2018-04-02 13:02:00

አባ ራኒየሮ ካንታ ላ ሜሳ፣ ወጣቶች አዳኛቸው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያገኙት አሳሰቡ።


አባ ራኒየሮ ካንታ ላ ሜሳ፣ ወጣቶች አዳኛቸው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያገኙት አሳሰቡ።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስና የቅድስት መንበር የሥራ ተባባሪዎቻቸው የወንጌል ሰባኪ የሆኑት አባ ራኒየሪ ካንታ ላ ሜሳ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት አስመልክተው ባሰሙት ስብከት ሐዋርያው ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር የሄደበትን ምስጢር እና ገና ወጣት ሳለ ከኢየሱስ ጋር የነበረውን ቅርበት በማስታወስ፣ ወጣቶች ኢየሱስ ክርስቶስን በሕይወታቸው ውስጥ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

በጥቅምት ወር 2011 ዓ. ም. በሮም ሊካሄድ የታቀደው የካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤም ዋና ዓላማም ወጣቶች በእምነታቸውና በሕይወታቸው ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን ማግኘት እንዲችሉ፣ ለወጣቶች የምትሰጠውን ሐዋርያዊ አገልግሎት የበለጠ የሚያድግበትን መንገድ ከወጣቶች ጋር በመመካከር ላይ እንዳለች አስረድተዋል። የአባ ራኒየሪ የስቅለተ ዓርብ አስተንትኖ ያተኮረው በወጣቶች መንፈሳዊ እድገት ላይ እንደሆነና፣ ለዚህ ስብከታቸው መሠረት ያደረጉት የኢየሱስ ክርስቶስን የስቃይ መንገድ ከኢየሱስ ክርስቶስ እናት ጋር ከመስቀል ስር ሆኖ የተመለከተውን ሐዋርያና ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስን ጠቅሰዋል።

የፍራንችስካውያን ንዑሳን ወንድሞች ማሕበር አባል፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስና የቅድስት መንበር የሥራ ተባባሪዎቻቸው የወንጌል ሰባኪ የሆኑት አባ ራይኔሪ ካንታ ላ ሜሳ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ገና ወጣት ሳለ ከሁሉ አስቀድሞ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ፍቅር ልዩ ቦታ እንደሰጠ አስረድተዋል። ከዚህ በመነሳት በወጣቶች ጠቅላላ ሕይወት ላይ ለመወያየት የታቀደው የካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ አስፈላጊነት ገልጸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከወጣቶች ምን እንደሚፈልግ ማወቅ መልካም ነው ያሉት አባ ራይኔሪ በማከልም ወጣቶችም በበኩላቸው ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለመላው ማሕበረ ሰብ ሊያበረክቱ የሚችሉት አስተዋጽኦ ምን እንደ ሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ብለዋል። ከሁሉ አስቀድሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሟላ ደስታንና ዘለዓለማዊ ሕይወትን እንደሚሰጥ ወጣቶች መገንዘብ አለባቸው ብለዋል። አባ ካንታ ላ ሜሳ በመቀጠልም ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሊያደርግ ስልጣን ያለው፣ የሞትን ስልጣን እንኳን ቢሆን አሸንፎ የተነሳ፣ ሕያው አምላክ ነው ብለዋል። ስለዚህ ወጣቶች ኢየሱስን ወደ ራሳቸው ሕይወት ቢቀበሉት የሚሳናቸው፣ ከአቅማቸው በላይ የሚሆን ነገር የለም ብለዋል።

ሐዋርያው ዮሐንስ ወደ መቃብር የሄደበትን ምሳሌ በመከተል፣ የሐዋርያው ዮሐንስ የመጀመሪያውን መልዕክት በማስታወስ አባ ካንታ ላ ሜሳ፣ ወጣቶችን ወደ ክፋት ጎዳና ከሚመራቸው በአንዳንድ ዓለማዊ አስተሳሰብ እንዳማረኩ በማለት እንደሚከተለው አሳስበዋል። እናንተ ተቃራኒውንና የተሻለ አቅጣጫን ከሚከተሉ ሰዎች ሁኑ! ክፉን የሆነውን ለመቃወም ድፍረት ይኑራችሁ። ለእኛ ትክክለኛ መመሪያችን ቦታ ሳይሆን አምላካችን እና አዳኛችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ, ነው። በማለት አስረድተዋል።

የእግዚ አብሔር ፍቅር የጸጋ ስጦታዎችን ይሰጣል፣ ዘወትርም ሊያድነን ይፈልጋል ያሉት አባ ራይኔሪ አባ ካንታ ላ ሜሳ፣ እግዚአብሔር ለእኛ የሚሰጠን የፍቅር ስጦታ ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ከእኛ ሳይለይ በየቀኑ ሙሉ ፍቅሩን ሊሰጠንና ሊያሳየን ይፈልጋል ብለዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባሳየው ፍቅር ለእኛ ያለውን ወሰን የሌለውን ፍቅር በመግለጡ ቀዳሚ ምሳሌ ሆኖአል ብለው ይህም በትንሹም ቢሆን በሕይወታችን ውስጥ የእርሱን ምሳሌን በመከተል ለሌሎች ፍቅርን ማሳየት፣ ፍቅርን በተግባር መግለጽ ያስፈልጋል ብለዋ። በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ በቤት ክርስቲያን ቅዱሳት ምስጢራት በኩል፣ በቅዱስ ቃሉ በኩል ሊደርሰን የሚችለው፣ የእርሱን መስቀል በእምነት ዓይን በመታገዝ የተመለከትን እንደሆነ ብቻ ነው ብለዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.