2018-02-02 15:55:00

“በእውነት የሚገኝ ደስታ”


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅርቡ “በእውነት የሚገኝ ደስታ” በሚል አርእስት ሐዋሪያዊ ሕግጋት በሰፊው የሚንጸባርቁበት መልእክት ባለፈው ሰኞ ማለትም በጥር 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካ ይፋ ማድረጋቸው ተገለጸ።

ይህ “በእውነት የሚገኝ ደስታ” በላቲን ቋንቋ “Veritatis gaudium” በሚል አርእስት የታተመው ሐዋሪያዊ ሕግጋት በተለይም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ ጳጳሳዊ ዩንቬርሲቲዎችን እና የትምህርት ተቋማትን በቀጥታ የሚመለከት እንደ ሆነም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተለይም ደግም በእነዚህ የካቶሊክ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነገረ መለኮት፣ በፍልስፍና እና በሕገ ቀኖና እና እንዲሁም በርከት ያሉ ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፎችን በቀጥታ የሚመለክት መሆኑን ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ “በእውነት የሚገኝ ደስታ” በሚል አርእስት የታተመው ሐዋሪያው ሕጋግትን የያዘው የቅዱስነታቸው መልእክት ከእዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1979 ዓ.ም. ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ከተካሄደ በኃላ ከወጣው “የክርስቲያን ጥበብ” በላቲን Sapientia christiana, በመባል የሚታወቀውን ሐዋሪያዊ ሕግጋትን በማሻሻል የቀረበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ “የክርስቲያን ጥበብ” ወይም በላቲን ቋንቋ Sapientia christiana በመባል የሚታወቀው እና ጳጳሳዊ የትምህርት ተቋማት ሊከተሉት የሚገባቸውን መስፈርት አቅፎ የያዘ  ሕግጋት ከእዚህ ቀደም ለሦስት ጊዜያት ያህል ማሻሻያ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን በእዚህ ሕግጋት ውስጥ የሚገኙ አንድ አንድ ህጎች በካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምስራቃዊያኑና በምራባዊያኑ ሕገ ቀኖና ውስጥ እንዲሰፍር እንዲሰፍሩም ተደርጎ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ መንበር ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እውቅና በመስጠት የምትሰጠውን የከፍተኛ ዲግሪዎችን በተመለከተ የሚያሳዩ ተለያዩ ስምምነቶች የተካተቱበት ሲሆን በእዚህም መስረት ይህ ሐዋሪያዊ ህግጋት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት የተደርገ ማሻሻያ እንደ ሆነም የተገለጸ ሲሆን ይህ ሐዋሪያው ሕግጋት የካቶሊክ የትምህርት መስጫ ተቋማትን በቀጥታ እንደ ሚመለከትም ተገልጹዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.