Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

"ኢየሱስ በየመንገዱ የሚያገኛቸውን ሰዎች እመነት እያነቃቃ፣ ከበሽታቸው እየፈወሰ በእየመንገዱ ይዘዋወር ነበር"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ። - AP

05/02/2018 17:20

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው ቅድሱ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።። በእዚህ መሰረት በትላንትናው እለት በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል 1፡21-39 ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት ኢየሱስ በየመንገዱ የሚያገኛቸውን ሰዎች እመነት እያነቃቃ፣ ከበሽታቸው እየፈወሰ በእየመንገዱ ይዘዋወር እንደ ነበረ ገልጸዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ

በዛሬው እለተ ሰነበት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 121-39) ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም መሄዱን፤ አይሁዳውያን ሳምንታዊ በዓል በሚከበርበት በሰንበት ቀን ወደ ኢየሱስ ያከናወናቸውን ድርጊቶች ይዘረዘራል። በዚህ ጊዜ ወንጌላዊው ማርቆስ የኢየሱስ የመፈወስ ተግባር እና ኢየሱስን በተገናኙት ሰዎች መካከል ያለውን እምነት በማጉላት ያሳየናል። በእርግጥ ኢየሱስ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎችን በመፈወስ ኢየሱስ የሕዝቡን እምነት ማነቃቃት ፈልጎ ነበር። በወቅቱ ኢየሱስ በቅፍርናሆም ያደርገውን ቆይታ የጀመረው የስምዖን አማት በመፈወስ ነበር። የከተማዋ ሕዝብ በሙሉ በቤቱ ደጅ ላይ ተሰብስቦ ነበር። 

እርሱም በተለያዩ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ። አካላዊ ሥቃይ የገጠማቸውን እና የመንፈስ ጭንቀት ያደረባቸው ሰዎች፣ የኢየሱስ ተልእኮ በቃላት እና በተግባር መሳካቱን በመገልጽ የሚያድን እና የሚያጽናና መሆኑንም በማሳየት  ይህም ከስተት "እጅግ አስፈላጊ’’ መሆኑን ይገልጻል። ኢየሱስ በአንድ ህክምና በሚሰጥበት የመመርመሪያ ክፍል ውስጥ ገብቶ ለማዳን አልመጣም፣ ኢየሱስ አንድ ገለልተኛ በሆነ የህክምና በሚሰጥበት የመመረመሪያ ክፍል ውስጥ ጎብቶ አለሰበከም፣ በሕዝቡ መካከል ነበረ። በብዙኃኑ መካከል ነበር የሚገኘው። ኢየሱስ በእዚህ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት አብዛኛው ሕይወቱን ያሳለፈው በመንገድ ላይ፣ በሕዝቦች መካከል፣ ወንጌልን በመስበክ፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ የሆኑ ቁስሎችን በመመፈወስ እንደ ነበረ እናስታውስ። ይህ ሕዝብ በተደጋጋሚ በመከረራ ውስጥ የኖረ መሆኑን ቅዱስ ወንጌል በተደጋጋሚ ያናገራል። በብዙ መከራዎች፣ ችግሮች እና እንግልቶች ውስጥ ሳይቀር ገብቶ የሚሰቃይ ሕዝብ ነበር፣ በእዚህ መከራ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ነጻ ለማውጣት ብቃት ያለው ኃይል ያስፈልጋል፣ ነጻ የሚያወጣ እና አዳሽ የሆነ የኢየሱስ ኃይል ያስፈልጋል። በእዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ ከእስከ ማምሻው ድረስ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል በመሆን ያንን የሰንበት ቀን ያጠንቃቀው በእዚሁ መልኩ ነው። ከእዚያን በኃላ ደግሞ ኢየሱስ ምን ሰራ?

በማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድ፣ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመረ። ኢየሱስ ይጸልያል። በዚህ መንገድ የራሱን እና ተልዕኮውን ወደ ታሪካዊ ራዕይ ይቀይረዋል፣ ይህም የእርሱ ተአምራቶችን እና የእርሱ ተዓማኒነት ያለውን ኃይል በሚገባ እንዲያሳይ አድርጎታል። እንዲያውም ተአምራት ለእምነት ምላሽ እንዲሰጡ የሚጋብዙ "ምልክቶች" ናቸው፣ ሁልጊዜ እርሱ የሚያስተላልፉቸው ቃላትን የሚያመለክቱ ምልክቶች ናቸው፣ በቃላት እና በተግባር በመገለጽ በእርሱ ላይ ያለንን እምነት በድጋሚ እንዲያንሰራራ ያደጋሉ በክርስቶስ መለኮታዊ ኃይል ጸጋ አማካይነት መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣትም ያስችላሉ። በዛሬው እለት የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የተደመደመው ኢየሱስ  የእግዚኣብሔርን መንግሥት ለማወጅ የሚያመች ተገቢው ስፍራ መነግድ ላይ መሆኑን በመግለጽ ነው። ደቀ መዛሙርቱ እርሱን ሊፈልጉት እና መልሰው ወደ ከተማ ልያመጡት ይፈልጉት ነበር፣ ኢየሱስ ለእነዚህ ደቀ መዛሙርት ምን ብሎ ነበር የመለሰው? እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው (ማር. 138) ይህ የእግዚአብሔር ልጅ መንገድ እና የእርሱ የደቀ መዛሙርቱ መንገድ ነው። ይህም መንገድ የእያንዳንዱ ክርስትያን መንገድ ሊሆንም ይገባል። መንገድ የወንጌል ምስጢራዊ አዋጅ የሚነገርበት  ስፍራ እንደመሆኑ፣ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ "መሄድ" የሚል ምልክት መከተል ይኖርባታል፣ ቤተ ክርስትያን የሕዝቡን ንቅናቄ እየተመለከተች አብራ መጓዝ ይኖርባታል እንጂ ቀጥ ብላ መቆም በፍጹም አይገባትም።

የህዝቡ ነብስና አካል አኪም የሆነውን፣ የኢየሱስን የፈውስ ቃላትን ሁሉ ለማጣጣም፣ ቤተክርስትያን በሕዝቡ ውስጥ ድንኳንዋን ሙሉ በሙሉ እንድታሰፋ የምያስችላትን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ በየቀኑ ለመስማት  ቤተክርስትያን ራሱን ክፍት ማድረግ ትችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትርዳን።

ከመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኃላ

ቅዱስነታቸው በትላንታንው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት አስተንትኖ በመቀጠል በካቶሊክ ቤተርስትያን ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን መልእኩ ገብርሄል ማሪያምን ያበሰረበት ጸልት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገቡ በኃላ ዘውትር እሁድ ቀን እንደ ሚያደርጉት ያስተላለፉት መልእክት የጀመሩት እንደ ጎርጎርሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1945 ዓ.ም. በጀርመን ሀገር ሄርስበርክ በሚባል ስፍራ በነበረው የናዚ የእስረኞች ማጎሪያ ጣቢያ ይኖር የነበረ ቴረዚዮ ኦሊቬሊ  የሚባል ወጣት በወቅቱ በወቅቱ በእዚያ የናዚ እስረኞች ማጎሪያ ጣቢያ ለፈጸመው መልካም ግድል የተነሳ የብጽሕና ማዕረግ እንደ ተሰጠው ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

እርሱ በወቅቱ ገና በጣም ወጣት የነበረ ሰው ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለደከሙ ሰዎች የክርስቶስን ፍቅር በመመስከሩ እና ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች የተስፋን ዘር በመዝራት በእዚያው በእስር ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል የወንድማማችነትን መነፈስ በመፍጠር በስቃይ ውስጥ ይገኙ ለነበሩ ሰዎች ተስፋ እንዲያደርጉ በማስተማር፣ በአሁኑ ዘመን ለሚገኙ ወጣቶች በአብነት የሚጠቀስ ምስክረነትን በመፈጸሙ፣ ለእነዚህ እና እነዚህን ለምሳሰሉ እርሱ በወቅቱ በፈጸማቸው ታላላቅ ገድሎች ምክንያት ይህ የብጽህና ማዕረግ እንደ ተሰጠው ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

በመቀጠልም “የህይወት ወንጌል ለዓለም ደስታ” በሚል መሪ ቃል በጣልያን የተከበረውን “የሕይወት ቀን” ለማክበር በእዚያ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን መልእክት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ “የህይወት ወንጌል ለዓለም ደስታ” በሚል መሪ ቃል የተከበረውን “የሕይወት ቀን” ለማክበር በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ የተገኙት ምዕመናን በቁጥር በጣም አናሳ መሆናቸውን ከጠቀሱ በኃላ በቁጥር የማነሳቸው ጉዳይ በጣም እንደ ሚያሳስባቸው ቅዱስነታቸው ተናግረዋል። ማክንያቱም አሉ ቅዱስነታቸው ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በጣም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች በሚመረቱበት በአሁኑ ወቅት፣ የሰው ልጆች ሕይወትን የሚቃረኑ ሕግጋት በሚጸድቁበት በአሁኑ ወቅት፣ በእየቀኑ የሰው ልጆች ሕይወት እንደ ዋዛ በሚቀጠፍበት በአሁኑ ወቅት ይህንን በመቃወም በተቃራኒው ደግሞ የሰው ልጆች ሕይወት ክቡር መሆኑን ለማስረዳት የሚደረገውን እንቅሳቃሴ የሚደግፉ ሰዎች በጣም ጥቂት መሆናቸው እንደ ሚያሳስባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። እባካችሁን የዓለም ሕዝብ ለእዚህ አሳሳቢ ጉዳይ በንቃት ተገቢውን ምላሽ ይሰጥ ዘንድ መጸለይ  ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ ሳይክሎን በተባለ አውሎ ንፋስ ምክንይታ በማዳጋስካር ሕይወታቸውን ላጡ እና የአደጋው ሰላባ ለሆኑ ሰዎች ሐዘናቸውን እንደ ሚጋሩ እና በጸሎት ከእነርሱ ጋር በመሆን እግዚኣብሔር መጽናናቱን እና ብርታቱን ይጸጣቸው ዘንድ እንደ ሚማጸኑ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እየተከሰቱ በሚገኙ ግጭቶች ሳቢያ እየተሰቃዩ የሚገኙትን ወገኖች ለማሳታወስ በመጭው የካቲት 16/2010 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ የጾም እና የጸሎት ቀን እንዲሆን ማወጃቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህም የጾም እና የጸለት ቀን በሁኑ ወቅት በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብልክ እና በደቡብ ሱዳን በቀጣይነት በመካሄድ ላይ ባሉት ግጭቶች ሳቢያ የባርካታ ሰዎች ነብስ እየጠፋ በርካቶችን ደግሞ ለችግር እየተዳረጉ በመሆናቸው የተነሳ ለየት ባለ ሁኔታ ለእነዚህ ሀገራት ጽሎት እንዲደርግ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ክርስትያን ያልሆናቸው ወንድሞቼ እና እህቶቼ ለእዚህ ለሰላም በምናደርገው ጸሎት ላይ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪየን አቀረባለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው ሰላም የጋራ ጉዳያችን በመሆኑ የተነሳ ሁላችንም በሕብረት፣ ጸሎታችንን ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ ይገባል ብለዋል።

ሰማያዊ የሆነ አባታችን የልጆቹን የጭንቀት እና የጭቆና ድምጽ ሁል ጊዜም ቢሆን እንደ ሚሰማ የገለጹት ቅዱስነታቸው “ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል” ካሉ በኃላ እኛም ብንሆን የእነዚህን በጦርነት እና በስቃይ ውስጥ የሚገኙ የወገኖቻችንን ጩኸት በመስማት እያንዳንዳችን በሕሊናችን ውስጥ “ሰላም ይሰፍን ዘንድ  እኔ ምን አስተዋጾ ማድረግ እችላለሁ? የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ እንደ ሚገብ ቅዱስነታቸው ገልጸው በእርግት የእያንዳንዳችን ጸሎት አስፈላጊ ቢሆንም ጸሎት ብቻ ግን በቂ አይደለም እያንዳንዳችን ማንኛውም ዓይነት ግጭቶች ለማሰውገድ የራሳችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል ካሉ በኃላ በራኬን ስጥተው ለእለቱ የነበረውን ዝግጅት አጠናቀዋል።

05/02/2018 17:20