Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ክርስቶስ ከሙታን ተንስቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ Urbi et Orbi መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት - REUTERS

03/04/2018 10:46

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በድምቀት ተከብሮ አልፉል። በመጋቢት 23/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ የዋዜማ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት መካሄዱ የታወቀ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ባዶ የሆነውን የኢየሱስን መቃብር በማስታወስ ያለምንም ፍርሃት ጌታችን ኢየሱ ክርስቶስን መከተል ይገባናል ማለታቸው ተገልጿል። በዛሬው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው ታውቋል።

በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘ መልእክት በዓላቱን አስመልክተው እንደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ረፋዱ ላይ Urbi et Orbi በአምሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘው መልእክታቸው የሚከተለውን ብለዋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለው።

ክርስቶስ  ከሙታን ተንስቷል።

ይህ እየሱስ ከሙታን የተነሳበት እለት በመላው ዓለም በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሃሌሉያ ጌታችን ኢየሱስ ስክርስቶስ ከሙታን ተንስቷዋል፣ አባቱ የሆነ እግዚኣብሔር ከሙታን አስነስቶት ለዘለዓለም በእኛ መሐል ይኖራል የሚለው መዝሙር በታላቅ መንፈሳዊነት እይተዘመረ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሞቱ እና ስለትንሳሄው አስቀድሞ ተናግሮ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንንም “እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች’ በማለት ስለሞቱ እና ስለትንሳኤው አስቀድሞ ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህም ኢይሱስ የተናግረው ቃል በተግባር መፈጸሙን ያመለከቱት ቅዱስነታቸው እንደ አድን የስንዴ ፍሬ በመሬቱ ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል ተቀብሮ በሦስተኛው ቀን ደግሞ ሁል ጊዜም ቢሆን ከእርሱ ግራ የነበረው የእግዚኣቤር ኃይል ከሙታን እንዲነሳ እንዳደርገው እና እነሆ ዛሬ የፋሲካን በዓል በደስታ እንድናከብር ምክንያት ሆኖናል  ብለዋል።

እኛ ክርስቲያኖች ይህ የጌታችን የኢየሱ ክርስቶስ መሞት እና ከሙታን መነሳት የእኛ እና የዓለማችን እጣ ፈንታ እንደ ሆነ እኛ ክርስቲያኖች በሚገባ እንረዳለን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም የክርስቲያን ተስፋ ምንጭ ነው ብለዋል። ይህም ተስፋ የመነጨው ልክ እንደ አንድ የስንዴ ፍሬ ራሱን ለእኛ ሲል በፍቅር ዝቅ ባደረገው እና እስከሞት ድረስ ራሱን ታዛዢ ካደረገው ከጌታችን ከኢየሱስ መታዘዝ የመነጨ ኣንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ዓለም በስሙ እንዲታደስ እንደ ሚረዳ ገለጸዋል። ይህ ኢየሱስን ከሙታን እንዲነሳ ያደረገው ታላቅ ኃይል ዛሬም ቢሆን በዓለማችን ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንጸባረቁትን ኢፍትሐዊነት እና ግጭቶች መፍትሄ እንደ ሚያስገኝ እና ሁሉም የሰው ልጆች ፍሬያማ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ የገለጹት ቅዱስነታቸው መገለል እና ስቃይ በበዛበት የማኅበረሰብ ክፍሎች ውስጥ፣ በረሃብ እና በስራ አጥነት የሚጎሳቆሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ውስጥ፣ በስደት ላይ ባሉ ሰዎች ሕይወት ውስጥ፣ በአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች ምክንያት መከራ በደረሰባቸው የማኅበርሰበ ክፍሎች ውስጥ በአሁን በእኛ ዘመን በሚታየው በዘመናዊ ባርነት በሚሰቃዩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መነሳት ተስፋቸው እንዲለመልም እና ሰብዕዊ መብታቸውን እንዲጎጸፉ ማድረግ የሚችል ኃይል አለው ብለዋል።

እኛም ብንሆን ዛሬ የሰላም ፍሬ ውጤት የሆኑ ነገሮችን እንዲሰጠን እርሱን በመማጸን በተለይም ደግሞ ማብቂያ በሌለው ጦርነት እየተጎሳቆለች በምትገኘው በሶሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ከሙታን የተነሳውን ጌታ መማጸን እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ የፋሲካ ስሞን የትንሳሄው ብርሃን በፖለቲካ ኃላፊነት ላይ የሚገኙትን ሰዎች፣ በእዚህ ጦርነት ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ሕሊና ያበራ ዘንድ እና ሰብዕዊ እርዳታ ለተጎጂዎ ይደርስ ዘንድ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ቅዱስነታቸው በአደራ ጭምር ተማጽነዋል።

እንዲሁም እኛ ክርስቲያኖች  የኢየሱስን በድን ሽቶ ለመቀባት ወደ መቃብሩ በማለዳ ሴቶች በሄዱበት ወቅት “ለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ! እርሱ እዚህ የለም ከሙታን ተንስቱዋል” (ሉቃስ 24፡5-6) ብሎ መልኣክቱ ለሴቶቹ እንደ ተናገረ ሁሉ ሞት እና ፍርሃት የእኛ ክርስቲያኖች የመጨረሻ እጣ ፈንታችን እንዳልሆነ በእግዚኣብሔር ኃይል ብቻ ሊከናወን የሚችል ከሙታን የመነሳት ተስፋ እንዳለን ልንረዳ ይገባል እንጂ በፍርሃት ልንዋጥ አይገባም ብለዋል።

የእግዚኣብሔር መለኮታዊ ፍቅር  “ክፉን ነገር ማሸነፍ ይችላል፣ ኃጢእታችንን ያጥባል፣ ለኃጢያተኛው ሰው ንጽዕናን ያጎናጽፋል፣ ለተስቃዩ ሰዎች ደስታን ይሰጣል፣ ጥላቻን ያስወግዳል፣ የኃያላንን ጉልበት እንዲገዛ ያደርጋል፣ መገባባትን እና ሰላምን እንድንጎናጸፍ ያደርጋል ብለዋል።

 

 

03/04/2018 10:46