2018-02-12 15:07:00

ኢየሱስ ማንም ሰው ልነካው ያልፈለገውን በሽተኛ ሰው ቀርቦ እንደ ዳሰሰው እና እንዳዳነው የእኛንም ቁስል ይፈውሳል


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው ቅድሱ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።። በእዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በየካቲት 04/2010 ዓ.ም. በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል 1፡40-45 ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የተጠቀሰው ኢየሱስ በለምጽ በሽታ የተጠቃውን ሰው መፈወሱን በሚገለጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ባደረገው አስተምህሮ እንደ ገለጹት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚያስጨንቀን እና ከሚያንገላታን እርግማን ነጻ ሊያወጣን የመጣ አምላካችን ነው ማለታቸው ተገልጹዋል። በወቅቱ በለመጽ በሽታ በአንድ ትልቅ ኃጢኣት ምክንያት በሚመጣ  እርግማን ውጤት ነው፣ ተብሎ ይታመን እንደ ነበረ ያወሱት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ግን ማንም ሰው ልናካው ያልፈለገውን በሽተኛ ሰው ቀርቦ እንደ ዳሰሰው እና ከሕመሙ እንደ ፈወሰው ሁሉ ዛሬውም ቢሆን እኛንም ከያዘን ማንኛውም ዓይነት በሽታ ነጻ ሊያደርገን ይፈልጋል ብለዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራና እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመስርተው ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

ከባለፉት ሳማንታት ጀመሮ በነበሩት የእለተ ሰንበት ምንባባት ውስጥ ኢየሱስ በተለያየ ዓይነት በሽታዎችን እየፈወሰ እንደ ነበረ ወንጌላዊው ማርቆስ ይተርክልናል። በእዚህም ሁኔታ ይህ ኢየሱስ የፈጸመው የፈውስ ተግባር በዛሬው ቀን ማለትም በጥር 4/2010 .. የሉርድ ማሪያም የመታሰቢያ በዓል ጋር ተያይዞ በምከበረው የበሽተኞች ቀን ጋር በተያያዘ መልኩ ይከበራል። ሰለእዚህ የልባችንን እይታ ማሪያም በሉርድ የተገለጸችበትን የማሻምቤል ዋሻ እንዲመለከት በማድረግ ኢየሱስ በእውነት የሰዎችን አካል እና ነብስ ለመፈወስ ወደ ዓለም የተላከ ሃኪማችን መሆኑን በማሰብ፣ የሰውን ዘር  በኃጢያቱ እና በኃጢያቱ ውጤት ምክንያት ከሚደርስበት መከራ እንዲፈውሰው እግዚአብሔር ኢየሱስን ወደ ዓለም እንደ ላከው ማሰላሰል ይኖርብናል።

በዛሬው እለት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 140-45) አንድ በለምጽ በሽታ የተያዘ ሰው  ከእዚህ ከያዘው በሽታ እንደ ተፈወሰ ይተርክልናል፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የእዚህ ዓይነቱ በሽታ በወቅቱ በነበረው በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ርኵስ እንደ ሆነ ይታመን ስለነበር ከቀሪው የማኅበረሰብ ክፍል ተለይቶ ብቻውን እንዲኖር ይደርግ ነበር። የእዚህ ዓይነቱ ሰው ቅጣት የሚጣልበት ሲሆን ይህም የሚደረግበት ምክንያት በእዚህ ዓይነት በሽታ የተጠቃ ሰው በሰዎች ፊት ብቻ ሳይሆን በእግዚኣብሔር ፊትም ሳይቀር ርኩስ እንደ ሆነ ይቆአጠር ስለነበረ ነው። በእግዚኣብሔርም ፊት ሳይቀር። ለእዚህም ነው ታዲያ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው (ማርቆስ 140-45) ይህ በእዚህ የለምጽ በሽታ የተጠቃው ሰው ኢየሱስንብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህበማለት በእግሩ ሥር ወድቆ የለመነው  በእዚሁ ምክንያት ነው።

ኢየሱስም ይህንን በሰማ ወቅት ለሰውየው ራራለት። በእዚህ በኢየሱስ ውስጣዊ ባሕሪ ላይ ማተኮር በጣም አስፈላጊ ነው፣ ይህንንም ባሳለፈነው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በሚገባ የተመለከትነው ጉዳይ ነበር። በርኅራኄ እና በምሕረት ወደ ተሞላው ወደ ኢየሱስ ልብ በጥልቀት ካልገባን በስተቀር ኢየሱስ የሚፈጽመውን ተግባራት፣ ወይም ደግሞ  ኢየሱስን ራሱን መረዳት ባጣም ይከብደናል። እነዚህ ነገሮች ናቸው እንግዲህ (ማለትም ርኅራኄ እና ምሕረት) ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ እንዲዳስሰው የናሳሳው እና  “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” በማለት የተናገረውም በእዚሁ ምክንያት ነው። በእዚህ ሁኔታ ውስጥ በጣም አስደንጋጭ የሆነው እውነታ ኢየሱስ በሙሴ ሕግ መሰረት ሙሉ በሙሉ የተከለከለውን ሕግ በመተላለፍ የለምጽ በሽታ የያዘውን ሰው መንካቱ ነው። በወቅቱ አንድ በለምጽ በሽታ የተያዘ ሰውን መንካት ማለት በሥጋ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ሳይቀር መርከስ ማለት ተደርጎ ይቆጠር ስለነበር ይህንን የምያደርግ ሰው ሙሉ በሙሉ ርኩስ ተድርጎ ይቆጠር ነበር።

ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ኢየሱስ ይህንን በለምጽ በሽታ የተያዘውን ሰው በመንካቱ የተነሳ ለምጹ  ከበሽተኛው ወደ ኢየሱስ በመተላለፍ ኢየሱስን አልበከለውም፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ወደ በሽተኛው ሰው የተላለፈው መንፈስ በሽተኛውን ከበሽታው አነጻው። በእዚህም የፈወስ ሂደት ውስጥ እኛ የምናደንቀው ኢየሱስ ያሳየውን ምሕረት እና ርኅራኄ ብቻ ሳይሆን በተላላፊ በሽታ መበከል የሰውን ዘር ከምያስጨንቀው እርግማን የሰውን ዘር ነጻ ለማድረግ የምፈልገውን የኢየሱስን ድፍረት እንመለከታለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ማንኛውም ዓይነት በሽታ የሚደርስብን በመርከሳችን የተነሳ አይደለም፣ በሽታ የሰው ልጆችን ሁሉ የምያካትት ቢሆንም ነገር ግን በምንም መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት አይነካም ወይም አይገድብም። እንዲያውም በተቃራኒው አንድ የታመመ ሰው ከአምላክ ጋር ይበልጥ አንድ መሆን ይችላል። እኛን የምያረክሰን ኃጢያት ብቻ ነው! ራስ ወዳድነት፣ ኩራት፣ ወደ ሙስና ዓለም ውስጥ መግባት፣ እነዚህ ልባችንን የሚያሳሙሙ በሽታዎች ናቸው፣ ከእነዚህ በሽታዎች መፈወስ ግድ ይለናል፣ ልክ እንደ ለምጻሙ ሰው ወደ ኢየሱስ በመቀረብብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላልህ!” ብለን ልንጠይቀው ይገባል።

እስቲ አሁን ደግሞ እያንዳንዳችን ለአንድ አፍታ ጸጥ እንበል-እናንተም-አንተም-እኔም ስልቀር እስቲ ለአፍታ ዝም እንበል፣ በልባችን እናስብ፣ ውስጣችንን እንመልከት በውስጣችን ያለውን ርኩስ ነገር እንመልከት፣ የየግላችንን ኃጢኣቶች እንመልከት። እያንዳንዳችን በዝምታ፣ ነገር ግን በልባችን ለኢየሱስብተፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህብለን እንጠይቀው። እስቲ ሁላችንም ይህንን  በዝምታ እንበለው።ብተፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ!”! “ብተፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ”! እንበል።

በተጸጸተ ልብ ወደ ምስጢረ ንስሐ በምንቀርበበት ወቅት ሁሉ ጌታም በበኩሉፈቅጃለሁ ንጻ”! በማለት ይመልስልናል። በእዚህ እንዴት ደስ የሚል ደስታ የገኝ ይሆን! በእዚህም የኃጢኣታችን ለመጽ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፣ አተነው የነበረውን የልጅነት መብት በድጋሚ በመጎናጸፍ ከእግዚኣብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት መልሰን እናድሳለን፣ ከማኅበርሰቡ ጋርም ሳይቀር ሙሉ በሙሉ ተመልሰን  እንቀላቀላለን።

ለበሽተኞች ፈወስን፣ ውስጣዊ ቁስሎቻችንን በማያልቀው ምሕረቱ እንዲያነጻን፣ ለልባችን ተስፋ እና ሰላም እንዲሰጠን ከልጇ ዘንድ እንድታማልደን ያለ አዳም ኃጢኣት በተጸነሰችሁ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት እንማጸናለን።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.