Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ሕይወታችንን እንደ አንድ ክርስቲያን በሚገባ ለመኖር እንችል ዘንድ መስዋዕተ ቅዳሴ መካፈል ይገባል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችነስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - AP

04/04/2018 15:28

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው ከጥር 7/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ መጋቢት 12/2010 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር ረቡዕ እለት በተከታታይ እያደርግያደርጉት የሚገኙት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ  በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዛሬው እለት በእዚሁ አርእስት ዙሪያ ባዳረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዐት ዙሪያ ላይ በማደርግ መሰረቱን በዩሐንስ ወንጌል 6:54-55 ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 26/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

በእለቱ የተነበበው ምንባብ

“በዚያኑ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርትም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው” (ዩሐንስ 20:19-20)።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ

ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ስናደርገው የነበረው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በዛሬው ቀን አስተምህሮ በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት መደምደሚያ  ላይ ባለው ስነ-ስረዓት ላይ ትኩረታችንን እናደርጋልን። የመስዋዕተ ቅዳሴ ማጠቃለያ ስነ-ስረዓት ላይ ያለው የመድምደሚያ ጸሎት ከተጸለየ በኃላ ካህኑ ምዕመኑን ከባረከ በኃላ ሕዝቡን ያሰናብታል። መስዋዕተ ቅዳሴ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ተብሎ እንደ ተጀመረ ሁሉ አሁን የቅድስት ስላሴ መገለጫ በሆነው በእዚሁ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ቡራኬን በመስጠት ይጠናቀቃል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንም በሚገባ እንደ ምናውቀው መስዋዕተ ቅዳሴ የሚጠናቀቀው ለክርስቲያናዊ ምስክርነት በር በመክፈት ነው። ከቤተ ክርስቲያን የምንወጣውበሰላም ሂዱከተባል በኃላ ሲሆን ይህም ደግሞ በእለታዊ ኑሮዋችን፣ በቤታችን፣ በሥራ ቦታችን ሁሉ የእግዚኣብሔርን ቡርኬ ይዘን በመሄድ ሲሆንይህም እግዚኣብሔርን በሕይወታችን እያከበርነው እንድንሄድ ያደርገናል። በምስጢረ ቅዱስ ቁርባን አማክይነት ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን እና በስጋችን ውስጥ ይገባል፣ ይህምበእምነት የተቀበልነው ምስጢር በሕይወታችን እንድንኖር ያስችለናል” ማለት ነው።

ስለእዚህ ከመስዋዕተ ቅዳሴ ጀምሮ እስከ ሕይወት ድረስ መስዋዕተ ቅዳሴ ምልኣትን የሚያገኘው እኛ በምናደርጋቸው ተጨባጭ ምርጫዎች ላይ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህም በቅድሚያ ከክርስቶስ ምስጢር ጋር መዋዕድን ይጠይቃል። መስዋዕተ ቅዳሴን የምንካፈልበት ዋነኛው ምክንያት እያንዳንዳችን በቅዱስ ቁርባን መንፈስ መታነጽን ለመማር መሆኑን በፍጹም መርሳት አይገባንም። ታዲያ ይህ ምን ማለት ይሆን? ይህ ማለት ክርስቶስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲንቀሳቀስ መፍቀድ ማለት ነው፣ የእርሱ አስተሳሰብ የእኛ አስተሳሰብ እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው፣ የእርሱ ስሜት የእኛ ስሜት እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው፣ የእርሱ ምርጫ ምርጫችን እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው። ይህንንም በተመለከረ ከክርስቶስ ጋር እንዴት መመሳሰል እንደ ሚገባን ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስለእግዚአብሔር እኖር ዘንድ፣ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቻለሁና። ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው” (ገላቲያ 2:19-20) በማለት ጠቅለል ባለ መልኩ ገልጾታል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ የነበረው ተመክሮ ለእኛም ብርሃን ይሆናል፣ የራስ ወዳድ ስሜታችንን ለማስወገድ በምንሞክርበት ጊዜ ሁሉ ከቅዱስ ወንጌል እና ከክርስቶስ በተቃራኒ በኩል የሚገኙ ነገሮችን እንዲሞቱ አደረግን ማለት ነው፣ ይህ ድርጊታችን ደግሞ በውስጣችን ለእርሱ መንፈስ ሰፊ ስፍራ እንድንሰጥ ያስችለናል ማለት ነው። በተባረከው እንጀራው ውስጥ በእውነት የሚኖረው እየሱስ መስዋዕተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኃላም እንኳን ቢሆን የሚቀጥል ሲሆን ቅዱስ ቁርባን ወደ መንበረ ማደሪያ ተመልሶ በመግባት ለበሽተኞች እንዲከፋፈል ይደረጋል ወይም በእዚህ በተቀደሰ ቅዱስ ቁርባን ውስጥ የሚገኘው ኢየሱስ በጸጥታ ይመለካል፣ በእዚህም አግባብ ከመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውጪ የሚገኘው የቅዱስ ቁርባን የአምልኮ ስረዓት ገላዊ በሆነ መልኩ ወይም ደግሞ ማኅበራዊ በሆነ መልኩ በመመለክ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳል።

በቅዱስ ቁርባን የሚገኘው ፍሬ በእለትዊ ሕያወታችን ውስጥ ቀስ በቀስ እየጠነከርን እንድንሄድ ያደርጋል።  በእርግጥ ቅዱስ ቁርባን ከክርስቶስ ጋር ያለንን ሕብረት እንዲጠናከር በማድረግ፣ ምስጢረ ጥምቀት እና ሚስጢረ ሜሮን በተቀበልንበት ወቅት የተቀበልነውን የመነፈስ ቅዱስ ጸጋ እንዲታደስ በማድረግ ታማኝ ክርስቲያን መስካሪዎች እንድንሆን ያደርገናል።

በተጨማሪም ቅዱስ ቁርባን በውስጣችን ያለውን መለኮታዊ ፍቅር በደንብ እንዲቀጣጠል በማድረግ ከኃጢኣት እንድንርቅ ያደርገናል፡በውስጣችን የሚቀጣጠለው የፍቅር ስሜት ቅዱስ ቁርባን ወደፊት ከሚገጥሙን ከባባድ ኃጢኣቶች ይጠብቀናል። የክርስቶስን ሕይወት ይበልጥ በተካፈልንና በወዳጅነቱም ይበልጥ በጸናን ቁጥር በክፉ ኃጢኣቶች ምክንያት ከእርሱ የምንርቅበት ሁኔታ እየጠበበ ይሄዳል (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ . 1399)

ቅዱስ ቁርባንን በማዘውተር በምንቀበልበት ወቅቶች ሁሉ ከክርስቲያን ማኅበረሰብ ያለንን ግንኙነት በማደስ ይህ ግንኙነታችን ይበልጡኑ እየጠነከረ እና ጥልቅ እየሆነ እንዲሄድ ያደርጋል በአጠቃላይ ቅዱስ ቁርባን ቤተ ክርስቲያን እንድንሆን ያደርጋል።

በመጨረሻም በቅዱስ ቁርባን ምስጢር ተካፋይ መሆን ከድኾች ጋር ያለንን ግንኙነት እንዲጠናከር ያደርጋል፣ የክርስቶስን ሥጋ ከተቀበልን ቡኃላ ለወንድሞቻችን እንድናስብ ያስተምረናል፣ በእዚህም ክርስቶስ ራሱንን እንደ ምናገለግለው፣ እንደ ምናክብረው፣ እንደ ምንወደው እንገልጻለን።

ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ የሰጠንን ጌታ እያመስገንን በታደሰ የእመነት መንፈስ ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት እንዲታደስ በማድረግ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለእኛ ሲል በሞተው እና ከሙታን በተነሳው እሁኑም ከእኛ ጋር ያለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለንን ሕብረት ማጠናከ ይገባል።   

 

04/04/2018 15:28