2018-03-27 15:21:00

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ የግብጽ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን አሳሰቡ።


የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ፣ የአገራቸው ሰላም ለዓለም ሰላም ዋስትና እንደሚሆን ገልጸዋል።

ፓትሪያርክ ታዋድሮስ 2ኛ፣ ሕዝቡ ለምርጫው የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ፣ ሰላማዊ እንዲሆን ጥረት እንዲያደርጉ  ተማጽነዋል። ከትናንት ጀምሮ የሚካሄደው የምርጫ ሂደት እስከ ረቡዕ ድረስ የሚቆይ እንደሆነ ታውቋል።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ባሁኑ ወቅት የግብጽ የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ ከሁለት ቀን በፊት የቦምብ ፍንዳታዎች በአንዳንድ የሃገሪቱ ከፍሎች ተሰምተዋል ተብሏል። በአሌክሳንድሪያ ከተማ የጸጥታ አስከባሪ ዋና አዛዥን ጭኖ በሚጓዝ ላይ ባለ ተሽከርካሪ አጠገብ ቦምብ መፈንዳቱ ተነግሯል። የምርጫውን ሂደት ሰላማዊና የተረጋጋ ለማድረግ እንዲቻል በሃገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች የጸጥታ አስከባሪዎች መሰማራታቸው ታውቋል። የካይሮ አውራ ጎዳናዎች የምርጫ ዘመቻን በሚያካሂዱ የተወዳዳሪ ምስሎች  የተሞላ እንደሆነ ሲነገር፣ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት አብድ አል ፋታሕ አል ሲሲ ምስልም ከ2010 ዓ. ም. ጀምሮ በየጎዳናዎች እና በየአደባባዮች ተሰቅሎ ይታያል ተብሏል። ፕሬዚዳንቱ ለሁለተኛ ዙር የሚወዳደሩ መሆናቸው ሲነገር፣ በዚህ የምርጫ ዘመቻ የሚወዳደሯቸውን ተፎካካሪዎች አብላጫ ድምጽን በማግኘት እንደሚያሸንፏቸው ይጠበቃል ተብሏል።

በግብጽ የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግብጻውያን ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹበት መንገድ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ ብጹዕ ፓትሪያርክ ታውድሮስ 2ኛ ገልጸዋል። የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሃገሩ 93 ሚሊያን ሕዝብ መካከል 10 ከመቶ እንደሆነ ታውቋል። ፓትሪያርክ ታዋድሮስ 2ኛ፣ ሲር ከተባለ የቤተ ክርስቲያን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሳቸው፣ የግብጽ ሕዝብ በምርጫው ሂደት እንዲሳተፍ አሳስበዋል። አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት አብድ አል ፋታሕ አል ሲሲ፣ በሕዝቡ ዘንድ ትልቅ ፍቅርና ተቀባይነት እንዳላቸው ገልጸው፣ ግብጽን እያስጨነቁ የሚገኙ ሁለት ፈተናዎች እንዳሉ እነርሱም ሽብርተኝነትንና አመጽን መዋጋት ሲሆን  ቀጥሎም በሃገሪቱ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን የልማትና የግንባታ ሥራዎችን በተገቢ መልኩ ወደ ፊት ማስቀጠል እንደሆነ መግለጻቸውን ሲር የተባለ የቤተ ክርስቲያን የዜና አገልግሎት ገልጿል።          

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.