Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ወጣቶች ያላቸውን ክሕሎት ተጠቅመው ዓለምን ማገልገል ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ወጣቶች ያላቸውን ክሕሎት ተጠቅመው ዓለምን ማገልገል ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገለጸ። - AP

24/03/2018 16:18

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደረው እና ኦፑስ ዴይ በማባል የሚታወቀው መንፈሳዊ ማኅበር በዓለም ዙሪያ በርካታ የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲዎች ያሉት መንፈሳዊ ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በኦፑስ ዴይ ማኅበር ጥላ ሥር የሚተዳደሩ ዩኒቬርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ 2500 ያህል ተማሪዎች ከነገ ከመጋቢት 16/2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሮም ከተማ የሚጀመረውን 50ኛው የኦፑስ ዴይ ዩኒቬርሲትይ ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ ለመሳተፍ በሮም እንደ ሚገኙ ተገለጽ።

በእዚህ 50ኛው የኦፑስ ዴይ ዩንቬርሲቲ ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ ከመላው ዓለም ለተውጣጡ 2500 ተማሪዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ይህ እነርሱ ከመጪው እሁድ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል የሚያድርጉት ጉባሄ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ የሕማማት ሳምንት እንደ ሆነ በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው እነዚህ ወጣት የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች በእዚሁ በተቀደሰው የሕማማት ሳምንት የሚያድርጉት 50ኛው ዓለማቀፍ ጉባሄ “ስለወደፊቱ ጊዜ በጥልቀት” ማሰብ እንደ ሚገባቸው ቅዱነታቸው አሳስበዋል።

“በእግዚኣብሔር ፍቅር ተሞልታችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን እና ወደ ዘላለማዊ ከተማ ኑ” በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ በእዚህ ቅዱስ በሆነው በሕማማት ሳምንት ከእናንተ ጋር ተገናኝቼ መወያየት በጣም መልካም የሚባል አጋጣሚ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጣችሁ እና የተለያየ ዓይነት ባሕል ያላችሁ፣ ነገር ግን በደስታ፣ በምልኣት እና በልግስና ላይ የተመሰረተ አንድ ዓላማ ያንገባችሁ በመሆናችሁ የተነሳ ከእናንተ ጋር መገናኘት መልካም የሆነ አጋጣሚ ነው በለዋል።

ይህ የኦፑስ ዴይ ያዘጋጀው 50ኛው ዓለማቀፍ የኦፑስ ዴይ ዩኒቬርሲቲ ጉባሄ የሚካሄደው በእዚሁ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በያዝነው በ2018 ዓ.ም መሆኑን በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህም በመጪው ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ከሚካሄደው 15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በሚካሄድበት ዓመት የሚካሄድ ጉባሄ በመሆኑ እና ይህ ሲኖዶስ “እምነት፣ ወጣቶች እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ወጣቶችን የተመለከቱ ሐሳቦች በስፊው የሚንጸባረቁበት በመሆኑ የተነሳ ከመጭው እሁድ ጀምሮ የኦፑስ ዴይ ማኅበር በዘጋጀው 50ኛው ዓለማቀፍ ጉባሄ ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች ለእዚሁ ሲኖዶስ የራሳቸውን አስተዋጾ ከወዲሁ እንዲያደርጉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በእዚህም መሰረት ወጣቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ኢየሱስ በጣም ይወደው የነበረው እና በመጨረሻው ሰዓት ኢየሱስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት እናቱን ማሪያም በአደራ ወደ ሰጠው የኢየሱስ ተወዳጅ ደቀ መዝሙር ወደ ነበረው ዩሐንስ ወጣቶች መመልከት እንደ ሚኖርባቸው በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እርሱም በሕይወታችሁ ውስጥ እያለፈ የሚገኘውን ኢየሱስን እንዴት ለማወቅ እንደ ምትችሉ እና "ልባቸውን ከኢየሱስ ጋር የምያገናኙ  ሰዎች ህይወት የሚሞላውን ተስፋ እና ደስታ ተከትሎ የሚመጣውን መልካም ሕይወት ማግኘት እንድትችሉ እንዲያስተምራችሁ የኢየሱስ ተወዳጅ ደቀ መዝሙር የነበረውን ዩሐንስን ልትመለከቱ ይገባል ብልዋል።

ጌታ እኛን ሁላችን እርሱን እና ወንድሞቻችንን በምልኣት በመውደድ እንድንከተለው ይጠራናል በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ክርስቶስን መፈለግ፣ ክርስቶስን ማግኘት እና ክርስቶስን መውደድ ይኖርብናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ከነገ ከመጋቢት 16/2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል በሚካሄደው ዓለማቀፍ 50ኛው የኦፑስ ዴይ ዩኒቬርሲቲ ባዘጋጀው ጉባሄ ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣቱ 2500 ታማሪዎች ባስተላለፉት መልእክት ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “መቼም ቢሆን ያላችሁን ኃይል በሙሉ አሟጣችሁ ከኢየሱስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ማዳበር ይኖርባችኃል ካሉ በኃላ ኢየሱስን በምስጢራት፣ በጸሎት ውስጥ እና በማንኛውም የሕይወታችሁ ጉዞ ውስጥ እንዲሁም እለት በእለት በምትገናኟቸው ሰዎች ውስጥም ሳይቀር ኢየሱስን መፈለግ ያስፈጋል ካሉ በኃላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

24/03/2018 16:18