Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "ወደ ቅዱስ ቁርባን ቀርበን መቅረብ መልካም ስራዎችን እናድናደርግ ያግዘናል" ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - AP

21/03/2018 14:20

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው ከጥር 7/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ መጋቢት 12/2010 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር ረቡዕ እለት በተከታታይ እያደርግያደርጉት የሚገኙት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ  በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዛሬው እለት በእዚሁ አርእስት ዙሪያ ባዳረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዐት ዙሪያ ላይ በማደርግ መሰረቱን በዩሐንስ ወንጌል 6:54-55 ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 12/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

በእለቱ የተወስደው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

 “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤ ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና” የዩሐንስ ወንጌል 6፡54-55

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ቀደም ባሉት በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ በመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ስረዓት ዙሪያ የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማድረጋችን የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ዙሪያ የምናደርገውን አስተምህሮ እንቀጥላለን። መስዋዕተ ቅዳሴን የምናስቀድስበት ምክንያት ራሱን በቃሉ እና በመንበረ ታቦት ላይ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበውን ክርስቶስን ለመመገብ እና እርሱን እንድንመስል እንዲያግዘን በማሰብ ነው። ጌታ ራሱ እንዲህ ይላል “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤ ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውናበማለት ተናግሩዋል። በእርግጥ ጌታ በመጨረሻ እራት ላይ ደሙን እና ሥጋውን ለደቀ-መዛሙርቱ በሰጠበት ወቅት ዛሬውም ቢሆን በምስጢረ ክህነት ወይም ድቁና አማካይነት የቀጠለ ምስጢር ሲሆን ለእዚህም ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በተዘጋጁ አገልጋዮቹ አማክይነት የሕይወት እናጀራ እና የደኽንነት ጽዋውን ዛሬም ይሰጠናል።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ካህኑ እንጄራውን አስንቶ ከቆረሰው በኃላ ለምዕመኑ በማሳየት ምዕመኑ በእዚህ በጌታ እራት ላይ እንዲሳተፍ ይጋብዛቸዋል። በእዚያን ወቅት ከመንበረ ታቦት ወደ እኛ የሚመጡትን እነዚያን ቃላት እንሰማቸዋለን፣ “እነሆ የዓለምን ኃጢኣት የሚያጠፋ የእግዚኣብሔር በግ ወደ እርሱ ራት የተጠሩ ሁሉ ብጹዕን ናቸው” በማለት ካህኑ ከቆረሰው እንጀራ ለምዕመኑ በማሳየት ይህንን ጸሎት ይደግማል። ይህም ቃል ከዩሐንስ ራእይ 19:9 ላይ ካለው “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸውከሚለው የተወሰደ ነው። ይህ የግብዣ ጥሪ የቅድስናና እና የደስታ ምንጭ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት እንድናጠናክር ታስቦ የሚደረግ የግብዣ ጥሪ ነው። ይህም ጥሪ አስደሳች የሆነ ጥሪ እና በእምነት አማካይነት ሕሊናችንን እንድንመረምር የሚያበቃን ጥሪ ነው። በእርግጥ በአንድ በኩል እኛ ከክርስቶስ ቅድስና ጋር ያለንን ርቀት እንድንመለከት ያደርገናል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የእርሱ ደም የፈሰሰው “ለኃጢኣታችን ስሪዬት እንደ ሆነ” እንድናምን ይረዳናል። ይህንን የማዳን ኃይል ያለውን ደም በማሰላሰል ቅዱስ አጎስጢኖስ “እኔ ሁልጊዜ ኃጢአት እሠራለሁ ስለእዚህ ሁል ጊዜ መድሃኒት እፈልጋለሁ” ማለቱ ያታወሳል። እኛም በእዚህ እምነት በመታገዝ ይህ የዓለምን ኃጢኣት ማስወገድ የሚችለውን የእግዚኣብሔር በግ በመማጸን “ጌታ ሆይ ይህንን የአንተን እራት ለመካፈል የተገባው አይደለሁኝም፣ ነገር ግን አንድ ቃል ብትናገር ነብሴ ትድናለች” በማለት እንማጸናለን።  

ይህንን የጌታ እራት ለመቀበል እኛ ተሰልፈን የምንሄድ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን እውነቱን ስንመለከት እኛን ከእርሱ ጋር ለማመሳሰል ወደ እኛ የሚመጣው ክርስትሶ መሆኑን እናገነዛባለን። ቅዱስ ቅርባንን መቀበል ማለት ያ የተቀበልነውን ቅዱስ ቁርባን እንድንሆነ የምያጎለበተን ነው። በእዚህ ረገድ ይህንን ሐሳብ በይበልጥ እንድንረዳ ቅዱስ አጎስጢኖስ ይረዳናል፣ ይህንንም እርሱ ከክርስቶስ ብርሃን የተቀበለበትን አጋጣሚ በማስታወስ እንዲህ ይላል “ እኔ ታላላቅ የሚባሉ ሰዎች የሚመገቡት ምግብ ነኝ፣ አንተም እደግ እና ተመገበኝ። ልክ ለአካላዊ ሥጋ እንደ ምትመገበው ምግብ ዓይነት አነተ አይደለህም ወደ ራስህ የምትቀይረኝ፣ ነገር ግን አንተ ነህ ወደ እኔ የምትቀየረው” ማለቱ ይታወሳል። እንጅራው እና የወይን ጠጁ ወደ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም እንደ ሚቀየሩ ሁሉ፣ እንደዚሁም ይህንን የክርስቶስ  ሥጋ እና ደም በእመነት የሚቀበሉ ሰዎች ሁሉ ሕያወ ወደ ሆነው ቅዱስ ቅርባን ይቀየራሉ። ይህንን ቅዱስ ቁርባን የሚያድለው ካህን በሚያድልበት ወቅት “ይህ የክርስቶስ ሥጋ ነው” በማለት በሚናገርበት ወቅት ይህንን ቅዱስ ቁርባን የሚቀበለው ሰው ደግሞ “አሜን!” በማለት ይመልሳል፣ በእዚህም ምክንያት ይህንን ቅዱስ ቁራባን የሚቀበል ሰው በእዚሁ ቅዱስ ቁራባን አማክይነት የሚያገኘውን ጸጋ እና ይህንን የተቀበለውን የክርስቶስ ሥጋ ለመምስል መትጋት ይኖርበታል ማለት ነው። ከራስ ወዳድነት መንፈስ ነጥቆ በማውጣት ከክርስቶስ ጋር በምያዋህደን ወቅት ይህ ቅዱስ ቁራባን በክርስቶስ አማካይነት አንድ ከሆኑ ሰዎች ሁሉ ጋር ሕብረት እንዲኖረን ያደርገናል። ይህም ቅዱስ ቁርባን የሚሰጠን ትልቁ ድንቅ የሆነ ነገር ነው፣ ይህም  የምንቀበለውን እንድንሆን ያደርገናል ማለት ነው።

ቤተ ክርስቲያን ምዕመኑ ሕያው በሆነ መልኩ ይህንን የክርስቶስን ሥጋ እንዲቀበሉ ምኞቱዋ ነው። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም በአፋችን ከተቀበልን በኃላ ይህንን የተቀበልነውን ጸጋ በልባችን ውስጥ በማኖር በጸጥታ ጸሎት በማድረግ የተቀበልነውን ጸጋ መጠበቅ ይኖርብናል ማለት ነው።

የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዐት ለቅዱስ ቁርባን ስረዓት በኃላ በሚደረግ የመደምደሚያ ጸሎት ይጠናቀቃል። በእዚህም ጸሎት ካህኑ በሁሉም ምዕመን ሥም በመሆን ወይም ምዕመኑን በመወከል ካህኑ ወደ እግዚኣብሔር የእርሱ እራት ተካፋዮች ስላደርገን በማመስገን እና እንዲሁም የተቀበልነው ቅዱስ ቁርባን ሕይወታችንን እንዲቀይር በመጠየቅ ጸሎቱን ወደ እግዚኣብሔር ያቀርባል።

21/03/2018 14:20