2018-02-02 14:05:00

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሩሲያ ፌዴሬሽን ብጹዓን ጳጳስትን ተቀብለው አነጋገሩ።


ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሩሲያ ፌዴሬሽን ብጹዓን ጳጳስትን ተቀብለው አነጋገሩ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሩሲያ ፌዴሬሽን ብጹዓን ጳጳስትን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ጳጳሳቱ ከሕዝባቸው ጋር እንዲሆኑ አሳሰቡ። የእግዚአብሔር ቃል የጠማውን ሕዝብ ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በማድረግ ላይ ያሉትን የሩስያ ፌደረሽን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ አግኝተው ባነጋገሯቸው ።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

የሩሲያ ፌዴሬሽን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት አቡነ ፓውሎ ፔዚ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ስለነበራቸው ቆይታ ሲገልጹ፣ ከቅዱስነታቸው ጋር ባደረጉት የሁለት ሰዓት ቆይታ፣ የሩሲያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባኤ ሐዋርያዊ አገልግሎትን በዝርዝር መመልከታቸውን፣ የእያንዳንዱ ጳጳስ የግል ሕይወት ሳይቀር በስፋት መወያየታቸውን ገልጸው በተጨማሪም ከምዕመናን ጋር በመሆን፣ ሐዋርያዊ አገልግሎታችንን ለእግዚአብሔር ሕዝብ እና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ለማከናወን ጥረት ማድረግ እንድሚያስፈልግ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

አንድ እረኛ ከመንጋው መራቅ እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፈለግ በማስታወስ አቡነ ፓውሎ ፔዚ እዳስረዱት፣ ከምዕመናኑ ጋር ሆነው የእግዚአብሔርን እርዳታን በመጠየቅ የመታደስን ተስፋ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል። ይህ ማለት ደግሞ ችግሮቻችንን በሙሉ ድል አድርገናል ማለት ሳይሆን ለምዕመናኑ ወይም ለሕዝቡ ድጋፍ በመሆን በተለይም በመካከላችን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በመንከባከብ ዕለታዊ ተልዕኮአችንን በሚገባ ለማከናወን ጥረት እያደረግን በተስፋ እንጓዛለን ብለዋል።

ብጹዕ አቡነ ፓውሎ ፔዚ ከሩስያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነት በማስመልከት፣ የሞስኮ ፓትሪያርክ ኪሪል ኩባ ላይ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ከተገኛኙበት ጊዜ ወዲህ በሁለቱ አብያተክርስትያናት መካከል፣ የተለያዩ አገልግሎቶችን በጋራ የማከናወንና የወንጌልን ቃል በጋራ የመመስከር ፍላጎት እየጎላ መጥቷል ብለዋል። የሰውን ልጅ ሕይወት ከጥቃት መከላከል፣ አቅመ ደካማ ለሆኑት እገዛን ማድረግ፣ መጥፎ ልማዶችን መዋጋት በሚሉ ጉዳዮች ላይ አብሮ የመሥራት ፍላጎት አለ ብለዋል። የቤተ ሰብ ሁኔታን በተመለከተ የሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ማለትም በሩስያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊት እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕምናንን የሚያሳትፉ ውጥኖችን አውጥተናል ካሉ በኋላ እነዚህ ውጥኖች የሌሎች አገሮች ምዕመናንን እንዲያሳትፉ ተደርገው ተዘጋጅተዋል ብለዋል።     

  








All the contents on this site are copyrighted ©.