Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ንግግሮች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "ትልቁ ኃጢኣት በእግዚኣብሔር ሥም ወንጀል መፈጸም ነው" ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅልሜንጦስ የመሰብሰቢያ አዳረሽ

02/02/2018 15:13

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “በእግዚኣብሔር ሥም የሚፈጸም ግጭት” ማብቂያ ይበጅለት ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን ጥሪ በዛሬው እለት ማለትም በጥር 25/2010 ዓ.ም. ያቀረቡት የሃይማኖትን ሥም ሽፋን በማድረግ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚፈጸሙ ግጭቶች ላይ ለመመካር በቫቲካን በሚገኘው በቅልሜንጦስ የምሰበሰቢያ አዳራሽ ለተሰበሰቡ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህ ጉባሄ “በእግዚኣብሔር ሥም የሚፈጸሙ ግጭቶችን እና ነውጦችን መከላለከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሜልውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው ቀን በቫቲካን በሚገኘው በቅልሜንጦስ የመሰብሰቢያ አዳረሽ ለተገኙ ከተለያዩ ሃይማት ተቋማት ለተውጣጡ ተወካዮች ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተከበራችሁ ወንድሞቼ

እንኳን ደሕና መጣችሁ በማለት ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ እዚህ በመገኘታችሁም በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!

የፖለቲካ ባለሥልጣናት እና የሃይማኖት መሪዎች በሃይማኖት ስም የሚፈጸሙትን የዓመፅ ድርጊቶች እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ለመወያየት መሰብሰባቸው በጣም ጠቃሚ የሆነ ሐሳብ ነው።

በግብፅ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ባዳረኩበት ወቅት (ሚያዝያ 18-20/2009 ..) በወቅቱ በእዚያእግዚአብሔር ነብስን ይወዳል፣ እግዚኣብሔር ሁል ጊዜም ሰውን የወዳል፣ ስለዚህም ማንኛውንም ዓይነት ግጭት የሚፍጥሩ ነገሮችን ማስወገድ ይገባልበማለት ተናግሬው የነበረውን ሐሳብ እንደ ገና ለመጠቀም እፈልጋለሁ። ከሁሉም በላይ በተለይም በዘመናችን የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ይህን ግዴታ እንዲያከብሩ ይጠየቃሉ፣ ምክንያቱም እኛ ፍፁም የሆኑ ነገሮች እንደ ሚያስፈልጉን ሁሉ፣ እነዚህን ፍጹማን የሆኑ ነገሮችን እንዳናገኝ የሚያግደንን ግጭቶችን ማስወገድ አለብን። ግጭት ከማንኛውም እውነተኛ ከሆነ ሐያማኖት  ባሕሪያት በተቃረነ መልኩ የሚገኙ አሉታዊ መገለጫ ነው። የሰብአዊ ክብርን እና ሰብአዊ መብቶችን ጥሰትን ማውገዝ፣ በሃይማኖት ስም የሚቃጡትን ማንኛቸውንም ዓይነት ጥላቻ ለማጋለጥ፣ በእግዚኣብሔር ስም የሚፈጸሙትን ጣዖታዊ ተግባራትን ማጋላጥ ይኖርብናል።

በሃይማኖት ስም እየተስፋፋ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ግጭቶች ያንን ሐይማኖት ክብሩን ያሳጡታል። በዚህም ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ግፍ በሁሉም፣ በተለይም ደግሞ እውነተኛ በሆኑ የሀይማኖት ሰዎች፣ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በመልካም፣ በፍቅር እና በርህራሄ የተሞላ መሆኑን እና በእርሱ ውስጥ የጥላቻ፣ የቅራኔ ወይም የበቀል ስሜት መቼም ቢሆን እንደ ማይኖር በሚሰብኩ ሰዎች አማካይነት ጥላቻ ሊወገዝ ይገባል። አንድ ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው ትልቅ የሆነ በእግዚኣብሔር ላይ የሚቃጣ ስድብ አንድ ሰው የእራሱን ኃጥያት እና ወንጀሎች ለመሸፈን ፈልጎ በእግዚኣብሔር ስም ወንጀል በመፈጸም፣ በተናጥል እና ጅምላ የሆኑ ግድያዎችን ማካሄድ፣ ሰዎችን ለባርነት፣ ለብዝበዛ ማጋልጥ እና ሕዝቦችን በሙሉ ለስቃይ መዳረግ የሚለው ትልቁ ኃጢኣት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።

ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው እግዚአብሔር ቅዱሱ አምላክ መሆኑን እና ማንም ሰው ክፋትን ለመፈጸም  በስሙ መጠቀም እንደማይችል በሚገባ ያውቃል። እያንዳንዱ የሃይማኖት መሪው ከአምላክ ጋር ወይም አማላክ  ካለው ክብር ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ማነኛቸውንም ሙከራዎች በማጋለጥ ማውገዝ ይኖርባቸዋል። ያለንን ኃይል ሁሉ አሟጠን በመጠቀም፣ የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ነብስ ቅዱስ መሆንን በማሳየት እና ከፍተኛ የሆነ ክብር እንዲሰጠው በማድረግ ሰዎች በዘር፣ በሃይማኖ፣ በባህልና በፖለቲካዊ አመለካከቶቻቸው የተነሳ  እንዲሁም በፖለቲካዊ አመለካከቶች ሳቢያ መንገላታት እንደ ሌለባቸው ማሳየት ያስፈልጋል።

የአንድ ሃይማኖት መከበር ለግለሰብ ተጨማሪ ክብርና መብት አይሰጥም፣ እንዲሁም የአንድ ግለሰብ አለመታዘዝ የሃይማኖትን ክብር አይቀንስም።

በፖለቲካ ባለልጣናት፣ በሃይማኖት መሪዎች፣ በመምህራንና፣ በትምህርት፣ ስልጠና እና በመረጃ ልውውጥ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉ፣ እይተዛመቱ የሚገኙትን የተጣመሙ እና የተሳሳቱ አክራሪ የአይማኖት አስተምህሮዎችን ከአንድ እውነተኛ ሃይማኖት መገለጫዎች ጋር የሚጣጣሙ ባለመሆናቸው የተነሳ ይህንን በብርቱ በመቃወም መሥራት ይጠበቅባቸዋል።

ይህም እግዚኣብሔርን ለሚፈልጉ እና እውነትን ለማግኘት የሚፈልጉ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ይረዳል፣ ከፍረሃት ነጻ የምያደርገንን አማላክ ለመገናኘት ያግዛል፣ የእራስ ወዳድነት መንፈስን እና ከጥላቻ ነፃ የሚያደርገንን ለማግኘት እና የእያንዳንዱን ሰው የፈጠራ ችሎታ እና ሀይል በመጠቀም የአማላክን የፍቅር እቅድ እና ሰላምን ለማሰራጨት ለሚፈልጉ ሁሉ የሚሰጥ ነው።

ክቡራን እና ክቡራት  በእውቀትና በፍቅር ላይ የተመሠረተው የሰላም ባህል ለማጎልበት ለባለድርሻ አካላት ይህንን መልእክት ለማስተላለፍ የበኩላችሁን አስተዋጾ ለማድረግ፣ ዝግጁ በመሆናችሁ በድጋሚ አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ። እግዛኣብሔር እናንተን እና ሥራዎቻቹን ይባርክ።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ቀደም ሲል ያዳመጣችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው ቀን በቫቲካን በሚገኘው በቅልሜንጦስ የመሰብሰቢያ አዳረሽ ለተገኙ ከተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት ለተውጣጡ ተወካዮች ያደርጉትንንን ንግግር ሙሉ ይዘት ነበር። አብራችሁን በመሆን ስለተከታተላችሁን ከልብ እናመስገናለን።

 

02/02/2018 15:13