2018-03-05 15:29:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "የጤና ባለሙያዎች በእውነት ሊተካ የማይችል በጣም ወሳኝ የሆነ ሚና አላቸው" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየካቲት 24/2010 ዓ.ም.  ረፋዱ ላይ ከጣሊያን የጤና ባለሙያዎች፣ ነርሶች፣ የጤና ረዳቶች እና የሕጻናት ተነካባካቢ ፈዴሬሽን ተወካዮች ጋር በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ መገናኘታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስሙት ንግግር እንደ ገለጹት “በቅድምያ ከእናንተ ጋር ተገናኚቼ ለመወያየት በመብቃቴ የተነሳ የተሰማኝን ደስታ ለመገልጸ እወዳለሁ” ካሉ በኃላ “እናንተ ለመላው የማኅበረሰብ ክፍል እያበረከታችሁት ለምተገኙት መልካም ተግባር ያለኝን ምስጋና እና አክብሮት ለመገልጸ እወዳለሁ” ብለዋል።

የእዚህን ዜና ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ይህ የጣሊያን የጤና ባለሙያዎች፣ ነርሶች፣ የጤና ረዳቶች እና የሕጻናት ተነካባካቢ ፈዴሬሽን በጣሊያን ከሚገኙ ተመሳሳይ ፌዴሬሽኖች ጋር ሲነጻጸር 450 ሺ ባለሙያዎችን አቅፎ የያዘ በቁጥር የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ልቀመጥ የሚችል ፌዴሬሽን እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው የእዚህ  ፌዴሬሽን አባላት በቁጥር መብዛት በተለመደ መልኩ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ እና ይህ ፌዴሬሽን የበለጠ ጠንካር እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር በመሄድ ከሁሉም በላይ ሥራቸውን በሚገባ ማነጸባረቅ የሚያስችላቸውን እሴቶች እና ሀሳቦች ለማካፈል ያስችላቸው ዘንድ እንዲጠቀሙበት ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

አንድ በሽተኛ የሆነ ሰውን በመርዳት ረገድ የጤና ባለሙያዎች የሚጫወቱት ሚና በእውነት ሊተካ የማይችል ሚና እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው የሕክምና ባለሙያዎች ከታካሚዎቹ ጋር ቀጥተኛ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እንዳላቸው፣ በየቀኑ እንደ ምንከባከቡዋቸው፣ የሚያስፈልጋቸውን ነግሮች በማዳመጥ አካላዊ የሆነ ንኪኪን በመፍጠር የታካሚውን መከራ እንደ ሚጋሩ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ይህ የጣሊያን የጤና ባለሙያዎች፣ ነርሶች፣ የጤና ረዳቶች እና የሕጻናት ተነካባካቢ ፈዴሬሽን “ጤናን በተመለከተ የተለያዩ ዓይነት አስተምህሮዎችን መስጠት፣ በሽታ ሳይፈጠር በፊት አስቀድሞ የመከላከል፣ ሕመምን የማስወገድ እና ስቃይን ማስታገስ የሚሉትን አራት መሰረታዊ የሆኑ መርሆችን ያነገበ ፌዴሬሽን እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህን ውስብስብ እና በርካታ ተግባራትን በማከናወን በሁሉም የጤና እንክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ እና ከሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ተግባራቸውን በተጠናከረ መልኩ የምያከናውኑ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

ማንኛውንም ሙያችሁን የተመለከቱ ተግባራትን በምታከናውኑበት ወቅት ተግባሮቻችሁን ሙያዊ በሆነ መልኩ ብቻ ሳይሆን ሰብዐዊ በሆነ መልኩም ማከናወን እንደ ሚጠበቅባቸው ያሳሰቡት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ ከታካሚው ጋር ብቻ ሳይሆን ከታካሚው ቤተሰቦች ጋርም ሳይቀር መልካም የሚባል ግንኙነት መፍጠር ጠቃሚ እና አስፈላጊ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በሕክምና መስጫ ጣቢያዎች ውስጥ በጣም በርካታ የሆኑ ሰዎች፣ ከተለያዩ ሰብዕዊ ባሕሪያቸው ጋር እንደ ሚመጡ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህም ምክንያት የጤና በለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሰዎችን እንደየ በህሪያቸው ማስተናገድ፣ ምንም እንኳን አስቸጋሪ የሆነ ተግባር ቢሆንም ይህንን ለማድረግ ግን ሙያዊ እና ሰብዕዊ በሕሪያቸውን በማቀናጀት በትኩረት ተግባራቸውን ማከናወን እንደ ሚጠበቅባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው  በዚህ ሥራ ላይ ያለው እሴት እና ውድነት ሙሉ በሙሉ ሊገለጽ የሚችለው ሙያዊ ክህሎቶችን እና ለሰው ልጅ ስብዕና ትኩረት በመስጠት በእዚህም መልኩ ብቻ ተግባራቸውን ማከናወን እንደ ሚጠበቅባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለልጆች እና ለአረጋውያን ስይቀር ከተወለዱበት ቀን አንስቶ እስከ የሕልፈታቸው ቀን ድረስ እንክብካቤን በማድረግ፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ የታካሚዎችን ፍላጎቶች ለመረዳት፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማወቅ ቀጣይ በሆነ መልኩ በማዳመጥ ላይ የተመሰረተ ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን ያደነቁት ቅዱስነታቸው የጤና ባለሙያዎች የሚደርጉት ተግባር እንደየ ታካሚው ባሕሪይ እና ሕመም ተለዋዋጭ በመሆኑ የተነሳ ሁሌም ቢሆን መስፈርቶችን ብቻ የተከተለ እንዳልሆነ ገልጸው በእዚህም ምክንያት የታካሚውን ስሜት ለመረዳት፣ ሕመሙን እና ስቃዩን ለመካፈል ከፍተኛ የሆነ ጥረት እና ድካም እንደ ሚጠይቅ ገለጸው አሁኑም ቢሆን ይህንን ሊተከ የማይችል ሚናቸውን የሰው ልጆችን ማዕከል ባደረገ መልኩ ማከናወናቸውን እንዲቀጥሉ ቅዱስነታቸው መክረዋል።

“እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉት የእናንተን የጤና ባለሙያዎች ተግባራት ስንመለከት ይህ ተግባራቸው ሙያዊ የሆነ ተግባር ብቻ ሳይሆን አንድ እውነተኛ የሆነ ተልዕኮ እንደ ሆነ ያሳያል” ያሉት ቅዱስነታቸው የጤና በሉሙያዎች እያበረከቱት የሚገኘው አስተዋጾ “ሙያዊ ተልዕኮ ብቻ ሳይሆን ሰብኣዊ ተልዕኮ ጭምር እንደ ሆነ ገለጸው በተለይም ደግሞ ዝቅተኛ የሚባሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የሰብዐዊ መብታቸውን እና ሰብኣዊ እሴቶቻችወን ከግምት ባስገባ መልኩ እንክብካቤ ማድረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የጤና ባለሙያዎች ቀን በቀን የአንድ በሽተኛን ፊት እንደ ሚመለከቱ ከበሽተኛው ጋር አካላዊ የሆነ ንኪኪ እንደ ሚፈጥሩ፣ የጤና ባለሙያዎች ያላቸው ሙያዊ እውቀት ወሰን ያለው በመሆኑ የተነሳ በሽተኛውን ከሕመሙ በተቻለ ፍትነት እንዲያገግም ባለማድረጋቸው የተነሳ በሚፈጠር የመረበሽ ስሜት እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች የሕክምና ባለሙያዎችን እንደ ሚያጋጥማቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ የሕክምና ባለሙያዎች እያከናወኑት የሚገኘው ከፍተኛ ተግባር በመሆኑ የተነሳ ምስጋናን እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

እናንተ የጤና ባለሙያዎች እያከናወናችሁት የምትገኙት ከፍተኛ የሆነ መልካም ተግባርን ከግንዛቤ በማስገባት  ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ለታካሚዎቸ የማስተላልፈው መልእክት እናንተ እያደረጋችሁት ለምተገኙት መልካም ተግባራት ታካሚዎች እውቅና በመስጠት እናንተን ማመስገን እንደ ሚጠበቅባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስነታቸው እናንተ ታካሚዎች እናንተን በማገዝ ላይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እንደ እናንተ ሰው መሆናቸውን መረዳት ይኖርባችኃል፣ ከጤና ባለሙያዎች ሁል ጊዜ ፈግግታን አትጠብቁ፣ እናንተም ብትሆኑ በሕመማችሁ ውስጥ ሆናችሁ የተቻላችሁን ያህል ፈገግታ ለጤና ባለሙያዎች ማሳየት ይኖርባችኃል ካሉ በኃላ የጤና ባለሙያዎች እያከናወኑ የሚገኙት ተግባር ከፍተኛ ምስጋና እንደ ሚገባው ከገለጹ በኃላ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው “እባካችሁ ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” በማለት ከተማጸኑ በኃላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.