2018-03-29 19:36:00

አንድ ካህን ለሕዝቡ በወንጌል አማክይነት ቅርብ ሊሆን ይገባዋል


የጎርጎሮሳዊያኑ  የቀን ቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ አሁን ያለንበት ወቅት የሕማማት ሣምንት እንደ ሆነ ይታወቃል። በእዚህ የሕማማት ሳምንት ውስጥ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስርዐተ አምልኮ ደንብ መሰረት እኛን ለማዳን እና ከእግዚኣብሔር ጋር እኛን ለማስታረቅ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበው ክርስቶስ ተላልፎ መሰጠቱን፣ መንገላታቱ፣ በመስቀል ላይ እንደ ሌባ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ መቀበሩን እና ከሙታን መነሳቱን እነዚህ ሁሉ ነገሮች የተከናወኑባቸው ሦስት ዋና ዋና ቀኖች በተለየ ሁኔታ በታላቅ መነፍሳዊነት የከበራሉ። እነዚህ ሦስት ቀኖች የሚከተሉት ናቸው።

  1. ኢየሱስ መከራውን ከመቀበሉ በፊት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን ራት ከመብላቱ በፊት የሐዋሪያቱን እግር ያጥበበት፣ እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት የጀመረውን መንፈሳዊ ተልዕኮ እንድያስቀጥሉ በማሰብ ምስጢረ ክህነትን የመሰረተበት፣ የመጨረሻ ራት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የተካፈለበት የጸሎተ ሐሙስ ማታ እለት በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
  2. በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የተፈረደበት፣ የተሰቃየበት፣ በመስቀል ላይ ተስቅሎ የሞተበት እና የተቀበረበት የስቅለተ ዐርብ እለት ይጠቀሳል።
  3. በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ኃይል ሞትን ድል አድጎ ከሙታን የተነሳበት የእለተ ሰንበት ቀን ይከበራል።

በእነዚህ የእምነታችን መሰረት በሆኑት በሦስቱ ቀናት ውስጥ በተፈጸሙት የፍቅር ምስጢራዊ ተግባራት ውስጥ ክርስቲያኖች ሁላችን ራሳችንን በማስገባት በታላቅ መንፈሳዊነት በንስሐ፣ በጾም እና እንዲሁም በጸሎት እንድንተጋ ያስፈልጋል።

ከላይ እንደ ለመጥቀስ እንደ ሞከርነው የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ በዛሬው እለት ኢየሱስ መከራውን ከመቀበሉ በፊት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን ራት ከመብላቱ በፊት የሐዋሪያቱን እግር ያጥበበት፣ እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት የጀመረውን መንፈሳዊ ተልዕኮ እንድያስቀጥሉ በማሰብ ምስጢረ ክህነትን የመሰረተበት፣ የመጨረሻ ራት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በመካፈል ቅዱስ ቅርባንን የመሰረተበት የጸሎተ ሐሙስ ቀን ዛሬ ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ እና ለምስጢረ ቀንዲል እና ለምስጢረ ክህንነት አገልግሎት የሚውል ቅባቅዱስ በመባረክ የተከናወነ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ካህናት ክህነታዊ አገልግሎታቸውን በፍቅር፣ በምስክርነት እና በምሕረት መንፈስ ማከናወን ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት (በመጋቢት 20/2010 ዓ.ም. ) በጸሎተ ሐሙስ ቀን ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ የሮም ሀገረ ስብከት ካህናት እና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሀገረ ስብከቶች የተወጣጣችሁ ካህናት!

በዛሬው እለት ስርዓተ አምልኮ የተነበቡትን ምንባባት በተለይም በኦሪት ዘዳግሞ መጽሐፍ ውስጥ በአጽኖት የተገለጸውበምንጠራው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር  ለእኛ ቅርብ እንደሆነ አማልክቱ የሚቀርቡት ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?” (. ዘዳግም 4: 7) በአእምሮዬ አንድ ነገር ትዝ እንዲለኝ አድርጎኛል። የእግዚኣብሔር ቅርብ መሆን . . . የእኛ ሐዋሪያዊ ቅርብነት።

በነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር መልእክተኛውን አስቀድሞ በሕዝቡ መካከል እንዲሆን፣ ለድሆች፣ ለታመሙ፣ ለእስረኞች ቅርብ ይሆን ዘንድቀብቶ እንደ ላከውመነፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ እንደ ሆነ እና መንፈስ ቅዱስ ወደ ፊት እንደ ሚመራው እና ከአገልጋዩ ጋር  በጉዞ ላይ አብሮት እንደ ሚሆን የሚገልጸውን መልእክት እናገኛለን።

በመዝሙረ ዳዊት በምዕራፍ 88 ላይ እግዚኣብሔር ከልጅነቱ ጀምሮ ንጉሥ ዳዊትን በእጁ ይዞት ይመራው እንደ ነበረና የእግዚኣብሔር ክንድ ሁልጊዜም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ፣ አሁን ደግሞ በስተርጅናው በሕይወቱ ሂደት ውስጥ እግዚኣብሔር ለእርሱ ቅርብ እና ታማኝ በመሆኑ የተነሳ እርሱም በስተእርጅናው ታማኝ የሚለውን መጠሪያ ለማግኘት ችሉዋል።

በዩሐንስ ራዕይ ላይ ደግሞ ከጌታ ጋር ተጨባጭ ግለሰባዊ የሆነ ቅርበት በመፍጠር ከእርሱ ጋር ሕብረት እንድንፈጥር ይጋብዘናል። "እርሱን የሠቀሉትም እንኳ" ሳይቀር እርሱን እንደ ሚያዩት የሚያመለክተው የትንሳኤ ጌታ ቁስሉ ምንጊዜም የሚታይ እንደሆነ እንዲሰማን ያደርገናል፣ እኛ ለእርሱ ቅርብ ለመሆን በምንፈልግባቸው ጊዜያቶች ሁሉ እርሱ እኛን ሊገናኘን እንደ ሚመጣ፣ በሥጋዊ ቁስል ለሚሰቃዩ በተለይም ለሕጻናት ቅርብ ለመሆን ሁሌም እንደ ሚመጣ ይገልጽልናል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በማዕከላዊነት የተገለጸው ከጌታ ጋር የነበሩ ሰዎችትኩር ብለው እርሱን ይመለከቱ እንደ ነበረ” (ሉቃስ 4:20) የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናሰላስላለን። ኢየሱስ በናዝሬት በሚገኘው ምኩራቦች ውስጥ ለማንበብ ተነስ። የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል”(ኢሳያስ 611) ንባቡን ያጠቃለለው ይህ ቃል እርሱን የሚያመለክት እንደ ሆነ በመግለጽእርሱም፣ “ይህ በጆሮአችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” (ሉቃስ 421) ይላቸው ጀመር።

ኢየሱስ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመክፈት አንድ የሕግ መምህር ማንበብ ጀመረ። እርሱ አንድ የሕግ መምህር ወይም የሕግ ጸሐፊ የመሆን ችሎታ ነበረው ነገር ግን እርሱወንጌላዊመሆን ፈለገ፣ በእየመንገዱ የተዘዋወረ የሚሰብክ ሰው መሆን ፈለገ፣ ነብዩ ኢሳያስ (52:7) እንደ ገለጸው በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራች ይዘው የሚመጡ እግሮች፣እንዴት የሚያምሩ ናቸው? እንዳለው ሁሉ ኢየሱስምመልካሙን ዜናለሕዝቡ እየተዘዋወረ መስብከ ፈለገ።

ይህ የእግዚአብሔር ምርጥ የሆነ ምርጫ ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ቅርብ የሆነ ሰው እንዲሆን መርጦታል። ሠላሳ አመታት የተደበቀ ሕይወት! ከዚያ በኋላ መስበክ ይጀምራል። ቃል ሥጋ የሆነበትን ምስጢር የማስተማር ዘዴ፣ በሕልን በማዋዕደ የማስተማር ዘዴ፣በእያንዳንዳችን ቁምስናዎች ውስጥ፣ አሁን ባለው በወጣቱ ትውልድ ብሕል ውስጥ ዘልቆ የሚገባ የማስተማር ዘዴ።

ለሰዎች ቅርብ መሆን ከአንድ የተወሰነ በጎነት በላይ የሆነ ተግባር ነው፣ ይህም በአጠቃላይ የግለሰብን፣ ከእርሱ ጋር ግንኙነት የመፍጠሪያ ሁኔታውን፣ በተመሳስይ መልኩም እርሱ በራሱ መንገድ ላይ በቀጣይነት የሚጓዝ እና ለሌላ ሰው ትኩረት የመስጠት ባሕሪን ያጠቃልላል። ብዙን ጊዜ ሰዎች አንድካህንለሕዝቡ ቅርብ መሆኑን በሚገልጹበት ወቅት ሁለት ነገሮች ላይ ተመስርተው ነው፣ በቅድሚያእርሱ በፍጹም በቦታው ተገኝቶ አያውቅም፣ እንዲያውም አንዳንዴአባ እርሶ እኮ በጣም በሥራ የተወጠሩ ሰው ስለሆኑ በፍጹም በሥራዎ ቦታ አይገኙምከሚለው በተቃራኒው የሚገኘውሁል ጊዜም በቦታው ይገኛልየሚለውን የሚያሰማ ሲሆን ሁለተኛው አግሞ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሆን ቃል እንዴት መናገር እንደ ሚገባው የሚያውቅከሁሉም ጋር የሚነጋገር፣ ከትላልቆች፣ ከትናንሾች፣ ከድኾች እምነት ከሌላቸው ሰዎች ጋርም ሳይቀር የሚነጋገር ሰው የሚለውን ያሰማል፣ ቅርብ የሆኑ ካህናት ማለት ከሁሉም ጋር መግባባት፣ መነጋገር የሚችሉ፣ በየመንገዱ እየተዘዋወሩ ከሰዎች ጋር የሚገናኙ ካህናት ማለት ነው።

በመንገድ ላይ ቅዱስ ወንጌልን እንዴት መስበክ እንደ ሚገባ ከኢየሱስ ከተማሩ ሰዎች መካከል ፊልጶስ አንዱ ነበር።በየከተማው እየተበታተኑ  በሄዱበት ሁሉ ቃሉን እና መልካም የሆነውን ዜና ሰበኩ፣ ከዚህ የተነሣም በከተማዪቱ ታላቅ ደስታ ሆነ” (የሐ.ሥራ 8:4-8) በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ስብከተ ወንጌል ካደርጉ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ፊልጶስ ነበር፣ መነፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ ወንጌልን እንዲሰብክ ወደ መራው ወደ ማንኛውም ሥፍራ በመጓዝ ይሰበክ ነበር፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላም ይዘዋወር ነበር፣ የንግሥቲቷ ቧለሟል የነበረውን ኢትዮጲያዊውን ጃንደረባ እንዳጠመቀ ሁሉ መልካም ፈቃድ እና መልካም የሆነ እምነት ያላቸውን ሰዎች እይተዘዋወረ፣ መነፈስ ቅዱስ በሚመራው ሥፍራ ሁሉ እየተገናኘ መንገድ ለመንገድ እየሄደ ያስተምር ያጠምቅም ነበር (የሐ. ሥራ 85. 36-40)

ለሕዝቡ ቅርብ መሆን ቅዱስ ወንጌልን በማወጅ ሂደት ውስጥ በጣም ወሳኝ የሚባል ቁልፍ የሆነ ሚና ይጫወታል። ለሕዝቡ ቅርብ መሆን ምሕረትን በመስገኘት ሂደት ውስጥ ቁልፍ የሆነ ሚና ይጫወታል፣ ምክንያቱም ርቀትን ለማስወገድመልካም ሰው እንደ ነበረው ሳማሪዊለሕዝቡ ቅርብ በመሆን ምሕረትን ማስገኘት ይገባል። ለሕዝቡ ቅርብ መሆን እውነትን ለማግኘት ቁልፍ የሆነ ሚና እንዳለው መገንዘብ እንዳለብን አማናለሁ። በእውነት አማካይነት ርቀትን ማስወገድ ይቻላል ወይ? አዎን በሚገባ ይችላል። እንደ እውነቱ ከሆነ እውነት ማለት አንድን ሁኔታን ለመግለጽ የምንጠቀምበት እና ቦታዎችን እና ርቀቶችን ለመጥቀስ ምክንያትዊ በሆነ መልኩ የምንጠቀምበት ትርጉም ማለት ብቻ አይደለም። ይህ ብቻ አይደለም። እውነት ማለት ታማኝ መሆን ማለት ጭምር ሲሆን ይህም ጌታ እንዳደረገው የሰዎችን ነባራዊ ሁኔታ ሳንመለከት እያንዳንዱን ሰው በየስማቸው መጥራት መቻል ማለት ነው።

የተወሰኑ ተጨባጭ እውነቶችን ብቻ እንደ ጣዖታት አድርገን የመሥራት ፈተና ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ አለብን። እነሱ ትልቅ ክብር እና ኃይልን የሚሰጡ እና ለመገንዘብ አስቸጋሪ የሆኑ ምቹ፣ ጣፋጭ ጣዖታት ናቸው። "እውነተኛው ጣዖት" በስውር የወንጌልን ቃላት እንደ ልብስ እንድንለብስ በማድረግ የወንጌል ቃላት ልብን እንዳይነኩ ያደርጋል። እናም ከእዚህ የከፋ ጉዳይ ደግሞ ተራው ሕዝብ ከቃሉ እና ከክርስቶስ ምስጢራት እንዲርቅ በማድረጉ ላይ ነው፣ የከፋውም ጉዳይ ይህ ነው።

በእዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ ከሆንን ደግሞ የካህናት እናት ወደ ሆነችው ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መመልከት ይኖርብናል።አንድ እውነተኛ የሆነች እናት፣ ከእኛ ጋር አብራ የምትጓዝ እናት፣ ከእኛ ጋር ሆና የምትታገል እናት፣ያለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለእኛ ቅርብ ይሆን ዘንድ የምታግዘን እናትየሆነችውን ማሪያም " “የቅርብ እናታችንብለን ልንጠራትም እንችላለን፣ በእዚህም መልኩ ማንም ሰው ከእዚህ ውጪ ሳይሆን ለእርሱ ቅርብ እንዲሆን ማድረግ ትችላለች። የእኛ እናት በዚህ "እንክብካቤ" አማካኝነት እኛ ወደ አገልግሎት እንድንቀርብ ብቻ የምታደገን ሳይሆን ነገር ግን በተጨማሪም በእዚሁ ተመሳሳይ ቅርበት ወደ ሕዝቡ እንድንቀርብ እና ነገሮችን በቅርበት መናገር እንድንችል ትረዳናለች። በቃና ዘገሊላ የሰርጉ ግብዣ ላይ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜእርሱ የሚላችሁን አድርጉያለችበት ቋንቁ ትልቅ አብነት በመሆኑ የተነሳ የቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ሁኖ ቀርቱዋል። ነገር ግን እንደ እሷ ለመናገር ፀጋን ከመጠየቅ በተጨማሪ አስፈላጊዎቹን ነገሮች "እያንዳንዳችን" ለእያንዳንዱ ልብ፣ ቤተሰብ፣ ሁሉንም ባሕል ከግምት ያስገባ ቅርበት ልንፈጥር ይገባል። በዚህ ዓይነት አቀራረብ ብቻ ነው  አንድ ሰው ምን እንደሚጎድለው እና ጌታ ሊሰጠው ከሚገባው ነገሮች ውስጥ አስፈላጊ እና መልካም የሆነው የቱ እንደ ሆነ መለየት የሚቻለው ለሕዝቡ ቅርብ ሲንሆን ብቻ ነው።

በመቀጠልም ክህነታዊ ቅረበት መፍጠር የሚያስችላችሁን ሦስት ቃላት ወይም ሀረጎችን ለመጠቆም እፈልጋለሁኢየሱስ የሚላችሁን ነገሮች ሁሉ አድርጉይህንንም በተለያዩ ከሺ በላይ በሚቆተሩ መነገዶች ለማስተጋባት የምትችሉ ሲሆን ነገር ግን በእዚህ አግባብ ትኩረት ማድረ የሚገባችሁ የምታናግሩትን ሰው ልብ በሚነካ መልኩ በእናትነት ባሕሪይ የተሞላ ንግግር፣ በመንፈሳዊ ሕይወት በሚደርገው ጉዞ አብራችሁ በመጓዝ በንስሓም ይሁን በስብከተ ወንጌል ተግባራችሁ ሁሉ ለሰዎች ቅርብ ሁኑ።

የመጀመሪያው ሰዎችን በመንፈሳዊ ውይይቶች አማካይነት መቀረብን በተመለከተ ጌታ ራሱ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር አድርጎት የነበረውን ውይይት ማስላሰል እንችላለን። ጌታ በቅድሚያ ይህቺን ሳማሪዊ የሆነች ሴት በመንፈስ እና በእውነት እንዴት ማምለክ እንዳለባት አስተማራት፡ ከእዚያም ቀስ በቀስ ለሰራችው ኃጢኣት መጠሪያ ሰጠ፣ በስተመጨረሻም በእርሱ ስብከተ ወንጌል መንፈስ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ ወደ መንደሩ ሂዳ በመደሩ ለሚገኙ ሰዎች ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ በሄደችበት ወቅት በመንፈስ አብሩዋት ሄደ። ይህ ጌታ ያሳየን መነፍሳዊ ውይይት ተምሳሌት የሳምራዊቷን ኃጢአት በማጋለጥ በእርሷ አምልኮ ላይ ጥላ አላጠላም፣ በእርሷ የስብከተ ወንጌል ተልዕኮም ላይ ተጽኖ አለፈጠረም ነበር።

በሁለተኛ ደረጃ በምስጢረ ንስሓ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መቀረብን በተመለከተ ደጎም ስታመነዝር የተገኘችሁን ሴት ታሪክ ላይ ማሰላሰል እንችላለን። በእዚህም ረገድ የሚደረገው ቅርበት በጣም ወሳኝ የሚባል ቅርበት ሲሆን በኢየሱስን  ፊት ቀርበው ሁል ጊዜ እውነቱን መናገር በጣም ወሳኝ እንደ ሆነ በግልጽ ያሳያል። ስታመንዝር የተገቸውን ሴት በኢየሱስ በፊቱ አምጥተው ባቆሙበት ወቅት ተንበርክኮ ወይም ቁጥት ብሎ ከነበረበት ቦታ ተነስቶ በመቆም ፊት ፊቷን ከተመለከተ በኃላእኔም አልፈርድብሽም” (ዩሐንስ 8:11) እንዳለት ሁሉ የሌሎችን ፊት መመልከት ያስፈልጋል፣ ይህም ሕግን ማፍረስ ማለት አይደለም። ነገር ግን በእዚህ ላይከእዚህ በኃላ ደግመሽ ኃጢኣት እንዳትሰሪማለት ግን የሚቻል ሲሆን ይህንን የምናደርገው ልክ በአንድ ፍርድቤት እንደ ሚደርገው ዓይነት ኃይል በተቀላቀለው ድምጽ ማድረግ ሳይሆን የሚጠበቅብን ነገር ግን የድምጻችን ኃይል የእግዚኣብሔርን መለኮታዊ ምሕረት በሚያንጸባርቅ መልኩ ሊደርገ ይገባዋል፣ ሰዎችን በእውነት ወደ እመንት የሚያመጣ ሊሆን ይገባዋል፣ ይህም ኃጢኣተኛውን ሰው ማትረፍ ይችላል።  ትክክለኛው የድምጽ አወራረድ በመጠቀምበድጋም ኃጢኣት አትሥራየሚለው ቃል አንድ ምስጢረ ንስሓ የሚያስገባ ካህን ሰባ ጊዜ ሰባት ጊዜ በመደጋገም የሚለው ቃል ሊሆን ይገባዋል።

ሦሰትኛው እና የመጨረሻው በስብከተ ወንጌል አማክይነት ሕዝቡን መቅረብ የሚለው ነው። ይህንን በተመለከተ ደግሞ በበዓለ ጴንጤ ቆስጤ ወቅት የተደርገውን የመጀምሪያውን የሐዋሪያው ጴጥሮስ ስብከት ላይ ማሰላሰል ይገባል። ሐዋሪያ ጴጥሮስ የእግዚኣብሔር ቃልየተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ጌታ አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው፣ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነውና”(የሐዋሪያት ሥራ 237) በማለት እና ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነክቶ፤ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት፣ወንድሞች ሆይ፤ ታዲያ ምን እናድርግ?” ብለው እስኪጠይቁ ድረስ ኃይል የነበረው ስብከተ ወንጌል ነበር። ይህም በሕዝቡ የተነሳው ጥያቄ ነገሮችን እንዴት እንደ ምንገልጽ፣ ነገሮችን እንዴት እንደ ምናከናውን እና ለምን ዓይነት ጥያቄ ምን ዓይነት መልስ መስጠት እንደ ሚገባን በሚገባ በመጥቆም ሁሉም ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድናመራ ማድረግ የሚችል እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል። ስብከተ ወንጌል በጣም ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን ይህም አንድ ካህን ለእዝቡ ምንኛ ቅርብ መሆኑን እና አንድ ካህን ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበት ወሳኝ የሆነ የመገናኛ መስመር ነው። በስብከተ ወንጌል ውስጥ እኛ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ምን ያህል እንደቀረብን እና በሕዝባችን እለታዊ ኑሮ ውስጥ ምን ያህል ቅርብ መሆናችንን እናያለን።

አንድ ካህን በማንኛውም መስፈርት ለሕዝቡ ቅርብ ሊሆን ይገባዋል፣ በሕቡ መካከል ሊጓዝ ይገባዋል፣ መልካም እረኛ ያልውን ዓይነት ርኅራኄ ሊኖረውም ይገባል፣ ሕዝቡም ይህንን በሚመለከትበት ወቅት አንድ ለየት ያለ ነገር እንዳለ ይገነዘባል፣ በካህኑ ውስጥ ኢየሱስ እንደ ሚገኝ ሊመለከት ይችላል።

ቅርብ እንድንሆን የምትረዳንእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምን ለእኛ ሁል ጊዜ ቅርብ እንድትሆን እናኢየሱስ የሚለንን ነገር ሁሉ በተግባር ላይ እንድናውል እንድትረዳን በልዩነታችንም ውስጥ ሳይቀር ለሰዎች ቅርብ መሆን የምንችልበትንእንደ እርሷ እንዳልከኝ ይሁንልኝ! ማለት እንድችል እና ሁሌም ቢሆን ለእየሱስ ቅርብ መሆን እንችል ዘንድ በአማላጅነቷ እንድትረዳን ልንማጸናት ይገባል።








All the contents on this site are copyrighted ©.