Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “እኛ ዳግም እንድንወለድ የሚያደርገው ኢየሱስ ብቻ ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - AP

28/03/2018 15:18

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 19/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ በአሁኑ ወቅት የሕማማት ሣምንት በታላቅ መነፈሳዊነት እያከበሩ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ኢየሱስ በእዚህ ምድር በነበረው ቆይታ ላይ የገጠመውን መከራ፣ ሞት እና ከእዚያም መቀበሩን እና ከሙታን መነሳቱን በምያመልክቱ ሦስት ቀናት ማለትም ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻ እራት የበላበት የእለተ ሐሙስ ምሽት፣ በመስቀል ላይ የተቸነከረበት የስቅለተ ዐርብ እለት እና ከሙታን የተነሳበት የእለተ ሰንበት እለት በእነዚህ ቀናት ውስጥ በኢየሱስ ላይ የተፈጸሙትን ተግባራት በማንሳት ሰፋ ያለ አስተምህሮ ማድረጋቸው ታውቁዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 19/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶአልና። ስለዚህ በዓሉን ግፍና ክፋት በሞላበት እርሾ፣ በአሮጌ እርሾ ሳይሆን፣ እርሾ በሌለበት ቂጣ በቅንነትና በእውነት እናክብር” (1ቆሮንጦስ 5:7-8)

የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በአመት ውስጥ ከሚገኙት ስርዓተ አምልኮዎች መካከል በጣም አስፈላጊ የሆነውን እና እኛን አማኞችን በቀጥታ የሚመለከተውን በእዚህ የሕማማት ሳምንት ውስጥ የሚገኙትን ኢየሱስ ስቃይ የተቀበለበትን፣ የሞተበትን እና የተቀበረበትን እንዲሁም ከሙታ የተነሳበትን ሦስት ቀናት ላይ ያተኮረ አስተምህሮ ላምድረግ እወዳለሁ። እነዚህም ቀናት የእየሱስን መሞት እና ከሙታን መነሳት በማስታወስ አንድ ታላቅ የሆነ ምስጢራዊ ትውስታን ይፈጥራሉ። እየሱስ መከራን የተቀበለበት፣ የሞተበት እና የተቀበረበት ከሙታን የተነሳበት ሂደት የሚጀምረው ከደቀ- መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻ እራት ከበላበት በጸሎተ ሐሙስ ማታ” የሚጀምር ሲሆን በእለተ ሰነበት ቀን በሚደርገው የማታ ጸሎት ይጠናቀቃል። እነዚህ ቀናት በዓለም ውስጥ የእኛን እምነት እና ጥሪ ዋና ዋና ደረጃዎችን የሚያመልክቱ ሲሆኑ ሁሉም ክርስቲያኖች እነዚህን ሦስት በጣም ቅዱስ የሆኑ ቀናትን አይሁዳዊያን ወንድሞቻችን ከግብፅ ባርነት የወጡበትን የስደት ጉዞ በማስታወስ በግለሰብ ይሁን በማኅበረሰብ ደረጃ እነዚህን ቀናት ለመኖር በመሞከር የሕይወታችን መገለጫ ቀናት ልናደርጋቸው የገባል።

እነዚህን ሦስት ቀናት ማለትም የጸሎተ ሐሙስ ማታ፣ ኢየሱስ የተሰቀለበት የዐርብ እለት እና ከሙታን የተነሳበት የሰንበት ቀናት በክርስቶስ አማክይነት የተከናወኑትን ታላክ የድኅንነት ክንውኖችን የክርስቲያን ማኅበረሰቡ በማስታወስ እና የወደፊት እጣ ፈንታቸውን በማየት በታሪክ ውስጥ ይህንን በቁርጠኝነት ለመመስከር የሚበረታቱበት ወቅት ነው።

በእነዚህ  ሦስቱ ቀናት  ማለትም ኢየሱስ መከራን የተቀበለበት፣ የሞተበት እና ከሙትና የተነሳበት በእነዚህ ሦስቱ ቀናት ውስጥ በቀደም ተከተል የተከናወኑ ድርጊቶች በፋሲካ እለት በማለዳ “ተስፋችን የሆነው ክርስቶስ ከሙታን ተንስቱዋል፣ በገሊላ ይገኛል” በማለት በሚታወጀው የደስታ አዋጅ ይጠናቀቃል። ይህም አዋጅ  የደስታና የተስፋ መግለጫ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በተጨማሪም  ኃላፊነትን እና ተልዕኮን ያመላክታሉ። ይህ ትዕዛዝ እርሱን እንድንቀበለው በማዘጋጀት የሚመራን፣ የእምነታችን ማዕከል እና ተስፋችን የሆነ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ያለማቋረጥ ስብከተ ወንጌልን ለማድረግ የተሰጣትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባት የሚያሳይ ነው።

ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ በትንሳኤ ወቅት የተፈጸሙትን ድርጊቶች ጠቅለል ባለ ሁኔታ “የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶልናል” (1ቆሮ. 5፡7) በማለት ገልጾታል። ስለእዚህ “አሮጌ የሆኑ ነገሮች አልፈዋል እንዲሁም አዳዲስ የሆኑ ነገሮች ተወልደዋል” በማለት ያክልበታል። በሌላ ዘይቤአዊ አቀማመጥ ደግሞ ክርስቶስን “እርሱ ስለ ኃጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ” (ሮሜ 4፡25) በማለት ጨምሮ ያብራራልናል። በእነዚህ ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት፣ በተስቃየበት፣ በተሰቀለበት፣ በሞተበት እና ከሙታን በተነሳበት ሦስት ቀናት ውስጥ የተከናወኑ ነገሮች የእዚህ መሰረታዊ ክስተት ትውስታ በምስጋና የተሞላ እና በተመሳሳይ መልኩም “እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ፤ አሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን” (ቆላሲያስ 3:1-2) በማለት የተጠመቁ ክርስቲያኖች አዲስ በሆኑ ሁኔታዎች በመታደስ መኖር እንደ ሚገባ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ያሳስባል። በእርግጥ በጥምቀት ከኢየሱስ ጋር ከሞት ተነስተናል፣ ዓለማዊ ለሆኑ ነገሮች እና ለዓለማዊ ምክንያቶች ያለን ፍላጎት ሞቶዋል፣ እንደ አዲስ ፍጡር በድጋሚ ተወልደናል፣ ይህም በየቀኑ ተጨባጭ እልውናችን እንዲሆን የሚጠበቅ እውነታ ነው።

አንድ ክርስቲያን በእውነት ክርስቶስ እንዲያነጻው ቢፈቅድለት፣ በእውነት ያረጀውን ማንነቱን ኢየሱስ አውልቆ እንዲጥል በመፈቀድ በአዲስ የሕይወት ጎዳና ለመራመድ ቢፈልግ መልካም ነው፣ ኃጥኣተኛ ሆኖ መኖሩን ቢቀጥል ግን ትክክለኛ ሰው ሊሆን አይገባውም፣ ከአሁን በኋላ በሞቱ ከነፍስ ጋር መኖር አይችልም፣ ይህም የሞቱ መንስሄ ሊሆን ይችላል። ባልንጄሮቻችን፣ በተለይም ደግሞ አነተኝ የሚባሉ እና በስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ለእኛ መስዋዕት በመሆን ያሳየውን የፍቅር ፊት እኛም ለእነርሱ ልናሳያቸው ይገባል። ይህንን ብናደርግ ደግሞ ዓለም የአዲሱ ህይወታችን ትንሳኤ መኖሪያ ወደ መሆን ይቀየራል። ዛሬ ልክ እንደ ኢየሱስ የተዋራዱ፣ የተሰቃዩ፣ እርቃናቸውን የቅሩ፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ፣ በብቸኝነት ውስጥ የሚኖሩ፣ በሞት ጥላ ሥር የሚገኙ ሰዎችን ስቃይ በመጋራት ይህ ስቃያቸው ለእርሱ እና ለእርሱ ብቻ ምስጋና ይደረሰውና ከእዚህ ዓይነት ችግሮቻቸው እንዲላቀቁ የመዋጃ እና የተስፋ መሳሪያዎች የሕይወት እና የትንሳኤ ምልክቶች መሆን ይኖርብናል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህን አሁን እጅግ በጣም የቀረበውን የክርስቶስ መስቃየት፣ መሞት ከሙታን መነሳት የምናስታውስበት ሦስት ቀናት በእነዚህ ቀናት ቅዱስ በሆነ መልኩ በጥሩ ሁኔታ ለመኖር እንዘጋጅ፣ ለእኛ ሲል በሞተው በክርስቶስ ምስጢር ውስጥ ራሳችንን በጥልቀት እንዲገባ እንድርግ፣ እርሱ የሞተው እና ከሙታን የተነሳው ለእኛ ነውና።በእዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ በጥልቀት ገብተን መጓዝ እንችል ዘንድ ቅድስት ድንግል የሆነችው እና ኢየሱስን በመከራው ጊዜ ሁሉ የተከተለችው፣ በመስቀሉ ሥር የነበረች እና የእርሱ ስቃይ ተካፋይ የነበረች፣ በእናቱ ልብ ውስጥ የትንሣኤን ታላቅ ደስታ ማግኘት እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ታግዘን። በመጪው ቀናት በሚከበሩት በዓላት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተካፍይ መሆን እንድንችል እንድትረዳን እና ይህም ልባችን እና ሕይወታችን ይለወጥ ዘንድ ምክንያት እንዲሆን እርሱ ትርዳን።

28/03/2018 15:18