2018-03-07 15:40:00

የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት እግዚ/ር ልጁቹን ሁሉ በእርሱ ፍጹም በሆነ ፍቅር ውስጥ እንዲሰበስባቸው የሚጠይቅ ጸሎት ነው።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በጥር 7/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ በተከታታይ አድርገው የነበረ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ በእዚሁ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያቸውን ክፍሎች በማንሳት አስተምህሮ ማድረጋቸውን ከቅድም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

በእዚህም መሰረት ቀደም ባሉት ጊዜያት በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የኑዛዜ ጸሎት፣ በመቀጠልም አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የመግቢያ ጸሎት አንስተው ሰፊ የሆነ ትንታኔ መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም በመቀተል ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ደግሞ ከእዚሁ የመግቢያ ጸሎት በመቀጠል የሚገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባትን በተመለከተ ሰፊ አስተምህሮ አድርገው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

በእዚህም መሰረት የእግዚኣብሔር ቃል በሕይወታችን የሚያደርገው ጉዞ በተመለከተ የተናገሩት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ቃል ከጆሮዋችን ወደ ልባችን ከልባችን ወደ እጃችን በመጓዝ መልካም ተግባራትን እንድናከናውን ይረዳናል ማለታቸውምን መዘገባችን ይታወሳል። ባሳለፍነው ሳምንት በጥር 30/2010 ዓ.ም. ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በእዚሁ በስረዓተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ እያደርጉት የሚገኘውን የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ሰለምነበቡት የእግዚኣብሔር ቃላት እና በመቀጠልም በእዚህ በእግዚኣብሔር ቃል ላይ መስረቱን ስላደርገው ስብከት በማንሳት ጥልቅ የሆነ አስተምህሮ አድርገው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።  በየካቲት 7/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ያደረጉት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል የነበረ ሲሆን በእዚህም መስረት በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ከሚነበቡት የምጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት እና በእነዚህ ምንባባት ላይ ተመርኩዘው ከሚሰጠው ስብከት በመቀጠል ባለው የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት የማቅረብ ስነስረዓት ዙሪያ ጠለቅ ያለ አስተምህሮ ማድረጋቸውን መገለጻችን ይታወሳል።

በየካቲት 14/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ይህንን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክቶ በእየአመቱ እንደ ምያደርጉት አመታዊ ሱባሄ ለማድረግ በሮም ከተማ አቅራቢይ ወደ ሚገኘው አራቺያ ወደ ሚባልበት ስፍራ በመሄዳቸው የተነሳ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አለማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በየካቲት 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመስዋዕተ ቁርባን ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። በዛሬው እለት ማለትም በየካቲት 28/2010 ዓ.ም. የዳረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ ጀምረውት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል  እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በዛሬው እለት በመስዋዕተ ቅዱስ ቁራባን ዙሪያ አድርገውት የነበረውን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እናግብዛለን።

እኔ ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠባት ሌሊት እንጀራን አንሥቶ ከባረከ በኋላ ቈርሶ፣ “ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ለመታሰቢያዬም አድርጉት” አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፣ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ ከጽዋው በምትጠጡበት ጊዜ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። (1ኛ ቆሮጦስ 11:23-25)።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ቀን በምናደርገው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በአኮተቴ ቁርባን ጸሎት ላይ ያተኮረ ይሆናል። ባለፈው ሳምንት እንዳየነው ለመስዋዕተ ቈርባን መስዋዕት አስፈላጊ የሆኑት እናጀራ እና የወይን ጠጅ የማቅረብ ሥነ-ስረዓት ከተጠናቀቀ በኃላ የመስዋዕተ ቁርባን ጸሎት በመቀጠል ይከናወናል፣ በእዚህም ጸሎት አማካይነት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ምልኣት እንዲያገኝ በማድረግ እና የመስዋዕተ ቅዳሴ ማዕከል የሆነውን ቅዱስ ቁርባን በመስዋዕትነት ይቀርባል። በእዚህ ወቅት የሚደረጉ ጸሎቶች ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ላይ ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ላይ በነበረበት ወቅት አድርጎት ከነበረው ጸሎት ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ የሚፈጸም ሲሆን (ማቴዎስ 2627, ማርቆስ 1423, ሉቃስ 2217.19, 1ቆሮንጦስ 1124) እርሱ በእዚያን ወቅት አድርጎት እንደ ነበረው እንጀራውን እና ጽዋውን አንስቶምሥጋን አቀረበእንደ ሚለው በእዚሁ መስረት በእንጀራው እና በጽዋው ላይ ምስጋና የማቅረብ ስነ-ስረዓት ይደረጋል። በእዚህም ተግባር እየሱስ ቀደም ሲል አከናውኖት የነበረው የምስጋና ጸሎት እና የደኽንነት መስዋዕት እኛ መስዋዕተ ቅዳሴን በምናሳርግበት ወቅት ቀድም ሲል እየሱስ ፈጽሞት የነበረው መስዋዕትነት ሕያው እንደርገዋለን።

በእዚህ ታላቅ በሆነው የመስዋዕት ጸሎት አማካይነት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ቁርባንን የምታከብረው እና እንድታከብር ያደርጋት ምክንያት በእዚህ በእንጀራ እና ጽዋ ውስጥ በእውነት ክርስቶስ ስለሚገኝ  ከእርሱ ጋር ኅብረት እንዳለት ለማሳየት ነው።  “ልባችሁን ወደ ጌታ አምላክችን ከፍ አድርጉ፣ ለእርሱም ምስጋና አቅርቡየሚለውን ጥሪ ለምዕመናን በማቅረብ ይህ መስዋዕት ይጀምርና ይህንን መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ድምጹን ከፍ በማድረግ በእዚያ በመዋዕተ ቅዳሴ ውቅት የሚገኙትን ምዕመናን ሁሉ በሚወክል መልኩ ጽሎቱን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማክይነት ለእግዚኣብሔር ያቀርባል።የእዚህ መስዋዕት ትርጉም በእዚያው የሚገኙ ምዕመናን ሁሉ ከከርስቶስ ጋር ኅብረት በመፍጠር እግዚኣብሔር ስላከናወነው ታላቅ ውዳሴን በማቅረብ እና ለእዚህም ታላቅ ተግባር መስዋዕት ማቅረብየሚለውን ትርጉም ይይዛል። በእውነትየክርስቶስ መስዋዕት እና የቅዱስ ቈርባን መስዋዕት ሊነጣጠሉ የማይችሉ እንድ መስዋዕት ናቸውየካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ 1367) እንደ ተጠቀሰው።

በመስዋዕተ ቅዳሴ መጽሐፍ ውስጥ የተለያዩ ዓይነት የአኮተቴ ቁርባን ጸሎቶች ተጠቅሰው የሚገኙ ሲሆን (በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መጽሐፍ ውስጥ በቁጥር 1352 ላይ እንደ ተጠቀሰውአኮተቴ ቁርባን የምስጋናና የቅድስና ጸሎት ነው፣ እኛም ከቅዱስ ቁርባን ጸሎት ጋር ወደ አከባበሩ ማዕከል የላቀ ደረጃ እንደርሳለን  በእዚህ የመስዋዕተ አኮተቴ ቁርባን ጸሎት መግቢያ ላይ በሚገኘው ጸሎት እግዚኣብሔር ስለሰጠን ስጦታዎች ሁሉ በቅድሚያ ምስጋናን ለእርሱ የምናቀርብበት ጸሎት የሚገኝ ሲሆን፣ ለየት ባለ ሁኔታ ደግሞ አንድኛ ልጁን የዓለም አዳኝ እንዲሆን በመላኩ ምስጋናን የምናቀብበት ጸሎት ይገኛል ይህም ጸሎት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሁሉን አሸናፊ እግዚኣብሔር ሰማያትና ምድር በክብሩ የተሞሉ ናቸው. . .” በሚለው ጸሎት ወይም የወዳሴ መዝሙር ይደመደማል፣ በእዚህም ወቅት በእዚያ የሚገኘው የክርስቲያን ማኅብረሰብ ሁሉ በአንድ ድምጽ እግዚኣብሔርን ዘወትር ከሚያመሰግኑት እና ከሚስግዱለት ቅዱስና እና መላእክት ጋር ድምጻቸውን በማስተባበር ለእግዚኣብሔር ውዳሴን ያቀርባሉ።

በመቀጠል ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በመስዋዕተ ቁርባኑ ላይ እንዲወርድ የሚያደርግ የመማጸኛ ጸሎት ይቀርባል፣ በእዚህም መንፈስ ቅዱስ እንጀራውን እና ጽዋውን ይባርክ ዘንድ የመመጻኛ ጽሎት ይቀርባል። በእዚህ ምስጢር ውስጥ ክርስቶስ የሚገኘው ኅብስት እና የወይን ጠጁን ወደ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም በመለወጥ ነው። አበው የክርስቶስ ቃል እና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይህንን ለውጥ በማስገኘት ረገድ ውጤታም እንደ ሆነ ቤተክርስቲያን ያላትን እምነት በሚገባ አረጋግጠዋል (የካቶሊክ ቤተክራቲያን ትምህርተ ክርስቶስ . 1375) የክርስቶስን መሞት እና ከሙታን መነሳት በማስታወስ፣ የእርሱን በክብር መምጣት በመጠባበቅ፣ ቤተ ክርስቲያን ስማይን እና ምድርን ማስታረቅ የሚችል መስዋዕት ወደ እግዚኣብሔር ታቀርባለች፣ የክርስቶስን የፋሲካ መስዋዕት በማቅረብ ከእርሱ ጋር እና በእርሱ ስም፣ በመንፈስ ቅዱስ አማክይነት በክርስቶስ አማክይነትአንድ አካል እና አንድ መንፈስ እንድንሆንበማሰብ መስዋዕት ታቀርባለች፣ ይህም የሃይማኖት ምስጢር ነው። ይህም የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት  ጸጋና ፍሬ ነው፣ የክርስቶስን ሥጋ በምንመገብበት ወቅት የምንመገበውን እንሆናለን፣ ክርስቶስ በሥጋው አማክይነት አሁንም በዓለም ውስጥ ሕያው ሆኖ ይኖራል።

መስዋዕተ ቅዳሴ የቤተክርስቲያን መሥዋዕት ነው። የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያንም ራሱዋ ከሆነው ከክርስቶ መስዋዕት ትሳተፋለች። ከእርሱ ጋርም ራሷን በምልኣት እና በአጠቅላይ ትሰጣለች። ለመላው የሰው ዘር እርሱ ለአብ ከሚያቀርበው ምልጃ ጋር ራሷን ታዋዕዳለች። በእዚህ ብርሃንበጥንታዊ ዋሻዎች ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እጆቹዋን ዘርግታ በመጸለይ ላይ ባለች ሴት ትመሰላለች። እጆቹን በመስቀል ላይ በዘረጋው ክርስቶስ ተመስላ በእርሱ አማካይነት፣ ከእርሱ ጋር በእርሱ ስም ሆና ስለ ሰዎች ራሱዋን ታቀርባለች ታማልዳለች” (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ . 1368)

የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት እግዚኣብሔር ልጁቹን ሁሉ በእርሱ ፍጹም በሆነ ፍቅር ውስጥ እንዲሰበስባቸው የሚጠይቅ ጸሎት ሲሆን በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት በየስማቸው ከሚጠሩ  ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከብብጹዕን ጳጳሳትን ስም በመጥራት በእዚህም ከመላው ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለንን ሕብረት በመግለጽ ይከናወናል። ይህ ልመና በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት እንደ ሚቀርበው የቁርባን መስዋዕት ይህ ልመናም ለመላው የሰው ልጆች ደኽንነት ይሆን ዘንድ የሚቀርብ የመመጸኛ ጸሎት ነው። ይህንን የልመና መስዋዕት ቤተ ክርስቲያን የምታቀርበው የቤተ ክርስቲያን አባልት ለሆኑ ሰዎች እና እንዲሁም በተጨማሪም በክርስቶስ ለሞቱ፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ላልነጹ ምዕመናን ወደ ክርስቶስ ብርሃን እና ሰላም ይገቡ ዘንድ መስዋዕተ ቅዳሴ ይቀርባል። በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ማንም ሳይረሳ ሁሉም ሰው ያታወሳል፣ ሁሉንም ነገር በማስታወስ ለእግዚኣብሔር ያቀርባል።

ይህንን በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የሚደርገውን  ጸሎት ሁላችንም ቀርብ ብለን በጥልቀት በምንመለክትበት ወቅት በይበልት ትርጉሙን እንረዳለን፣ ትርጉሙን በይበልጥ የምንረዳ ከሆንን ደግሞ በተሻለ ሁኔታ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ለመሳተፍ ያስችለናል። በመሠረቱ በመስዋዕተ ቅዱስ ቁርባን ሥነ ሥርዓቶች ውስጥ የሚገኙ ጸሎቶች ሁሉንም ነገር በግልጽ ያስቀምጣሉ፣ ከእዚህም ባሻገር አንድ የክርስቶስ ተከታይ ወይም ሐዋሪያ የሆነ ሰው ሊኖረው የሚገባቸውን ሦስት ባሕሪይያት ያስቀምጣል እነዚህምምስጋናን ሁል ጊዜ እና በሁሉም ቦታ ማቅረብእኛን ሲመቸን ብቻ እና እኛ በፈለግንበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜ ማቅረብ የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን በሁለተኛ ደርጃ የሚቀመጠው ደግሞ ሕይወታችንን በነጻነት እና በነጻ የፍቅር ስጦታ አድርጎ ማቅረብ የሚለው ሲሆን ሦስተኛው እና የመጨረሻው ደግም ተጨባጭ የሆነ ሕብረት ከቤተ ክርስቲያን እና ከሁሉም ጋር መፍጠር የሚለው ነው። በአጠቃላይ በመስዋዕተ ቅዳሴ ውስጥ የሚገኘው ምዕከላዊ ጸሎት
እኛም ሕይወታችንን የምስጋና መስዋዕት አድርገን ማቅርብ ይኖርብናል የሚለውን ጭብጥ ቀስ በቀስ እንድንማር ያደርገናል።








All the contents on this site are copyrighted ©.