2018-03-21 15:06:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከወጣቶች ጋር ያደርጉት ቃለ መጠይቅ እና መልስ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከወጣቶች ጋር ያደርጉት ቃለ መጠይቅ እና መልስ

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በመጪው ጥቅምት 2011 ዓ.ም. “እመንት እና በጥሪ  ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ  መልካም ውሳኔ መወሰን” በሚል መሪ ቃል ወጣቶች ላይ ትኩረቱን ያደርገ 15ኛው የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት አጥቃላይ መደበኛ ጉባሄ በቫቲካን እንደ ሚካሄድ ይታወቃል። ለእዚህም የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት 15ኛው አጥቀላይ መደበኛ ጉባሄ የተለያየ ዓይነት በተለይም ወጣቱን ትውልድ ያሳተፈ ቅድመ ዝግጅት በመደርግ ላይ ይገኛል። በእዚህ መሰረት ከመጋቢት 10-15/2010 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣቱ ወጣቶች ተሳታፊ የሆኑበት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተሳተፉበት እና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የማሕበርሰብ ክፍሎች ዘንድ በኢንተርኔት እና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎች አማካይነት በቀጥታ የተላለፈ ስብሰባ ባለፈው ሰኞ እለት ተጀምሩዋል። ይህ ባለፈው ሰኞ በይፋ በተጀመረው ቅድመ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ መገኘታቸው ታውቁዋል። በእዚህ ጉባሄ ላይ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣቱ 5 ወጣቶች ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያቀረቡትን ጣያቄ እና የእርሳቸውን መልሽ በአጭሩ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የእዚህን ጥይቄ እና መልስ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላሁ!

 

ጥያቄ ቁጥር 1

(ጠያቂ፦ ከናይጀሪያ የመጣች በጣሊያን ሀገር የምትኖር ወጣት ብለሲንግ ኦኮዌዲዮን ነበር)

ጥያቄ፡ እኔ ብለሲንግ ኦኮዌዲዮን እባላለሁ። የመጣሁት ከናይጀሪያ ነው፣ ወደ ኢጣሊያ የመጣሁት ከአራት ዓመት በፊት፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በኩል ነበር። ይህ የጉዞ መስመር ሙሉ በሙሉ ሰብዓዊ ክብሬን ያጣሁበትና የተዋረድኩበት ነበር። አንድ ቀን በእግዚአብሔር እርዳታ፣ ከዚያ የስቃይ ኑሮ ነጻ ወጥቼ ወደ አንድ የደናግል ማሕበር በመጠጋት ራሴን ለማዳን በቃሁ። አሁንም ቢሆን ያንን እኔ ያሳለፍኩትን የስቃይ፣ የባርነትና የውርደት መንገድ የሚከተሉ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ስላሉ፣ ከሕገ ወጥ ጉዞ እንዲቆጠቡና በገዛ እጃቸው ወደ ስቃይ ሕይወት እንዳይገቡ እንዴት ማስረዳት እንችላለን? ሰባዓዊ ክብራቸውን በማሳጣት፣ ወደ ባርነት ሕይወት የሚዳርጋቸውን፣ ወንጀለኞች የራሳቸውን ፍላጎት የሚያረኩበትን፣ ኪሳቸውን የሚያዳብሩበትን ይህን የተሳሳተ መንገድ እንዴት ማስቀረት እንችላለለን? ከእነዚህ የስቃይና የባርነት ሕይወት ቀማሾች መካከል አብዛኛዎቹ ካቶሊክ ወጣቶች ናቸውና፣ ቤተ ክርስቲያናችን መለስ ብላ ራሷን በመጠየቅ፣ ለእነዚህ ወጣቶች ትክክለኛና የሚበጅ የሕይወት መንገድ በማሳየት፣ ከምእመናኖች የሚቀርብላትን ጥያቄዎች በመመለስ ልትረዳቸው የምትችልበት መንገድ ካለ? 

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ምላሽ

ይህ አሁን የሚታይ ነባራዊ እውነታ ነው። ባለፈው ዓመት ከዚህ ባርነት ነጻ የወጡ ሴት ልጆች የሚኖሩበትን አንድ ቤት ጎብኝቼ ነበር። ለማመን የሚያስችግር ነገር ነበር። ከእነዚህ ሴቶች መካከል አንዷ በሞንዶቪያ ታግታ እቃ በሚጫንበት የመኪና ክፍል ውስጥ እጅ እና እግሯን ታስራ አንድ ሌሊት ሙሉ ተጉዛ እስከ ሮም ድረስ መጣች፣ በጣም አሰቃይተዋት ነበር፣ ለማምልጥ ብትሞክር ደግሞ ቤተሰቦቹዋን እንደ ሚገሉ አጋቾቿ ተናግረው ነበር። ከዚያም በመጀሪያ ከአፍሪካ በቀረበው ጥያቄ ላይ እንደ ሰማነው ለእዚህ አሰቃቂ ድርጊት እጅ አልሰጥም የሚሉ ሰዎችን እነሱ ማለትም አጋቾቹ ይደበድቧቸዋል፣ ያሠቃያቸዋልም፣ በመጨረሻም ያሸንፋዋቸዋል። ይህንንም ነው አንዳንድ ያገኘዋቸው ወጣቶች የነገሩኝ። ከእዚያም ሥራቸውን መሥራት ይጀምራሉ። ልባቸውን እና አእምሮዋቸውን ከሌሎች በማግለል፣ “ይህ የእኔ ተግባር ነው፣ ይህ የእኔ ሥራ ነው በማለት” ይናገራሉ፣ ነገር ግን በውስጣቸው ያለውን ውስጣዊ ክብር ለመጠበቅ የተቻላቸውን ሁሉ አያደርጉም፣ ነገር ግን ውጫዊ እና ማህበራዊ የሆነ ክብር ለማግኘት ይተጋሉ። በእዚህም ሁኔታ ራሳቸውን ይከላከላሉ። ነገር ግን ምንም ተስፋ የላቸውም። በእዚህ መልኩ ከሚያስቃዩዋቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ለማምልጥ ችለዋል፣ ነገር ግን የእነዚህ የማፊያ አባልት እነዚህን ሰዎች በማሳደድ መልሰው ያገኙዋቸዋል፣ አንዳንዴም የበቀል እርምጃ ይወስዱባቸዋል። ከአፍሪካ እና ከአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ወደ እዚህ የሚመጡ ስደተኞች፣ የሥራ እድል እናስገኝላችኃለን በማለት አታልለው ነው ወደ እዚህ እንዲመጡ የሚያደርጉዋቸው፣ የአውሮፓልን ውስጥ አስተናጋጅ፣ ወይም ሆስተስ ሥራ እናስገኛለን፣ እነዚህን እና እነዚህን በመሳሰሉ የሐሰት ወሬ ሕይወታቸው እንዲማረክ በማድረግ አታለው ወደ እዚህ ያመጡዋቸዋል። ይሁን እና በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ወደ እዚህ ተታለው መጥተው ተስፋ የተገባላቸውን  ሳያገኙ ቀርተው፣ ተንገላተው ከእዚህ ባርነት ነጻ ሲወጡ ደግሞ ወደ ትውልድ ሀገራቸው መመለስ አይፈልጉም፣ ምክንያቱም በቤተሰባቸው ዘንድ ክብር እንዳጡ ስለሚሰማቸው፣ እውነቱን ለመናገር ስለሚፈሩ፣ ወደ ሀገራቸው መመለስ አይፈልጉም። ፈርጣማ ስለ ሆኑ ሳይሆን ነገር ግን ቤተስቦቻቸውን በጣም ስለሚወዱ፣ በእዚህ በእነርሱ ላይ በደረሰው ታሪክ የተነሳ እህት ወንድሞቻቸው እንዲቆሽሹ እና የገፈቱ ቀማሽ እንዲሆኑ ስለማይፈልጉ ነው። በጣም ብዙ መከራ ይደርስባቸዋል። አንድ ወጣት ልጅ እንደ ነገረችኝ በቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ ያለባትን ገነዘብ አንድ ቀን ገቢ ማድረግ ካልቻለች ጆሮዋን እንደ ሚቆርጡ ወይም ጣቱዋን እንደ ሚሰብሩ ነግራኝ ነበር። ይህ አሁን በእኛ ዘመን እየታየ ያለ ዘማንዊ ባርነት ነው። በእዚህ መልክ የሚሰቃዩትን ሴቶች የሚረዱ ብዙ የበጎ ሥራ የሚሰሩ ሰዎች አሉ። በተለይም ለአስገዳጅ የወሲብ ባርነት የተጋለጡትን ሴቶች ቀስ በቀስ ወደ ትክክለኛው ሕይወት እንዲመለሱ፣ ከአጋቾቻቸው እጅ ነጻ እንዲሆኑ በማድረግ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ የሚያደርጉዋቸው ብዙ የበጎ ተግባር የሚያከናውኑ ሰዎች አሉ። ከእነዚህም አንዳንዶቹ በእዚህ የወሲብ ባርነት ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ነጻ እንዲወጡ በማድረግ፣ ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ በማድረግ፣ ተፋቅረው የተጋቡ ቤተሰብ የመሰረቱ ብዙ ሰዎችም አሉ። ሴቶች ያለአግባብ ለስቃይ ተዳርገዋል። ይህም በሰበዐዊነት ውስጥ የተከሰተ ትልቁ በሽታ ነው፣ አሁን አሁን ማኅበራዊ የሆነ በሽታ እንደ ሆነ የመጣ በሽታ ነው፣ በሰው ልጆች ላይ እየተቃጣ ያለ ወንጀል ነው። ታዲያ እንደ እነዚህ ዓይነቶቹን ለጥቃት የተዳረጉ ሴቶች ማን ልረዳቸው ይችላል? በቅድሚያ እነዚህን ሴቶች መርዳት የሚችሉት ሴቶች ወይ ገዳማዊያን ሲስተሮች ሊሆኑ ይችላሉ። በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማነኛውም ጥቃት ማውገዝ ያስፈልጋል፣ በተለይም ደግም እነዚህ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየተፈጸሙ የሚገኙት በተጠምቁ፣ ክርስቲያን በሆኑ፣ ካቶሊክ በሆኑ የማኅበረሰብ ክፍል ውስጥ ሲሆን ደግሞ ይህንን ድርጊት ፈጻሚዎች ማኅበረሰቡን ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባቸዋል።

ጥያቄ ቁጥር 2

(ጠያቂ፡- ማክሲም ራሲዮን ይባላል። ከፓሪስ)

ጥያቄ፡ በፓሪስ ከተማ የሕግ ተማሪ ነኝ። አልተጠመቅሁም፣ የካቶሊክ እምነት ተከታይም አይደለሁም። ዛሬ እንደበርካታ የማያምኑ የሁን የሚያምኑ ወጣቶች፣ በሥራዬ ዘርፍ አንድ ምርጫ ማድረግ አለብኝ ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን ግራ ስለተጋባሁና ስለተጨንቅሁ ይህን ምርጫ ለማድረግ ተቸግሬአለሁ። በትምህርቴም ቆራጥ ውሳኔን እንዳላደርግ በውስጤ መተማመን ይጎድለኛል። በጠንካራ መሠረት ላይ እንዳልቆምኩ የሰማኛል። ለሕይወቴ ትርጉም እንዲኖረው ከፊቴ የቆመውን ትልቅ ግድግዳ መጋፈጥ እንዳለብኝ ይሰማኛል። ስለዚህ ወደ ውስጤ መለስ ብዬ፣ የሕይወቴን አካሄድ መመልከት ይኖርብኛል። በዚህ ዓለም ማንነቴን በሚገባ እንዳውቅ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ግንኙነት እንዳውቅ የቆምኩበትን መሠረት ለይቼ ማወቅ አለብኝ። አንድ ከሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ኃይል መኖሩን ማወቅ ብችል ኖሮ፣ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በመገንዘብ የራሴን አቋም ቤተ ክርስቲያን ሊኖረው ከሚችለው ሃይል ጋር በማመዛዘን አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እችል ነበር። ለልቤ ከለላን ማዘጋጀት እፈልጋለሁ። ምርጫን የማድረግና የመውሰን ብቃት እንዲኖረኝ ስለምፈልግ፣ ከየት መጀመር እንዳለብኝና የትኛውን አቅጣጫ መያዝ እንዳለብኝ ቢያግዙኝ።            

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰጡት ምላሽ

 

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ምላሽ

አደጋው ጥያቄዎች እንዲነሱ ማድረግ ላይ አይደለም። ይህንን ጣይቄ ባነሳህበት ወቅት ምን እንደ ሚከሰት ለመስማት ፈልገህ ያደርከው እንደ ሆነ ለመረዳት እችላለሁ። አንተም ጥያቄዎችን ከስጥህ አውጥተህ ተይቀሃል፣ ጥያቄዎችህን ማደንዘዣ ስታክልበት በግልጽ አቅርበሃል። ይህ አሁን አንተ የጠየከው ጥያቄ እኛም ልንጥይቀው የሚገባው ወሳኝ ጥያቄ ነው። በማነኛውም መስፍርት በውስጣችን ያለውን ጥያቄ አውጥተን መጠየቅ እጅግ አስፈላጊ ነው። እኛ ሁላችን በማስተዋል ጥበብ የተሞላ መልካም የሆኑ ውሳኔዎችን ማድረግ ይኖርብናል። ለእዚህም ነው በመጪው ጥቅምት ወር በሚደርገው የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ በሚል አርእስት እንዲካሄድ የመረጥነውም በእዚሁ ምክንያት ነው። በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሳይቀር በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ የማድረግ ችሎታ ይጎላቸዋል። በእዚህም ሁኔታ መደናገጥ አይኖርብንም። ምክንያቱ በእየእለቱ የሚያጋጥሙ እውነታዎች ናቸው። ወጣቶች በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ ይችሉ ዘንድ፣ ማገዝ፣ ማዳመጥ፣ ሰዎች በውስጣቸው ያለውን ሐሳብ እንዲያወጡ ማስቻል፣ ትክክለኝእውን መንገድ እንዲይዙ ማገዝ ያፈልጋል። በትሳሳቱም እንኳን ከስትታችሁ እንድትመለሱ ማገዝ ያፈልጋል። ለምሳሌ አሁን እዚህ ባምድረግ ላይ በምንገኘው ውይይት ላይ ይህ ውይይት ስርዓት በጥበቀ መልኩ እንዲሄድ የሚያደርጉ አስተናባሪዎች እዚህ አሉ። እነዚህ አስተናባሪዎች እናንተ ጥያቄዎቻችሁን ከውስጣችሁ አውጥታችሁ እንድትጠይቁ እያገዛችሁ የለምን? አይደለም እንዴ?። አሆን በእዚህም መልኩ በማስተዋል ጥበበ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ ያስችላችሁ ዘንድ በተደጋግሚ መወያየት ያስፈልጋል። ይህም ውሳኔ ላምድረግ ይረዳል። በሕይወታችን ውስጥ በዋነኝነት ሁለት ነገሮች ሊኖሩን ይገባል አንደኛው በውስጣችን ያለውን ነገር አውጥተን ለመናገር ብርታት ሊኖረን ያስፈልጋል፣ ሁሉንም የውስጣችንን ነገሮች አውጥተን ከሁሉም ሰዎች ጋር  መነጋገር የከብደን ይሆናል፣ በእዚህ ረገድ አንድ እምነት የምትጥለበት ሰው ፈልግ እና ከእርሱ ጋር መወያየት ያስፈልጋል፣ እርሱም እንዲያግዝህ ፍቀድለት፣ ይህ ሰው አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ሊሆን ይችላል፣ ወይም አንድ ጥበበኛ የሆነ ወጣት ሰው ሊሆንም ይችላል። አንድ ጥበበኛ የሆነ ሰው ማዳመጥ አይፈራም፣ ማዳመጥ ይችልበታል፣ ትክክለኛ ቃል በትክክለኛ ቦታ የመናገር ስጦታ እግዚኣብሔር ስጥቶታል። ራሳችንን በራሳችን ቆልፈን መኖር አይገባም፣ ስሜቶቻችንን በግልጽ መናገር ያስፈልጋል፣ በውስጣችን የሚገኙ ሐሳቦችን አድንዝዘን በእዚያው ማስቀረት አይገባንም፣ አንድ የምታምኑትን ሰው ፈልጉ እና ከእርሱ ጋር ተወያዩ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ እንድታደርጉ ይረዳችኃልና።

 

ጥያቄ ቁጥር 3

(ጠያቂ ማርያ ደ ላ ማካረና፣ ከአርጀንቲና)

ጥያቄ፡  በትምህርት ዓለምና ከወጣቶች ጋር ካለን የሥራ ልምድ እንደተረዳነው፣ የቀሰምነው መሠረታዊ እውቀት ምክንያታዊና በእውነት ላይ የቆመ ቢሆንም፣ ዛሬ ግን ይህ እውቀት በመዳከሙ፣ ከሁሉ በላይ ታላቅ ሃይል መኖሩን የሚያረጋግጥልን እምነታችን በሌሎች አዳዲስ እሴቶች በመሸርሸሩ ጥርጣሬ ውስጥ ገብተን እንገኛለን። አስተማሪዎች እንደመሆናችን አርቆ የማሰብ ችሎታችንን ከሚጋርደን መንገድ ተመልሰን፣ ሌሎችንም እሴቶች ለማጥናት ራሳችንን እንድናዘጋጅ፣ እስካሁንም ላካበትናቸው ውብ ለሆኑ እውቀቶች ምስጋናን እናቀርባለን። በእርስዎ አስተሳሰብ፣ አሁን ምሁራን ያመጡትን አንዳንድ አዲስ የማስተማሪያ መንገዶችን በመጠቀም፣ ወጣቶች ዘላቂ ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለማድረግ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል ይላሉ? 

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ምላሽ

ማሪያ ማካሬና በጠይቀችሁ ጥያቄ ላይ ​​"ትምህርት ሕይወቴን ቀይሮታል” በማለት ተናግረሻል። ከተናግረቻቸው ነገሮች ውስጥ ስለትምህርት ስርዓት በተናገረችው ላይ ማንኛውም የትምህርት ስርዓት በንቃተ-ህሊና በተፈጥሯቸው የተገነቡ፣ ተጨባጭ የሆኑ፣ እውነት የሆኑ ነገሮችን የሚያስትምሩ፣ በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረቱ የጥርጣሬ ስሜንትን የሚያዳክሙ የትምህርት ስርዓት ይስፈልጋል ብለሻል።

እስቲ እውቀት እየገበያችሁ ያደጋችሁበትን ትምህርት ቤቶች ተመልከቱ፣  እነሱ እጅግ የላቁ ከፍተኛ የእውቀት መሽመቻ ቦታዎች ቢሆኑም አሁን አሁን ግን ይህንን ሊያስመሰግናቸው ወይም ሊያስሞግሳቸው የሚችለውን እሴት ብዙዎችሁ እያጡ መጥተዋል። ይህም አሁን ያለውን ዘመናዊነት ተከትሎ የማጣ ጉዳይ ነው አይደል? ማንኛውም የትምህርት መስጫ ማዕከል የሕነጻ ትምህርቶችን በአግባቡ ሊስጠ ይገባል፣ ይህም በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። ትምህርት ቤቶች ያጡትን ሙገሳ መልሰው ለመጎናጸፍ መሞከር ይኖርብቸዋል።

አንድ እኔ መናገር የምፈልገው ነገር አለኝ፣ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነገር አለኝ፣ አንድ የተሟላ ትምህርት ለማግኘት በሶስት ቋንቋዎች መጠቀም ይኖርብናል፣ የአእምሮ ቋንቋ የሚለው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህም በትክክል እንድናስብ ያደርገናል። ስለ ነገሮች ብቻ አስቡ ነገሮችንም እወቁ። ይህም በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው፣ ሐሳባችሁን እያሳደግችሁ ሂዱ፣ የሐስብ ነጻነት ሐሳቦችን መፈለግ ጥሩ የሆኑ አስተሳሰቦችን ማሳደግ፣ የሚለው ከሶስቱ ቋንቋዎች የመጀመሪያው ነው።

 

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ -የልብ ቋንቋ የሚለውን እናገኛለን። ጥሩ ስሜት እንዲሰማችሁ መማር፣ በሁኑ ወቅት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ብዙ ችግሮች ያታያሉ፣ የማሾፍ፣ የማላገጥ ያለመግባባት ወዘት  ይህንን እና ይህንን የመሳሰሉ ችግሮች ይኖራሉ። እነዚህም ችግሮች በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተለመዱ ችግሮች ቢሆኑም ቅሉ ነገር ግን የልባችንን ቋንቋ በመጥቀም በትዕግስ እና በትህትና በብርታትም ሳይቀር ማሳለፍ ይኖርብናል።

ሦስተኛው ቋንቋ ደግሞ እጅ ነው። ይህም መሥራት የሚለውን ያሰማል። ይህ ከእግዚኣብሔር ፈጣሪያችን  የተቀበልነው ትልቁ ስጦታችን ነው። እደጥበብ የሚወልደውም ከእጃችን ሥራ ነው። ምህንድስና ወይም የእንጻ ሥራ የእጃችን ሥራ ውጤት ነው። 

እነዚህ ሶስት ቋንቋዎች ማለትም የጭንቅላት፣ የልብ እና የእጅ ቋንቋ ምን እንደ ሚሰማኝ እና ምን እንደ ምስራ አስባለሁ፣ ያስበኩትን እና የተመኘውትን እሰራለሁ፣ የሚስመኝ ስሜት እና የማስበው ሐስብ በተግባር ላይ አውላለሁ። ሶስቱም ቋንቋዎች ተስማሚዎች ናቸው፣ ይህም የትምሕርት ቤት ተመክሮ ነው። ሶስቱም ቋንቋዎች መጣመር ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳት በትምሕርት ግላዊ የሆነ ጉዳይ ቢሆን ነገር ግን በየጠቃላይ ለማህበረሰብ እድገት አስፍለጊ መሳሪያ ነው። አሁን ያለንበት ዓለም ትንሽ ለመተቸት እፈልጋልሁ፣ ምን አልባትም ሽማግሌ በመሆኔ የተነሳ የድሮ አስተሳሰብ የያዘ ሰው ነው ልትሉኝ ትችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ይህ ሐሳብ በጣም ጠቃሚ በመሆኑ የተንሳ ላካፍላችሁ እፈልጋልሁ።

ምክንያቱም አደጋ የምያስከትል ነገር ነውና። ለምሳሌ ቤተሰብ በምሽት አባት እና እናት ቴሌቪዥን ሲመለከት እያንዳንዱ ልጅ ከስልክ ጋር ነው የሚጫወተው አይደል? ከጓድኞች ጋር ማውራት ወይም ከእናት እና ከአባት ጋር መነጋገር ያስፈልጋል፣ በምናባዊ ዓለም ከሚደርጉ ግንኙነቶች ይልቅ ተጨባጭ የሆነ ግንኙነት ማደርግ ይገባል። ምናባዊ ዓለም ስር መሰረት እንዳይኖረን ያደርጋል። ስለእዚህም ምንም እንኳ ምናባዊ ዓለም መልካም የሆኑ ገጽታዎችም ቢኖሩትም ነገር ግን ከወሰን ስያልፍ መልካም ልሆን አይችልም እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ግንኙነት ማድረግ ይኖርብናል። ጨዋታው ተጨባጭ ነው። ግንኙነታችም ተጨባጭ ሊሆን ይገባዋል።

ጥያቄ ቁጥር 4

(ጠያቂ ፦ጁሊያን ቨንዚሎቪች ከዩክሬን፣ የግሪክ ስርዓተ አምልኮን ከምትከተል ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን)

ጥያቄ፦ ዘመናችን  በተለያዩ አዳዲስ ባሕሎች የተዋጠ ነው። አንድ ካህን የሐይማኖት አስተማሪ ብቻ ሳይሆን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ምስክርም በመሆኑ፣ የዘመናችንን ሁኔታ በመገንዘም፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን ጥበብ በመጠቀም እነዚህን አዳዲስ ባሕሎችን የማወቅ ችሎታ አለው። በእርስዎ አስተያየት፣ አንድ ለክህነት አገልግሎት የሚዘጋጅ የዘርዓ ክህነት ተማሪ፣ በዘመኑ ባሕሎች ውስጥ የሚገኙ ጥሩና መጥፎ የናሕል እሴቶችን እንዴት ለይቶ ማወቅ ይችላል? ለምሳሌ ወጣቶች በገላቸው ላይ የሚነቀሱት ምስሎች ለአንድ ወገን ወጣቶች የቁንጅና መግለጫ ሲሆን ለሌላው ወገን ደግሞ የባሕል መግለጫ መንገድ ነው ቢባልም፣ የባሕል መግለጫነቱን ማወቅና መረዳት ለብዙዎች አስቸጋሪ ነው። አንድ ወጣት ካህን፣ የተወሳሰቡ ባሕሎች ሲያጋጥሙት ምን ዓይነት አቋምሊኖረው ይገባል?

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ምላሽ

በጣም አመስግናለሁ ይህም እውነተኛ የክርስቶስ ምስክርነት ነው፣ የክርስቶስ ምስክር ያለሆነ አንድ ካህን በጣም ይጎዳል፣ በጥእም ክፉ ይሆናል፣ በጣም መጥፎ ይሆናል፣ ሕዝቦችን በትክክለኛ መልኩ አያንጽም ያሳስታል። ነገር ግን ምስክርነት ሊሰጥ የሚገባ ማኅበርሰቡ ራሱ ሊሆን ይገባል፣ አንድ ካህን የክርስቶስ መስካሪ ሊሆን የሚችለው የእዚያው ማኅበረሰብ አንድ አካል በመሆን ብቻ ነው። አንድ የክርስቶስ ምስካሪ የሆነ ካህን ባለበት ማኅበረሰብ ውስጥ ምስክርነቱን መስጠት ካልቻለ እርሱ ወደ ፊት መጓዝ አይችልም፣ የክርስቲያን ማኅበረሰቡ ራሱ ከካህኑ ጋር በጋር ምስክርነትን የመስጠት ክርስቲያናዊ ግዴታ አለበት፣ነገር ግን ካህኑ ብቻውን ምስክር ሊሆን ይከብደዋል፣ ነገር ግን የክርስቲያን ማኅበረሰብ ካህኑ ብቻ መስካሪ እንዲሆን ብቻውን ከተወው ካህኑ እንዲሁ ዝም ብሎ እንደ አድን አገልጋይ ይሆናል ማለት ነው፣ ምዕመኑም በበኩል ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጣል፣ ቅዳሴ ያስቀድሳል፣ የሞተ ዘመድ ካለው ያስቀብራል እንዲሁ የመጀመሪያ ቅዱስ ቁርባን ለምሳተፍ ይመጣል ከእዚያም ከቤተ ክርስቲያን ይጠፋል። የእዚህ ዓይነቱ ማኅበርሰብ በእውነት የክርስቶስ ምስክር ነው ልንለው አንችልም። ስለእዚህ ማነኛውንም ዓይነት በማኅበርሰቡ ውስጥ የሚደረገው ምስክርነት ማኅበርሰቡ ራሱ ከካህኑ ጋር በመተባበር ሊመስከረው የሚገባ ምስክርነት ሊሆን ይገባል።

ባህልን በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ ነበር። በተለይም በሰውነታቸው ላይ የተለያዩ ዓይነት ስዕሎችን ወይም ምልክቶችን የሚነቀሱ ሰዎችን አስምልክተህ ላነሳሀው ጥያቄ በተመለከተ በእዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መፍራት የሚኖርብህ አይመስለኝም፣ ምክንያቱም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራዊያን (ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ባሕል በሀራችን በኢትዮጲያ በክርስቲያንቾ ዘንድ በሰፊው የሚንጸባርቅ በሕል እንደ ሆነ ልብ ሊባል ይገባል) ዘንድ ግንባር ላይ የመስቀል ምልክት የመነቀስ ባህል ነበራቸው ዛሬውም ቢሆን የሚታይ እውነታ ነው። ቅዱስ መስቀልን በግንባራቸው ላይ ይነቀሱ ነበር። ምንም እንኳን በዛሬው ዘመን የሚታየው በሰውነት ላይ የሚደረግ ንቅሳት በጣም የተጋነነ ነው። ለጤናም በጣም አስጊ የሆነ ጉዳይ እየሆነ መጥቱዋል። ዋናው ነገር በአሁኑ ወቅት የምናያቸው በሰውነት ላይ የሚደረጉ ንቅሳቶች ወይም ታቱ በጣም የተጋነኑ መሆናቸው ነው እንጂ። ምን አልባት የወጣትነት መገለጫ ሊሆን ይችል ይሆናል፣ እንደ እነዚህ ያሉ ውይይቶችን በምንከፍተበት ወቅት ወጣቶች ራሳቸው እንዲህ ዓይነት ባሕል ውስጥ ለምን እንደ ገቡ ከእነርሱ መረዳት ይቻል ይሆናል። መወያይት መልካም ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ሊያስፈራችሁ አይገባም። ወጣቱ ትውልድ በፍጹም ልያስፈራን አይገባም። መንም እንኳን አንዳንዴ መልካም ሆኖ የምይታዩን ነገሮች ቢኖሩም እንኳን ወደ እውነት ሊያደርሰን የሚችል ብዙ መነግድ አለ። ይህንንም በፍጹም መርሳት የለባችሁም ማኅበረሰቡ ከካህኑ ግራ በጋር በመሆን ክርስቶስን ሊመሰክሩ ይገባል አመስግናለሁ።

 

ጥያቄ ቁጥር 5

(እህት ተሬዚና ቻዎይንግ ቸንግ ከቻይና ነው፣ በኡርባንያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የስነ ሐይማኖት ሳይንስ ተማሪ)

ይህን አጋጣሚን በማግኘት የእርሶን ምክር ለመጠየቅ ዕድል በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ቻይና በኤኮኖሚ እድገት ትልቅ ለውጥ እያሳየ ያለ አገር ነው። ሕዝቡ በሃብት ለመበልጸግ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ወጣቶችን ግን የማንነት ጥያቄ እጅግ እያስጨነቃቸውና እያሳሰባቸው ይገኛል። ልባቸው በተለያዩ ሃሳብ ውስጥ በመግባት ወዲያና ወድህ እያለ ይገኛል። ኢንተርኔት ሁሉን ነገር ፈጣንና የተመቻቸ በማድረግ ብዙ እውቀቶችን እያስጨበጣቸው ይገኛል። በዚህ ሁኔታ የተለያዩ ዓለማዊ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። ትክክለኛውን ባሕል የተከተለ የቤተክርስቲያን አገልጋይ እህቶችን የማዘጋጀት ሥራ በጣም ዝቅተኛ ነው። የእነዚህ ወጣት ልጃገረዶች መንፈሳዊነት ሌሎች ወጣቶችን ለመሳብ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም ውጤቱ በጣም አነስተኛ ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ እኛ ወጣት ደናግል፣ ተልዕኮአችን ፍሬያማ እንዲሆን አሁን ሕዝቡ እየተከተለ ያለውን ባሕል ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር እንዴት ልናቀራርብ እንችላለን?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ

ስለጥያቄሽ አመስግናለሁ። ራስሽን ለጌታ አገልግሎት መስዋዕት ለማድረግ በማሰብ የመንፈሳዊ መኅበር አባል ለመሆን ወደ ማኅበር መግባትሽን ገልጸሽልኛል፣ ይህም በጣም አስፈላጊ ነው።  ማኛውም ወጣት መነፍሳዊ ሕይወት ለመንሮ ራሱን ከማዘጋጀቱ በፊት ይህ መንፈሳዊ ሕይወት ምን መሆኑን በሚገባ ማወቅ ይኖርበታል። አንድ ትክክለኝእ መነፍሳዊ የሕነጽ ትምህርት በተለይም ደግሞ በገዳም ውስጥ ለመኖር ዝግጅት የሚያደርግ ሰው አራት መስረታዊ የሆኑ ነገሮችን ልያውቅ ወይም ልያሟል ይገባዋል። የመነፈሳዊ ሕየወት የሕነጻ ትምህርት፣ የአእምሮኣዊ የሕነጻ ትምህርት-ይህም ማለት በደንብ ማጥናት ይኖርባቸዋል ማለት ነው-በማሕበር መኖር የሚያስችላቸው ማኅበራዊ ኑሮን የተመለከቱ የሕነጻ ትምህርት-ይህም በማሕበር ወስጥ የሚነሱ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት እና የአብሮ መኖር መንፈስን ለማጠናከር በቃት እንዲኖራቸው ማስተማር ማለት ነው- እና በመጨረሻም የሐዋሪያው ተልዕኮን በሚገባ ማከናወን የሚያስችላቸው የሕነጻ ትምህርት-ይህም ቅዱስ ወንጌል በሚገባ ለማስራጨት በቃት እንዲኖራቸው የሚራዳ የሕነጻ ትምህርት አንድ ወጣት ወደ ማኅበር ገብቶ መነፈሳዊ ሕይወት ለመኖር ከመጀመሩ በፊት ሊኖረው የሚገባው 4 ዋና ዋና ባሕሪያት እነዚህ ናቸው።

በቻይና በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ባለው የኢኮኖሚ እድገት የተነሳ ብዙ ወጣቶች ትኩረታቸው ወደ እዚሁ ቁሳዊ የሆነ ሐብት ለማጠራቀ ወደ ሚደርገው እስቅድድም ይዞራል ማለት ነው። በእዚህም ረገድ እየሱስ ከአንድ ወጣት አብታም ሰው ጋር ያደርገውን ውይይት መመልከት ይችላል። ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለው ኢየሱስ ይህንን ወጣት ሐብታም ሰው እንዳየው ወደደው ይለናል። በጣም ተገቢ እና መልካም የሚባል ሕይወት ነበረው፣ ነገር ግን አንድ ትልቅ ነገር ይጎለው ነበር፣ ከሐብት ጋር ከፍተኝ እየሆነ ቁርኝት ነበረው። የእዚህ ዓይነት በሕሪይ ጥሩ ባሕሪ አይደለም። በእዚህ ረገድ አንድ ካህን ወይም አንድ ገዳማዊት ከገንዘብ ጋር ጥብቅ የሆነ ቁርጭት ያላቸው ከሆነ ደግሞ በጣም አደገኛ ነው። ዲያቢሎስ በኪሳችን በኩል ዘልቆ ወደ ውስጥእችን እንደ ሚገባ በፍጹም መዘንጋት የለብንም። በመቀጠልም በትዕቢት መወጠር፣ ኩራት በኣነዚህ እና እነዚህን ነገሮ በመሳስሉ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ኃጢኣት ውስጥ እንገባለን። ስለእዚህም አንድ ገዳምዊት ወይ አንድ ካህን በፍጹም ከገንዘብ ጋር ቁርጭት ሊፈጥሩ አይገባምእባካችሁን በገንዘብ ፍቅር ከመወስደድ ይልቅ በርሃብ መቆየት ይሻላል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.