2018-02-20 12:52:00

"የዐብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን የሚፈታተኑዋትን ነገሮች ለይተን የምናውቅበት ወቅት ነው"


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው ቅድስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት በየካቲት 11/2010 ዓ.ም. በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል 1፡12-15 ላይ  ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ወደ በረሃ ሄዶ በእዚያው ለ40 ቀናት ይህል መቆየቱን በሚያወሳው የቅድሱ ወንጌል ክፍል ላይ ተመስርተው ቅዱስነታቸው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት ይህ ያለንበት የዐብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን  የምፈታተኑዋትን ነገሮች ለይተን የምናውቅበት፣ የሚፈታተኑንን ነገሮች በማሸነፍ መንፈሳዊ ለውጥ የምናመጣበት መልካሙን ዜና የምናውጅበት ወቅት እንዲሆን ቅዱስ ወንጌል  ይጋብዘናል ብለዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላልችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  አድርገውት የነበረውን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አርፈዳችሁ።

በእዚህ በመጀመሪያ የዐብይ ጾም ሳምንት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 112-15) መፈተን፣ መለወጥ እና መልካም ዜና የሚሉትን ሦስት ዋና ዋና ጭብጦችን ያቀርብልናል። ወንጌላዊው ማርቆስወዲያውም መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ በረሓ መራው፤ በሰይጣንም እየተፈተነ አርባ ቀን በበረሓ ቈየ። ከአራዊትም ጋር ነበር፤ መላእክትም አገለገሉት (ማርቆስ 112-13) በማለት በዛሬው ወንጌል ስገልጽ እናያለን። ኢየሱስ የእዚህ ዓለም ተልእኮውን በያፍ ለመጀመር ያስችለው ዘንድ ለመዘጋጀት ወደ በረሃ ሄደ። ኢየሱስ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት  አያስፈልገውም ነበር፣ ነገር ግን የሰውነት ባሕርይው የራሱ እና የአባቱን ፈቃድ በመፈጸም ለመታዘዝ ለእኛ ሳይቀር ፈተናዎችን ማለፍ የሚያስችለንን ጸጋ ለመስጠት በማሰብ በእዚህ ፈትና ውስጥ አለፈ። ይህ ኢየሱስ ያደርገው ዝግጅት የተመሰረተው ከክፉው መንፈስ ጋር ማለትም ከዲያብሎስ ጋር በተደረገ ግብ ግብ ነው። ለእኛም ቢሆን ይህ የዐብይ ጾም ወቅት መፈሳዊጭንቀትበውስጣችን የሚያድርበት፣ መንፈሳዊ ግብግብ የምናደርግበት፣ ክፉ የሆኑ መንፈሶችን በጸሎት እና በእግዚኣብሔር እርዳታ በብቃት የምንመክትበት፣  በእለት ኑሮዋችን ክፉ መንፈስ የምናሸንፍበት ወቅት እንዲሆን ተጠርተናል። እንደምናውቀው ክፉ መንፈስ በእኛ ሕልውና እና በአቅራቢያችን እየሠራ ይገኛል፣ ይህም በሁከት፣ ሌላውን ሰው በማግለል፣ ራሳችንን ለሌሎች ዝግ በማድረግ፣ በጦርነቶች፣ በኢፍትሃዊ ድርጊቶች እየተገለጸ ይገኛል። እነዚህ ነገሮች ሁሉ የክፉ መንፈስ ተግባር ውጤቶች ናቸው፣ ክፉ የሆኑ ነገሮች ናቸው።

ኢየሱስ በምድረ በዳ ከተፈተነ በኋላ ወዲያውኑ ወንጌልን መስበክ ጀመረ፣ ይህም ማለት የምሥራቹን  ቃል መስበክ ጀምረ፣ ይህም በዛሬው ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ሁለተኛው ቃል ነው። የመጀመሪያወመፈተንየሚለው ቃል ሲሆን ሁለተኛው ቃል ደግሞየምስራች ቃልየሚለው ነው። እናም ይህ መልካም ዜና ሰው መንፈሳዊ ለውጥ ካመጣ በኃላ የሚያገኘው እምነት ነው። ይህም በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በሦስተኛነት የተጠቀሰ ቃል ነው። ኢየሱስጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችበማለት ይሰብክ ነበር። ከእዚያም በመቀጠልንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ይገስጻቸው ነበር (ማርቆስ 115) የእግዚኣብሔር መንግሥት ስለቀረበች በእዚህ መልካም ዜና እምኑ ይለናል። በህይወታችን ውስጥ ሁል ጊዜም መለወጥ ያስፈልገናል - በየቀኑ፣ ቤተክርስቲያናችን ይህንን መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ ሁሌም ትጋብዘናለች።

እንደ እውነቱ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ወደ እግዚኣብሔር አምርተን አናውቅም፣ ስለእዚህም  አዕምሮአችንን እና ልቦናችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ እርሱ እንዲያመራ ማድረግ ይኖርብናል። ይህንን ለማድረግ ወደ ተሳሳተ መንገድ ልመሩ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ፣ ለምሳሌም  ራስ ወዳድነትን ስውር በሆነ መንገድ በመቀስቀስ እኛን የሚያታልሉንን የተሳሳቱ እሴቶችን ለመተው ድፍረት ሊኖረን ይገባል። ይልቁንም በጌታ፣ በእርሱ መልካምነት እና እርሱ ለእያንዳንዳችን ባለው የፍቅር እቅድ ማመን አለብን። የዐብይ ጾም ወቅት የመጸጸቻ ወቅት ነው እንጂ የምናዝንበት ወቅት ግን አይደለም። የእኛን የራስ ወዳድነት መንፈስ፣ አሮጌውን ማንነታችንን፣ በጥምቀታችን ወቅት ባገኘነው ጸጋ ላይ ተመስርተን ቆራጥ የሆነ እርምጃ የምንወስድበት ወቅት ነው።

እውነተኛ  ደስት ሊሰጠን የሚችለው እግዚኣብሔር ብቻ በመሆኑ የተነሳ እውነተኛ ደስታን በሀብት፣ በጊዜያዊ ደስታ፣በስልጣን . . .ወዘተ ውስጥ እውነተኛ ደስታን በመፈለግ  ጊዜያችንን ማባከን ምንም ፋይዳ የለውም።

የእኛ ምኞቶች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ የሚሆኑት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ነው። ምክንያቱም ወቅት የሰው ደኽንነት የሚረጋገጥበት እና የእግዚአብሔር ክብር የሚገለጥበት ወቅት ስለሆነ ነው። በእዚህ በመጀመሪያው የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት ቀን ላይ በጥሞና እንድናዳምጥ እና ኢየሱስ ያስተላለፈው፣ ያቀረብልንን ጥሪ ተቀብለን መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እና በወንጌል እንድናምን ይጋብዘናል። በእዚህ የመጀመሪያው የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት እለት በዓለማችን ውስጥ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ፍትህ እንዲሰፍን ዓለምን በመለወጥ የእግዚኣብሔር ጸጋ በይበልጥ በመቀበል ወደ ትንሳኤው በዓል ጉዞ እንድናደርግ ጥሪ ያቀርብልናል።

እናታችን የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት የእግዚኣብሔርን ቃል በታማኝነት መፈጸም እንድንችል እና ኢየሱስ በምድረበዳ እንዳደረገው ያለማቋረጥ እንድንጸልይ ትርዳን። ይህ የማይቻል አይደለም። የእግዚኣብሔርን ፍቅር ለመቀበል እና ሕይወታችንን እና መላውን ዓለም ለመለወጥ የሚያስችለንን ሕይወት እንድንኖር በጸጋዋ ትርዳን።

ከመላከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኃላ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት የወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል፣ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው መልኣኩ ገብሬኤል ማሪያምን ያበሰረበት የምልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ዘወትር እሁድ እለት እንደ ምያደርጉት ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በመጪው ጥቅምት 2011 ዓ.ም. በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት ለወጣቱ ትውድ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት “ወጣቶች፣ እመንት እና ጥሪን በሚገባ ልይቶ ማወቅ” በሚል መሪ ቃል በቫቲካን ለሚካሄድው 15ኛው መደበኛ የብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ዝግጅት ይሆን ዘንድ ከመላው ዓለም የተውጣጡ 300 የሚሆኑ ወጣቶች ከመጪው መጋቢት 10-15/2010 ዓ.ም. ድረስ በሮም ተገኝተው የተለያዩ ወጣቶችን የተመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት እንደ ሚወያዩ ቅዱስነታቸው ገለጸዋል። ወጣቶች በእዚህ የቅድመ መዘጋጃ ስብሰባ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ከወዲሁ ጥሪ ያቀረቡት ቅዱስነታቸው ይህ በሮም የሚደርገው የቅድመ መዘጋጃ ስብሰባ በተለያዩ ቋንቋዎች በቀጥታ በኢንተርነት ስለሚተላለፍ ይህንን ስብሰባ በተለያዩ አካቢዎች የሚኖሩ ወጣቶች በኢንተርኔት በመከታተል የነቃ ተሳስትፎ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅረበዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በመቀጠል እንደ ገለጹት ቀደም ስል በእለቱ በተነበበው  ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አድርገውት የነበረውን አስተንትኖ በድጋሚ በማስታወስ እንደ ገለጹት ይህ የያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣጥ የምንሞክርበት እና ከክፉ ነገሮች ጋር የምንዋጋበት ወቅት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው አስታውሰው ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ምክንያቶች በእየ ማረሚያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት “በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለምትገኙ ውድ መንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ የዐብይ ጾም በኢየሱስ ምሕረታዊ እይታ ውስጥ በመግባት  በእርቅ የግል ሕይወታችሁን የምታድስቡበት ወቅት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፣ ኢየሱስ እኛን ይቅር ማለት መቼም ቢሆን ታክቶ ያውቅም” ካሉ በኃላ ቡራኬን ከሰጡ  መልካሙን ሁሉ ከተመኙ በኃላ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.