Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

“እናንተ ሐዘን የደረሰባችሁ ደስ ይበላችሁ; ሐሴትም አድርጉ”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት እና አስተንትኖ ባደርጉበት ወቅት - AP

13/03/2018 09:18

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው ቅድስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 02/2010 ዓ.ም. በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በዐራተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት ላይ ከዩሐንስ ወንጌል 3፡14-21 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ለኒቆዲሞድ “ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤ይኸውም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው” ብሎ በተናገረው የወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አድገውት የነበረውን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ይህ አሁን የምንገኝበት ዐራተኛው የዓብይ ጾም ሳምንት ሰንበት እለትየደስታ ሰንበትበመባል የሚጠራ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በዛሬው እለት በስርዓተ አምልኮዋችን የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ከመዝሙረ ዳዊት 136 ላይ ተወስዶ በተነበበው ቃል ውስጥኢየስሩሳሌም ሆይ ደስ ይበልሽ!” በማለት ሁላችን ደስተኞች እንሆን ዘንድ በመጋበዝእናንተ ሐዘን የደረሰባችሁ ደስ ይበላችሁ; ሐሴትም አድርጉበማለት ለሁላችን ጥሪ በማድረጉ የተነሳ ነው። የእዚህ ደስታ መነሻው እግዚኣብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ያሳየው ፍቅር ሲሆን የህም በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥእግዚኣብሔር ዓለምን እጅግ ስለወደደ አንድ ልጁን ሰጠ፣ ስለእዚህ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ይኖረዋል እንጂ አይጠፋም” (ዩሐንስ 316) የሚለው የደስታችን መነሻ ነው። ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር በተነጋገረበት ወቅት ኢየሱስ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ሁኔታዎች ተስፋ አስቆራጭ በሚመስሉበት ጊዜ እንኳ እግዚአብሔር ጣልቃ በመግባት ለሰው ልጅ መዳንን እና ደስታን ይሰጣል የሚለውን የክርስቲያኖች አዋጅ ማዕከላዊ የሆነው ጭብጥ ያጠቃልላል። እግዚአብሔር በእርግጥ ዝም ብሎ አይቀመጥም፣ ነገር ግን በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ በመግባትከሕይወታችን ጋር ይቀላቀላልበህይወታችን ውስጥ ይገባል፣ በጸጋው ሕይወትን ይሰጣል ያድናልም።

እኛም እራሳችንን በራሳችን  እርግጠኛ አድርገን እንድንቆጥር፣ እግዚአብሔርን ያለመፈለግ እና ከእርሱ እና ከእርሱ ቃል ሙሉ በሙሉ ነጻ ለመሆን በመፈለግ. . . የመሳሰሉትን ስሜቶች በመተው ጆሮዎቻችን የእርሱን ቃላት ለመስማት ማዘጋጀት ይገባናል። እኛ ማን መሆናችን ለማወቅ ብርታት ካለን ደግሞ እኛ ደካሞች እና ውስን የሆን መሆናችንን ለመረዳት ብርታት ይኖረናል ማለት ነው። እኛ ከጭንቀት፣ ለነገ ከማሰብ፣  ህመምና ሞትን በመፍራት የተነሳ ወደ ጭንቀት ውስጥ እንገባለን። ከእዚህ ክስተት እና ችግር ለመውጣት ደግሞ አንዳንድ ሰዎች መውጫ መንገድ ፍለጋ አንዳንድ ጊዜ እንደ አደገኛ መድሃኒት ይጠቀማሉ፣ ይደበቃሉ ወይም የአጉል እምነቶች ወይም አስማታዊ የአምልኮ ሥርዓቶች የመሳሰሉትን አደገኛ አቋራጮችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል።

አንድ ሰው ውስን መሆኑን እና የራሱን ድክመቶች ማወቅ ጥሩ ነገር ነው፣ ይንንም ማወቅ ይገባል፣ ነገር ግን ይህንን ድክመታችንን የምናወቀው ተስፋ ለመቁረጥ ሳይሆን ነገር ግን ለጌታ ለማቅረብ ሊሆን ይገባል፡ እርሱም ከእነዚህ ነገሮች እንድንፈወስ ያደርገናል፣ እጃችንን ይዞ ይመራናል፣ በፍጹም ብቻችንን አይተወንም። እግዚኣብሔር ከኛ ጋራ ነው ለእዚህም ነው የምንደሰተው፣ እስቲ ዛሬ በእዚህ ምክንያት ለመደሰት እንሞክር።እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ ኢየሩሳሌም ሆይ ደስ ይበለሽስለሚል እኛም ዛሬ ልንደሰት ይገባናል።

እኛም ደግሞ በታላቅ ምሕረት በተሞላው እግዚአብሔር አብ እውነተኛና ታላቅ ተስፋ አለን፣እንዲያድነን ልጁን ሰጠን፣ ይህም ደስታችን ምንጭ ነው። ብዙ ሐዘኖች አሉን ነገር ግን እውነተኛ ክርስቲያኖች ስንሆን ደስታን እንድናገኝ የሚያደርገን ብዙ ተስፋ አለን። ውስን፣ አጢኣተኛ እና ደክሞች በመሆናችን የተነሳ ተስፋ መቁረጥ አይኖርብንም፣ ምክንያቱም እግዚኣብሔር ቅርባችን በመሆኑ እና ኢየሱስ ሊያድነን በመስቀል ላይ ስለሚገኝ ነው። የህም የእግዚኣብሔር ፍቅር መገለጫ ነው። ወደ መስቀሉ እየተመለከትንእግዚኣብሔር የወደኛልእንበል። ምንም እናኳን ኃጢያተኞች፣ ደካሞች፣ ውስን የሆንን ሰዎች መሆናችን እውነት ቢሆንም እንኳን እርሱ ከኃጢኣታችን፣ ከድክመታችን ከውስንነታችን ሁሉ በላይ ነው። እግዚኣብሔርን በእጃችን በመያዝ እና ወደ መስቀሉ በመመልከት ጉዞዋችንን ወደ ፊት እንቀጥል።

እግዚኣብሔር በልቡ ውስጥ ሁል ጊዜ እንደ ሚያስቀምጠን እንረዳ ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትርዳን። ብቻችንን በምንሆንባቸው ጊዜያት ሁሉ ከእኛ ጋር በመሆን የሕይወትን ፈተናዎች እንድንወጣ ትርዳን። ልጇ የሆነውን የኢየሱስን ስሜት መከተል እንችል ዘንድ በተለይም ደግሞ በእዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት በእርሱ መለኮታዊ ምሕረት ተስፋ ማድረግ እንችል ዘንድ ትራዳን።

 

13/03/2018 09:18