2018-02-10 16:36:00

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለ2010 ዓ.ም. ዓብይ ጾም ያስተላለፉት መልእክት


 

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 2010 .. ዓብይ ጾም ያስተላለፉት መንፈሳዊ መልእክት

ክፋት ስለሚገን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል” (ማቴዎስ 2412)

 

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መጭውን የፋሲካ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት እናከብር ዘንድ መዘጋጃ በሚደርግበት በእዚሁ አመት የአብይ ጾም ወቅት የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሕይወታቸው መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጡ፣ ባልንጀራቸውን እንደ ራሳቸው እንዲውዱ፣ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ቀረቤታ አጠናክረን እንድንቀጥል ይረዳን ዘንድ ከማቴዎስ ወንጌል 24፡12 ላይ የተጠቀሰው “ክፋት ስለሚገን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል” በሚል መሪ ቃል መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጸ።

የእዚህን መልእክት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን በማስከተል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ክፋት ስለሚገን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል” በሚል መሪ ቃል ለእዚህ ዓመት የአብይ ጾም አስተንትኖ ይሆነን ዘንድ ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

በድጋሚ የእዚህ ዓመት የፋሲካ በዓል በጣም ቀርቡዋል። ለፋሲካ በዓል በምንዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት እግዚኣብሔር በመለኮታዊ ጥበቃው ይህንን የዓብይ ጾም ወቅት መዘጋጃ ይሆነን ዘንድ በመስጠትበምስጢራት የታጋዘ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣይጋብዘናል። ይህ የዓብይ ጾም ወቅት እኛ ወደ እግዚኣብሔር በሙሉ ልባችን፣ ማንኛውንም ዓይነት የሕይወት አካሄዳችንን ወደ እርሱ እንድንመልስ ዘንድ ይጠራናል ይህንንም ለውጥ እንድናደርግ ያበቃናል።

በእዚህ መልእክት በዚህ አመት እንደገና መላውን ቤተክርስትያን በእዚህ በዓብይ ጾም ወቅት በሚገኘው ጸጋ በመታደስ፣ በደስታና በእውነት ውስጥ መኖር ይችሉ ዘንድ ለማገዝ እሻለሁ። ይህንንም ለማድረግ ያስችለኝ ዘንድ ይህንን መስመር የምጀመረው ኢየሱስ ከማቴዎስ ወንጌል 2412 ላይ በተጠቀሰውክፋት ስለሚገን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛልበምለው መሪ ቃል ነው።

እነዚህ ቃላት የመጡት ኢየሱስ ሰለ መጨረሻው ጊዜያት በሰበከበት ወቅት ነበር። እነዚህ ቃላት የተስበኩት በኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በኢየሱስ ላይ የሚደርሰው መከራ ከሚጀምርበት ሥፍራ ነው። ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈልጎ ኢየሱስ ታላቁ መከራ እንደሚመጣ እና አማኝ የሆነው የማኅበረሰብ ክፍል ራሱን እንዲያዘጋጅ በማሰብ፣ ታላቅ የሆነ መከራ እንደ ሚገጥማቸው፣ ሀሰተኛ ነቢያት ሰዎችን በተሳሳተ መንግድ እንደ ሚመሩዋቸው ለማሳሰብ ፈልጎ የነበረ ሲሆን፣ እናም የወንጌል ዋናው ማዕከል የነበረው ፍቅር በበርካታ ሰዎች ልብ ውስጥ ቀዝቅዞ እንደ ነበረ ለማመልከት ፈልጎ ነው።

 

 

ሐሰተኛ ነብያት

እስቲ የቅዱስ ወንጌልን ክፍል እንመልከት እና እነዚህ ሐሰተኛ ነብያት የሚባሉት እነማን እንደ ሆኑ እንገነዘብ። እንደአታላይ እባብሆነው በመቅረብ  የሰው ልጆችን ስሜት በመጫን፣ የእነርሱ አስተሳሰብ ባሪያ በማድረግ ወደ ፈለጉበት ቦታ የሚመሩዋቸው ሰዎች ናቸው። በጣም በርካታ የሆኑ የእግዚኣብሔ ልጆች በጊዜያዊ ደስታ እየታለሉ እውነተኛ ደስታን ስያጡ እንመለከታለን።  ስንት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ናቸው የገንዘብ ትርፍ ባሪያ ብቻ የሚያደርጋቸውን እና የፍጆታ ቁሳቁሶችን ብቻ ማስገኘት የሚችለውን ሐብት እያለሙ የሚኖሩ ስንቶች ናቸው! ስንቶች ናቸው ራሳቸው ተጨማሪ ነገር የማያስፈልጋቸው፣ ራሳቸው በራሳቸው ሙሉ የሆኑ ሰዎች አድርገው በመቁጠር የሚኖሩ ፣ነገር ግን በመጨረሻ በብቸኝነት መንፈስ ውስጥ ገብተው የምሰቃዩ ሰዎች ስንት ናቸው!

ሐሰተኛ ነብያት ብዙም ጊዜ ለመከራዎች ሁሉ ባዶ የሁኑ እና የማይጠቅሙ ቀላል እና ፈጣን የሆኑ መፍትሄዎችን በማቅረብ የምያታልሉቀማኞችናቸው።

በአደገኛ አደንዣዥ ዕጾች፣ ተጋላጭ ለሆኑ ጾታዊ ግንኙነቶችን በፍጥነት፣ ነገር ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመሮጥ ሂደት ወስጥ ስንት ወጣቶች ይወሰዳሉ! ግንኙነታቸው ፈጣን የሚመስል እና ቀጥተኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በምያዩት እውነተኛ ባልሆነ "ምናባዊ" ህይወት ውስጥ የሚኖሩ ስንቶቹ ናቸው! እነዚህ አጭበርባሪዎች እውነተኛ ዋጋ የሌላቸው ነገሮች በሚያሽከረክሩበት ጊዜ በሰዎች ዘንድ እጅግ ውድ የሚባሉ ለምሳሌም እንደ  ክብር፣ ነፃነት እና ፍቅር የመሳሰሉ የሰው ልጆች እሴቶችን ይሰርቃሉ። በውጫዊ ገጽታችን እንድንኩራራ ይገፋፉናል፣ በመጨረሻም ያታልሉናል። በእዚህም በፍጹም መገረም የለብንም። የሰውን ልብ ለማስደመም በዩሐንስ ወንጌል 844 እንደ ተጠቀሰውሐሰተኛ እና የሐሰትም አባትበመሆን  ክፉን ነገር እንደ መልካም ሐሰትን ደግሞ እንደ እውነት አድርገው ያቀርባሉ። ለዚህም ነው እያንዳንዳችን ወደነዚህ ሐሰተኛ ነብያት ውሸቶች እየተጓዝን እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ ለመመልከት ወደ ልባችን እንድንመለከት የምጋብዘው በእዚሁ ምክንያት ነው።

ውስጣችንን በጥልቀት መመርመርን እና መልካሙን እና ዘላቂውን ምልክት በልባችን ውስጥ መተው እንድንችል መማር አለብን ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት እና ለእኛ ጥቅም ሲባል ጭምር ነው።

 

የቀዘቀዘ ልብ

ዳንቴ አልጊዬሪ (13ኛው ክፍለ ዘመን የኖረ ገጣሚ፣ ጸሐፊ እና ፖሌቲከኛ የነበረ ጣልያናዊ ሰው ነበር) ገሃነምን በተመለከተ ስለ ገሃነም በሳለው ስዕል ላይ ዲያቢሎስ በበረዶው ዙፋን ላይ ተቀምጦ በረዶ ሆኖ እና ፍቅር የሌለው ገለልተኛ ሰው አድርጎት በማስቀመጥ ስሎት ነበር። በውስጣችን ያለው ፍቅር እንዴት ልቀዘቅዝ ቻለ በማለት ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። ይህም በውስጣችን ያለው ፍቅር እየቀዘቀዘ መሄዱን የምያሳይ ምልክት ነው።

ከሁሉም በላይ ደግሞ በውስጣችን ያለውን ፍቅር የምያበላሸውለገንዘብ ያለን ፍቅርሲሆን ይህም 1 ጢሞቴዎስ 610 ላይ እንደ ተጠቀሰውየክፋት ሁሉ ሥርነው። ከእዚያም በመቀጠል ከእግዚኣብሔር እና እርሱ ከሚስጠን ሰላም መራቅ እንጀምራለ፣ እግዚኣብሔር በቃሉ እና በምስጢራቱ ከሚሰጠን ምቾት በመራቅ የራሳችንን ምቾት እንፈልጋለን። በማህጸን ውስጥ ያለ ሕጻን፣ አዛውንቶች እና በሽተኞች፣ ስደተኞች፣ በመካከላችን የሚኖሩ ግን ለእኛ ባዕድ የሆኑ ሰዎች፣ ከእኛ እኩል እንደ እኛ ምኖር ያልቻሉ ጎረቤቶቻችን   ከእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ወጣ ባለ መልኩ የሚያስቡ ሰዎችን ሁሉ ለእኛ አደገኛ እንደ ሆኑ በማሰብ መጠራጠር እንጀምራለን።

ተፈጥሮ በራሷ ይህንን እየቀዘቀዘ ያለውን ፍቅር ትረዳለች። መሬታችን በእኛ እንቢተኛነት ተመርዛለች፣ በቸልተኝነት እና የራስን ጥቅም ብቻ በማሳደድ ተበዝብዛለች። በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ለአስገዳጅ ስደት የተዳርጉ ስደተኞችን በሚያመላልሱ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ጀልባዎች ምክንያት በሰጠሙ ስደተኞች ምክንያት ባሕር ተበክሉዋል። በእግዚኣብሔር እቅድ መሰረት ለእርሱ የሚቀርበው ዝማሬ ያምያርግበት ሰማይ በራሱ ሞትን በሚያፍጥኑ በራሪ ነገሮች (አውሮፕላኖች) ተጨናንቁዋል።

በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለው ፍቅር ራሱ በጣም እየቀዘቀዘ መጥቱዋል። በቅርቡ ሄቫንጄሊ ጋውዲዩም (የወንጌል ሐሴት) በሚል አርእስት በጻፍኩት ቃለ ምዕዳን ውስጥ እንደ ጠቀስኩት በማኅበረሰቡ ውስጥ ፍቅር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን በአንጻሩም ራስ ወዳድነት፣ መነፈሳዊነትን ማጉደፍ፣ መጭው ጊዜ ጨለማ እንደ ሆነ ማሰብሁሉንም ነገር ለራሳችን ብቻ ለማጋበስ ማሰብ እርስ በራሳችን ያለአጋቡ መወዳደር መፎካካአር፣ ቆንጆ መስለን ለመታየት ብቻ በመፈለግ ዓለማዊ የሆኑ አስተሳሰቦችን  መቀራመት ከቀን ወደ ቀን ለሐዋሪያዊ  ተልዕኮ ያለን ፍላጎት እየቀነሰ መምጣት እነዚህ እና እነዚህ ምልክቶች ናቸው።

 

ታዲያ ምን ማድረግ አለብን?

ምን አልባት ቀደም ሲል የጠቀስኩዋቸውን ፍሬ ሐሳቦች በውስጣችሁ እና በሁለንተናቸው የተረዳችሁ ይመስለኛል። ነገር ግን እናታችን እና አስተማሪያችን የሆነችው ቤተክርስትያን መራራ ከሆነ የእውነት መድኃኒት ጋር በመቀናጀት፣ በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት በጸሎት፣ ምጽዋት በመስጠት እና በጾም የሚገኘውን ጸጋ እንድንቀበል ትጋብዘናለች።

ለጸሎት ያለንን ጊዜ ከፍ በማድረግ ለጸሎት ተጨማሪ ጊዜን በመስጠት በሚስጥር የምንሰራቸውን ሚስጥራዊ ውሸታችንን እና እራስን የማታለል ተግባሮቻችን ከልባችን ውስጥ እናስወግዳለን፣  ከዚያም እግዚአብሔር የሚያቀርበውን መጽናኛ እናገኛለን። እርሱ አባታችን በመሆኑ የተነሳ ሕይወታችንን በምልአት እንድንኖር ይፈለጋል።

ምጽዋት መመጸውት ከስግብግብነት ነፃ ያደርገናልን እናም ጎረቤታችንን እንደ ወንድም ወይም እህት አድርገን እንድንመለከትም ይረዳናል። ያለኝ ነገር ሁሉ የእኔ የብቻዬ አይደለም። ክርስትቲያን እንደ መሆናችን መጠን፣ የሐዋሪያትን መልካም ምሳሌ በመከተል እና ያለንን ከሌሎች ጋር በመካፈል የቤተክርስቲያኖናችንን ተጨባጭ ምስክርነት እና ኅብረት መግለጽ እንዴት ደስ ያሰኛል። በእዚህ ረገድ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በኢየስሩሳሌም ለሚኖሩ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች የሚውል ምጽዋዕት እንዲሰበስቡ የጻፈላቸውን የማበረታቻ መልእክት መጥቀስ እፈልጋለሁ (2ቆሮ.810) በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት በትክክል ልናደርገው የሚገባው ጉዳይ ይህ ነው፣ ብዙ ሰዎች ምጽዋዕትን ሰብስበው ቤተክርስቲያንን እና የተቸገሩ ሰዎችን ማረዳት ይኖርባቸዋል። ሆኖም የእኛን እርዳታ ከሚማጸኑ ሰዎች ጋር በየቀኑ ስንገናኝ፣ እንደ እነዚህ ያሉ ተማጽኖዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚመጡ እመለከታለን። ምጽዋዕት በምንሰጥበት ወቅት ሁሉ የእግዚኣብሔርን መለኮታዊ ጥበቃ ከሁሉም ጋር እንቋደሳለን ማለት ነው። እግዚአብሔር በእኔ በኩል አንድ ሰው ዛሬ ቢረዳ ነገ እኔን ሲቸግረኝ ደግሞ እንዴት አይረዳኝ? እግዚአብሔር በተሻለ ሁኔታ ደግ የሆነ ማንም ሰው የለም።

ጾም ለቁጣ ወይም ለረብሻ ያለንን ዝንባሌ ያዳክመዋል፣ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድንላቀቅ በማድረግ ለእድገታችን ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። በአንድ በኩል ችግረኞች እና ረሃቦችን ለመቋቋም እንድንችል ያደርገናል። በሌላ በኩል ደግሞ እኛ ለእግዚአብሔር  ያለንን መንፈሳዊ ረሃብ እና ጥማት ይገልጻል። ጾም እንድንነቃ ያደርገናል። ይህም የእራሳችንን ፍላጎት ማርካት የሚስችለንን እግዚአብሔርን የመታዘዝ ምኞታችንን ያድሳል።

በተጨማሪም ከካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ባሻገር በመሄድ እና በጎ ፈቃድ ላላችሁ ሰዎች ሁሉ የእግዚኣብሔርን ድምጽ እንድትሰሙ እጋብዛችኃለሁ። እናንተም ልክ እንደ እኛ በዓለም ውስጥ በሚታዩ ብልሹ ነገሮች እንደ ተረበሻችሁ፣ ልብን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀዘቅዝ እና ደንዳና  እንዲሆን በሚያደርጉ ተግባራት፣ የሰው ልጆች ሁሉ የአንድ ቤተሰብ ልጆች የመሆናችንን መንፈስ የሚያዳኩም ነገሮች እናንተንም እንደ ሚረብሽዋችሁ እምናለሁ። እንግዲያውስ ለተቸገሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የተቻለንን እርዳታ በማድረግ በጾም ወደ አምላክ በምናደርገው ልማና አብራችሁን ሆናችሁ እንድትጸልዩ እናማጸናለን።

 

የፋሲካ እሳት

ከሁሉም በላይ የቤተክርስቲያኗ አባላት በእዚህ በዓብይ ጾም ወቅት የምናደርገውን ጉዞ ምጽዋት በመስጠት፣ በጾም እና በጸሎት መነፈስ በተቀናጀ መልኩ በጉጉት እንዲደረግ ማስቻል ይኖርባቸዋል።

አንዳንድ ጊዜ በልባችን ውስጥ የሚገኘው የልግስና እሳት በሚሞትበት ወቅት፣ ይህ ነገር የእግዚኣብሔር የሆነ ልብ ውስጥ በፍጹም እንደ ማይከሰት ማወቅ ይኖርብናል። እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ ቀጣይነት ባለው መንፈስ በአዲስ መልኩ የምንወድበትን መንፈስ ይሰጠናል።

እንዲህ ዓይነቱ የጸጋው ወቅት በዚህ ዓመት "24 ሰዓታት ለጌታ" በሚል ተነሳሽነት ጠቅላላው የቤተክርስቲያኗ ማህበረሰብ የእርቅ ምስጢር የሆነውን ምስጢረ ንስዐን ከቅዱስ ቁርባን አምልኮ ጋር በማቀናጀት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የካቲት 30 እና መጋቢት 1 ቀን 2010 .. በመጽሐፈ መዝሙር 130: 4 የተቀሰውነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለበሚለው ቃል አነሳሽነት የሚደርገው ጸሎት ላይ ሁላችንም እንድንካፈል ቤተክርስትያን ጥሪ ታቀርባለች።  በእዚህም መሰረት በእያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ አንዱ 24 ሰዓታት ያህል ክፍት በመሆን የቅዱስ ቁርባን ስገደት እና የምስጢረ ንስሐ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣሉ።

በፋሲካ በዓል ዋዜማ ላይ የፋሲካ በዓል የብርሃን ምልክት የሆነውን ሻማ የማብራት ስነ-ስረዓት እናከናውናለን። ከእዚህ "ከአዲሱ እሳት" የወነጨው ይህ ብርሃን ቀስ በቀስ ጨለማን ያሸንፋል እንዲሁም ቀስ በቀስ ስርዓት አምልኮዋችን በብርሃን የተሞላ እንዲሆን ያደርጋል።

"ከሙታን የተነሳው የክርስቶስ የብርሃን በክብር በእኛ ልብ እና አእምሮ ውስጥ ያለውን ጨለማ ያብራለእያንዳንዳችንም ወደ ኤማዎስ በመሄድ ላይ የነበሩትን የሁለቱን ደቀ-መዛሙርት ተመክሮ ለእኛም ይግለጽልን ዘንድ እንመኛለን። የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት እና ከመንበረ ታቦቱ ላይ ከሚገኘው በቅዱስ ቁርባን ተመግበን ልባችን በእምነት በተስፋ እና በፍቅር  የተማላ ይሁን።

በታላቅ ፍቅር ሁላችሁንም በጸሎቴ እንደማስታውሳችሁ እያረጋገጥኩኝ ቡራኬዬ እንዲደርሳችሁ ምኞቴ ነው። እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.