ ላይ ደክመን እንዳንጠፋ እና መንገዳችንን እንዳንቀይር እርሱ ከእኛ ጋር ሁሌ አብሮን ይሆናል።

እኛም በበኩላችን ኢየሱስን እንድናውቀው ተጠርተናል። ይህ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያመልክታል። እይህም በራሳችን የመመካት ዝንባሌን በመተው በአዲስ ጎዳና ላይ ለመራመድ መዘጋጀት ማለት ሲሆን ይህም ክርስቶስ በራሱ የተገለጠበት እና እርሱ ራሱ ወደ ከፈተው ስፊ አድማስ መራመድ ማለት ነው። ከኢየሱስ ጋር ያለን ግንኙነት ሲበላሽ፣ የእርሱን ድምጽ ለማዳመጥ እና ማኅብረሰቡ በታማኝነት እርሱን ለመከተል የነበረው ፍላጎት ሲቀዘቅዝ በእዚያ ስፍራ ከወንጌሉ ጋር ያልተጣጣሙ ሌሎች የአስተሳሰብና የኑሮ አመራሮች መኖራቸው የማይቀር ጉዳይ ነው። ከኢየሱስ ጋር ያለንን ግንኙነት እያጠናክረን ለመጓዝ እንችል ዘንድ እናታችን ቅድስ ድንግል ማሪያም ትርዳን። ኢየሱስ ወደ ውስጣችን እንዲገባ ራሳችንን  እንክፈትለት። ከሙታን ከተነሳው ጋር ጠንካራ የሆነ ግንኙነት እንመስርት።  በእዚህ በዛሬው እለት በምናክብረው ዓለማቀፍ ለመነፈሳዊ ጥሪ ጸሎት በሚደርግበት በዛሬው ቀን አማላጃችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ለሚያቀርብላቸው ጥሪ በጎ ምላሽ እንዲሰጡ ሁሉንም ነገር በመተው በብርታት የእርሱን መንግሥት ለመፈለግ እንዲጓዙ እንድትረዳን ልንጸልይ ያስፈልጋል።

“የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ! ይበልሽ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና!” ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት ሳምንታዊ ፣መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ቀደም ሲል ያስነበብናችሁን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚቀርቡት የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን እና በፋሲካ በዓል ሰሞን ባሉ ቀናት ውስጥ የሚደገመውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በኒካራጓ የተቀሰቀሰው የፖሌቲካ አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸው ይህ ማኅበርሰቡ በመንግሥት ላይ እያቀረበው የሚገኘው ተቃውሞ የሰው ልጆችን ሕይወት ዋጋ እያስከፈለ ያለ ሂደት በመሆኑ በተቃውሞ ሂደቱ ነብሳቸውን ላጡ ሰዎች በጸሎት እያስታወስኩኝ በእዚህ አጋጣሚ በሀገሪቷ ከሚገኙ ብጽዕን ጳጳሳት ጋር በጋራ በመሆን ይህ ደም እያፋሳሰ የሚገኘው አመጽ እና ለእዚህ አመጽ መነሻ የሆነው ጥያቄ በሰላማዊ መልኩ እና ኅላፊነት በተሞላው መልኩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

በእለቱ “ማዳመጥ፣ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ እና እግዚኣብሔር የሰጠንን ጥሪ በአግባቡ መኖር” በሚል መሪ ቃል የተከበረውን  ዓለማቀፍ የመነፈሳዊ ጥሪ ቀን ጸሎት በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በቤተ ክርስትሲያን ውስጥ ተከታታይነት ባለው መልኩ ለእርሱ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ለኢየሱስ ያላቸውን ፍቅር በመግለጽ፣ የእርሱን ክብር ከፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ እና ወንድም እህቶቻቸውን ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች አሁንም እያገኘን በመሆናችን የተነሳ እግዚኣብሔርን ማመስገን እንደ ሚገባ፣በተለይም ደግሞ በእለቱ 16 ካህናት ማዕረገ ክህነትን በመቀበላቸው እግዚኣብሔርን እናመሰግናለን ካሉ በኃላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ካሉ በኃላ ሰላምታን አቅርበው መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

23/04/2018 16:07