Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ምስጢረ ንስሐ በምንገባበት ወቅት የሚጠብቀን ማስፈራሪያ ሳይሆን ይቅርታ ነው

ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባደርጉበት ወቅት

01/03/2018 13:10

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ምስጢረ ንስሐ በምንገባበት ወቅት የሚጠብቀን ማስፈራሪያ ሳይሆን ይቅርታ ነው ማለታቸው ተገለጸ።

ጌታ ሁላችን መጥፎ የሆነ የሕይወት መስመራችንን እንድንቀይር ከመጥራት መቼም ቢሆን ታክቶ አያውቅም ያሉት ቅዱስነታቸው በተቃራኒው ቀስ በቀስ ወደ እርሱ እንድንመለስ በሚጣፍጥ መልኩ ወደ እርሱ እንድንምለስ ያደርገናል ብለዋል።

አሁን ያለንበት የዐብይ ጾም ወቅት መነፈሳዊ ለውጥ የምናመጣበት እና እግዚኣብሔርን የምንቀርብበት ወቅት መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም በበኩላችን ጌታ ሕይወታችንን መቀየር የምያስችል ጸጋ ይሰጠን ዘንድ ልንልመነው ይገባል ብለዋል።

በእለቱ በቀዳሚነት ከትንቢተ ኢሳያስ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በተገለጸው፣ ነብዩ ኢሳያስ የሰው ልጆች ሁሉ የሕይወት መስመራቸውን እንዲቀይሩ፣ ወደ እግዚኣብሔር እንዲመለሱ እግዚኣብሔር ያቀረበላቸውን ጥሪ የሰው ልጆች ሁሉ እንዲቀበሉ በሚያሳስበው የትንቢት ቃል ላይ ተመስርተው ስብከተቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሐጥአታችን የተነሳ ኢየሱስ እኛን ከመንቀፍ ይልቅ ለየት ባለ ሁኔታ ጣፋጭ በሆነ መልኩ ወደ እርሱ እንመለስ ዘንድ ይጠራናል መንጉድንም ያሳየናል ካሉ በኃላ እግዚኣብሔር በነቢዩ ኢሳያስ አማካይነት “ኑ እና እንወያይ” በማለት ለሰዶም እና ለጎሞራ ሕዝቦች ተናግሮ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ክፉ የሆነውን የሕይወት አካሄድ በመተው መልካሙን የሕይወት አቅጣጫ ይከተሉ ዘንድ በትህትና ለሕዝቡ ጥያቄ ማቅረቡን ቅዱስነታቸው በዋቢነት ገለጸዋል። ይህንንም በተምለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል፡

ኑና እንዋቀስይላል እግዚአብሔርአንድ አባት ወጣት ልጁ ጥፋት በሚያጠፋበት ወቅት ይገስጸዋል እንጂ ዱላ አንስቶ ሊመታው አይፈልግም። ምክንያቱም ዱላ ልጁን ይበልጥ እንዲሸሽ ያደርገዋል እንጂ በአባቱ ላይ ያለውን መተማመን አይጨምርለትም። በተመሳሳይ መልኩ እግዚኣብሔር እኛን ልጆቹንኑና እነወቃቀስ፣ ኑና እንወያይ፣ አትፍሩ ወደ እኔ እኔ በዱላ አላስፈራራችሁምይለናል እንጂ እንድንፈራ አያደርገንምኃጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናልይለናል እንጂ እግዚኣብሔር በፍጹም እኛን አያስፈራራንም።

አንድ አበት ወጣት የሆነውን ልጁን ወደ መልካም ጎዳና እንዲመለስ እንደ ሚገስጸው ሁሉ፣ ኢየሱስም በተመሳሳይ መልኩ በእርሱ ተማምነን በምሕረቱ ታግዘን ልባችንን እንድንቅየር በትዕግስት ይጠባበቀናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው፣ የዜኪዮስን እና ሌዊ በመባል ይታወቅ የነበረው ቀራጭ የነበረው ማቴዎስ ታሪክን በዋቢነት መመልከት እንደ ሚችላ ገልጸው ኢየሱስ በተመሳሳይ መልኩ እኛ ሕይወታችንን እንድንቀይር፣ ቀስ በቀስ ወደ እርሱ እንድንመለስ ይረዳናል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል፡

መልካም ስለ ሆነ እግዛኢብሔርን ልናመሰግን ይገባናል። እርሱ ልያወግዘን ሊፈርድብን አይፈልግም። ለእኛ ሕይወቱን ሰጥቷል ይህ የእርሱን መልካምነት ያሳያል። እርሱ ሁልጊዜ ወደ እኛ ልብ ልያደርሰው የሚችለውን መንገድ ይፈልጋል። እኛ ካህናት ኢየሱስ የሰጠንን መንፈሳዊ አላፊነት ተጠቅመን ምስጢረ ንስሐን በምናስገባበት ወቅት ይህንን የኢየሱስን ባሕሪይ መከተል ይኖርብናል፣ የእርሱን መልካምነት በመከተል ንስሐ የሚገባ ሰው መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጣ ልናግዘው የገባል፣ እግዚኣብሔርኑና እንወቃቀስ፣ አትፍሩ ለኃጢያታችሁ ይቅርታን ታገኛላችሁእንዳለን ሁሉ ካህኑም ንስሐ የሚገባውን ሰው ማውገዝ እና ማስፈራራት ሳይሆን የሚኖርበት በትዕግስት ኃጢያተኛው ከሐጢያት መንገዱ እንዲመለስ ማድረግ ይገባል።

 ካሉ በኃላ ስብከታቸውን አጠቅለዋል።

 

01/03/2018 13:10